19 hours ago
"የህዝብ፣ በህዝብ፣ ለህዝብ የሆነ አስተዳደር ከምድረ ገጽ አይጠፋም!"— አብርሃም ሊንከን
#ethiopia |ይህ 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብርሃም ሊንከን በፔንስልቬንያ በተደረገው የጌቲስበርግ ብሔራዊ መቃብር ምርቃት ወቅት ያደረጉትና የዓለምን የዲሞክራሲ ስርአት የለወጠ ታሪካዊ ንግግር ነበር።
በወቅቱ አሜሪካ በደም አፋሳሹ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በነበረችበት ወቅት የተደረገው ይህ ንግግር እስከዛሬ ድረስ በዓለም ታሪክ ውስጥ እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ንግግሮች አንዱ ተብሎ ይጥቀሳል።
ንግግሩ እጅግ አጭርና 272 ቃላት ብቻ የነበሩት ሲሆን ለማንበብ ከ2 እስከ 3 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀው።
ከሊንከን በፊት ተናጋሪ የነበሩት ኤድዋርድ ኤቨሬት ለ2 ሰዓታት ያህል ረጅም ንግግር አድርገው የነበረ ቢሆንም ታሪክ ግን የሊንከንን አጭር ንግግር ዘክሮታል።
ሊንከን ዲሞክራሲን "የህዝብ፣ በህዝብ፣ ለህዝብ" በማለት ያቀረቡት ብያኔ እስከዛሬ ድረስ የመንግስታትና የዲሞክራሲ ዋነኛ መለኪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
ንግግሩ በጦርነቱ የወደቁትን ወታደሮች ከማሰብ ባሻገር አሜሪካ አንድነቷ ተከብሮ የሰው ልጅ ሁሉ በነጻነትና በእኩልነት የሚኖርበት ሀገር እንድትሆን አዲስ ተስፋ የሰጠ ነበር።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopiaabrahamlincoln #democracy #government #gettysburgaddress #abrahamlincoln

Comments