የዳግማዊ ቴዎድሮስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቀድሞ መምህራን የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ
#ethiopia | በደብረታቦር ከተማ የሚገኘው የዳግማዊ ቴዎድሮስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች፣ በትውልድ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የቀድሞ መምህራኖቻቸው የምስጋናና የእውቅና መርሃ ግብር አካሂደዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የቀድሞ መምህራን፣ የቀድሞ ተማሪዎችና ሌሎች የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል።
የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኮሚቴ አስተባባሪና በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የጉናና ጣና ልማት ዳይሬክተር ዶክተር ጥላሁን አዱኛ፣ በ1962 ዓ.ም. ትምህርት ቤቱ ከመከፈቱ በፊት የደብረታቦርና አካባቢው ተማሪዎች ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ወደ ሌሎች ከተሞች በመሄድ ብዙ ችግር እንደነበረባቸው አስታውሰው፣ ትምህርት ቤቱ ከተከፈተ በኋላ ይህን እንግልት ማስቀረቱን ገልጸዋል።
መምህራን የአገር ባለውለታዎች እንደሆኑ ጠቅሰው፣ ፕሮግራሙ የቀድሞ መምህራኑን "አለንላችሁ" ለማለት፣ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለመዘከርና የአሁኑን መምህራን ለማበረታታት መዘጋጀቱን አስረድተዋል።
የደብረታቦር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን በበኩላቸው፣ መምህራን ጥሩ ዜጋን በመፍጠር ለአገር እድገት የማይተካ ሚና እንዳበረከቱ ገልጸው፣ እንደዚህ ዓይነቱ የምስጋና መርሃ ግብር በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። የከተማ አስተዳደሩም የቀድሞ መምህራንን በተለያዩ መንገዶች ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተማው ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ እየበሩ አእምሮ በበኩላቸው፣ የቀድሞ ተማሪዎች መምህራኖቻቸውን በዚህ መልኩ ማመስገናቸው አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ጠቅሰው፣ የትውልድ ግንባታ ሥራ በትብብር ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ተመስጋኝ የነበሩት የቀድሞ መምህራንም፣ ተማሪዎቻቸው ወደ ተሻለ ደረጃ ደርሰው ዛሬ አስታውሰው በማክበራቸው ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው፣ የአሁኑ መምህራንም ስነ-ምግባር የታነፀና ለአገሩ የሚጠቅም ትውልድ ለማፍራት ተግተው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
በፕሮግራሙ መጨረሻ ለቀድሞ መምህራን የእውቅና ሰርተፍኬትና የገንዘብ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፣ የመርሃ ግብሩ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን

13 days ago