13 days ago
የዳግማዊ ቴዎድሮስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቀድሞ መምህራን የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ
#ethiopia | በደብረታቦር ከተማ የሚገኘው የዳግማዊ ቴዎድሮስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች፣ በትውልድ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የቀድሞ መምህራኖቻቸው የምስጋናና የእውቅና መርሃ ግብር አካሂደዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የቀድሞ መምህራን፣ የቀድሞ ተማሪዎችና ሌሎች የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል።
የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኮሚቴ አስተባባሪና በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የጉናና ጣና ልማት ዳይሬክተር ዶክተር ጥላሁን አዱኛ፣ በ1962 ዓ.ም. ትምህርት ቤቱ ከመከፈቱ በፊት የደብረታቦርና አካባቢው ተማሪዎች ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ሌሎች ከተሞች በመሄድ ብዙ ችግር እንደነበረባቸው አስታውሰው፣ ትምህርት ቤቱ ከተከፈተ በኋላ ይህን እንግልት ማስቀረቱን ገልጸዋል።
መምህራን የአገር ባለውለታዎች እንደሆኑ ጠቅሰው፣ ፕሮግራሙ የቀድሞ መምህራኑን "አለንላችሁ" ለማለት፣ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለመዘከርና የአሁኑን መምህራን ለማበረታታት መዘጋጀቱን አስረድተዋል።
የደብረታቦር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን በበኩላቸው፣ መምህራን ጥሩ ዜጋን በመፍጠር ለአገር እድገት የማይተካ ሚና እንዳበረከቱ ገልጸው፣ እንደዚህ ዓይነቱ የምስጋና መርሃ ግብር በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። የከተማ አስተዳደሩም የቀድሞ መምህራንን በተለያዩ መንገዶች ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተማው ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ እየበሩ አእምሮ በበኩላቸው፣ የቀድሞ ተማሪዎች መምህራኖቻቸውን በዚህ መልኩ ማመስገናቸው አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ጠቅሰው፣ የትውልድ ግንባታ ሥራ በትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ተመስጋኝ የነበሩት የቀድሞ መምህራንም፣ ተማሪዎቻቸው ወደ ተሻለ ደረጃ ደርሰው ዛሬ አስታውሰው በማክበራቸው ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው፣ የአሁኑ መምህራንም ስነ-ምግባር የታነፀና ለአገሩ የሚጠቅም ትውልድ ለማፍራት ተግተው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
በፕሮግራሙ መጨረሻ ለቀድሞ መምህራን የእውቅና ሰርተፍኬትና የገንዘብ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፣ የመርሃ ግብሩ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን

1 month ago
ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ 758 ተማሪዎችን ለ15ኛ ጊዜ አስመረቀ
#ethiopia | የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ሲያስተምራቸው የቆዩ 758 ተማሪዎችን ለ15ኛ ጊዜ አስመረቀ።
ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብሮች፣ በመደበኛ፣ በኤክስቴንሽን እና በክረምት ፕሮግራሞች ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን በተመራቂዎች ቤተሰቦችና በተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ሥነ-ስርዓት አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተናገሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን አበጋዝ፣ ተመራቂዎቹ ከብዙ ጥረትና ትጋት በኋላ ለዚህ ደረጃ መብቃታቸውን አድንቀው፣ ምረቃ የሕይወት አዲስ ምዕራፍ እንጂ መጨረሻ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ተመራቂዎችም በሙያቸው ውጤታማ ለመሆን እና ለአገር ልማት አስተዋፅኦ ለማበርከት በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንቱ ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት አገልግሎት በተጨማሪ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ጉልህ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸው፣ የደብረታቦር ከተማ ህዝብ ለተማሪዎችና ለዩኒቨርሲቲው እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በምረቃው ልዩ ትኩረት የሳቡት ከደቡብ ሱዳን በትምህርት ዕድል መጥተው ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ የተማሪዎቹ ተወካይ በዩኒቨርሲቲውና በአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍ እንዳገኙ ገልጻለች። በቆይታቸውም የኢትዮጵያን ባህልና እሴቶች ማወቅ እንደቻሉ ጠቅሳ፣ ይህንን ልምድ ወደ አገራቸው ይዘው እንደሚመለሱ ተናግራለች።
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ከየኮሌጁና ከየኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፣ ከሴት ተመራቂዎች መካከል የሜዲካል ላቦራቶሪ ሳይንስ ዲፓርትመንት ተማሪ እየሩስ ተቀባ 3.9 ነጥብ በማስመዝገብ ልዩ ተሸላሚ ሆናለች።
በአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ውጤት ባለቤት የሆነው የሜዲካል ላቦራቶሪ ሳይንስ ተማሪ አሸናፊ ታከለ 3.97 ነጥብ በማስመዝገብ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ከ32 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች አስመርቋል።
– ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን

5 months ago
🎓 እናትና ልጅ አብረው ተመረቁ
#ethiopia | በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ 14ኛው ዙር የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ በመድረኩ ከተሰለፉት 1,254 ተማሪዎች መካከል የሁለት ሴቶች ታሪክ የዕለቱ ዋነኛ መነጋገሪያ ሆኗል። እናት ወይዘሮ ትግስት ታከለ እና ልጃቸው ሰላማዊት ተድላ በማኔጅመንት የትምህርት ዘርፍ ትምህርታቸውን አጠናቀው በአንድ ቀን፣ በአንድ መድረክ ካባ ለብሰው ተመርቀዋል።
ከቤት እስከ ዩኒቨርሲቲ - የጋራ ጉዞ
እናት ልጇን ከኬጂ ጀምሮ ኮትኩታ ለዩኒቨርሲቲ ማብቃት ብቻ ሳይሆን፣ አብሯት ተማሪ ሆና ተመራቂ መሆኗ ለታዳሚው ልዩ ስሜት ፈጥሯል። እናት ትግስት ታከለ በመማር ሂደቱ ውስጥ የገጠማቸውን "በዚህ እድሜ ተምረሽ የት ልትደርሺ ነው?" የሚል ተስፋ አስቆራጭ ትችት፣ በትጋትና በውጤት በመመለስ ለብዙዎች አርአያነታቸውን አሳይተዋል።
"ልጅን እያስመረቁ አብሮ መመረቅ ደስታው ወደር የለውም፤ ትምህርት እድሜ አይገድበውም!" — እናት ትግስት ታከለ
የእናት ጉያ እንደ ጥንካሬ ምንጭ
ልጅ ሰላማዊት ተድላ ከእናቷ ጋር በአንድ ክፍል ተቀምጣ መማሯ ትልቅ የሞራል ጥንካሬ እንደሆናት ትገልጻለች። እናቷ አጠገቧ መሆኗ ጊዜዋን በአግባቡ እንድትጠቀም እና ከአልባሌ ነገሮች ተቆጥባ ለስኬት እንድትበቃ ትልቅ አጥርና መነሳሳት እንደሆናት በደስታ ትናገራለች።
የወደፊት ራዕይ፡ ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት
ይህ የእናትና ልጅ ጥምረት በምርቃት ብቻ የሚያበቃ አይደለም። ሁለቱ ተመራቂዎች ወደፊት በጋራ በመሆን የራሳቸውን ስራ ለመፍጠር (Entrepreneurship) ወጥነዋል። በተጨማሪም ትምህርታቸውን በሁለተኛ ድግሪ ለመቀጠል ትልቅ ተስፋ ሰንቀዋል።
እናት ትግስት ታከለ ለሁሉም ስኬቶች መሰረቱ ሰላም መሆኑን በማሳሰብ፣ ትውልዱ ሰላምን በማጽናት ለሀገር ዋልታ እንዲሆን የሚከተለውን የወላጅነት መልዕክት አስተላልፈዋል፦
"ሰላም ከራስ ይጀምራል!"
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #አሚኮ #ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ #የእናት_ፍቅር #ትምህርት_ለዘላለም #አርአያነት #ኢትዮጵያ #ስኬት

6 months ago
🏗️ በደብረታቦር ከተማ በትልቅ በጀት እየተከናወኑ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ተጎበኙ
#ethiopia | የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ወይብላ ካምፖስ እና ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ከተጎበኙት ውስጥ ይጠቀሳሉ
የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በደብረታቦር ከተማ በመንግስት ከፍተኛ በጀት እየተገነቡ ያሉ ወሳኝ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
በምልከታው የተዳሰሱ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች፡
🏫 የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ወይብላ ካምፖስ ግንባታ፣
📚 የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ፕሮጀክት፣
🏪 የገበያ ማዕከል ግንባታ እና ሌሎችም የልማት ስራዎች ናቸው።
በጉብኝቱ ላይ የተገኙ ከፍተኛ አመራሮች፡
አቶ ይርጋ ሲሳይ - የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ መልካሙ ፀጋየ - የአብክመ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሲሳይ ዳምጤ - የአብክመ መሬት ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሙሉቀን ሰጥየ - የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ለከተማዋ እድገት እና ለህዝቡ ተጠቃሚነት ከፍተኛ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን
#debretabor #development #projects #amhararegion #education #infrastructure #visit #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments