13 days ago
"በዐይኔ በብረቱ ...!"
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም ማህበራዊ ጉዷንም፣ ገዷንም በድሯ ሸምና የሰው ልጅ የደረሰበትን ታላላቅ አብዮቶች ታስመለክተን ይዛለች ።
ይህ የዲጂታሉ ዘመን፣ አዲስ መስኮት ነው።
የዓለምን ታሪክ ሰፊ ንዋይ፣ ብዙ የሰው ኃይል እና ጊዜ በልቶ የመንገር ሩጫ በዚህ የመስኮት አቋራጭ በግለሰቦች ስልክና ካሜራ መዳፍ ላይ እየወደቀ ነው።
የማህበራዊ ትስስር ሜዳው ከትናንት ዛሬ፣ ከዛሬም ነገ ትተው ቢሄዱ ቆሞ አይጠብቅም። በዐይን ጥቅሻ ፈትለክ ነው። ለውጡ ፈጣን፣ ተለዋዋጭነቱ ነቅተው እንደ ቴኒስ ዳኛ ወዲህ ወዲያ አንገትዎን የሚነቀንቅ ሆኗል።
ወደ ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ የካሜራ ሌንሳቸውንና በሚሊየን የሚከተሏቸውን ዐይን ይዘው የሚመጡ የመስኮቱ ዘዋሪዎች ለኢትዮጵያ አዲስ ነጋሪት የሚጎስሙ ናቸው።
በሚሊየን የሚቆጠሩ ተከታዮቻቸው በየሰከንዱ ለሚለቀቁ ይዘቶች ሲሉ ዐይንና ጆሯቸውን በእነዚህ የዘዋሪዎች ዳና ላይ አድርገዋል።
ምክንያቱም ዓለም የዲጂታል ዝመና አብዮቷ ላይ ወደ ፊት እንጂ የኋልዮች ዳራዋን ለመመልከት አፍታም የላትም፤ ተከታዮቻቸውም ጊዜ የለቸውም። አጭር፣ ፈጣን፣ አዲስ ይናፍቃሉ።
የአሜሪካው ታዋቂ የቀጥታ ስርጭት አቅራቢ አይሾው ስፒድ፣ እንዲሁም ከ19 ሚሊየን በላይ የቲክቶክ ተከታዮች ያሉት የዲጂታል ዜና አቅራቢው ዲላን ፔጅ ወደ አዲስ አበባ መምጣት ኢትዮጵያ በአፍሪካ የዲጂታል ዲፕሎማሲና የቱሪዝም ስበት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን የሚያሳይ ትልቅ የጂኦፖለቲካዊና የማኅበራዊ ሚዲያ ለውጥ ማሳያ ነው።
ቀድሞ በኢትዮጵያ ፍቅር የወደቀው ብሪታኒያዊው የቲክቶክ ዜና አቅራቢ ዲላን ፔጅ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታና ስለ ኢትዮጵያውያን የአንድነት መንፈስ በአዎንታ በመዘገብ መንፈሱ ከአካሉ ቀድሞ አዲስ አበባ ከደረሰ ከርሟል።
ይህ ፕሮጀክት በውጭ ዕዳ ሳይሆን በሕዝብ ቦንድና በላብ የተገነባ ነው በማለት አጉልቶ አሳይቷል።
ግድቡንም “በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የሚቀይረው የአፍሪካ የብርሃን ተስፋ” በማለት ለዓለም ማስተዋወቁን አንረሳም።
ዲላን በርካታ ቀናትን የሚወስደውን ታላቁን ጉዞዬን፣ በቅኝ ግዛት ባልተገዛችው ሀገር ኢትዮጵያ ጀምሬያለሁ በማለት ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ይዞት የመጣው የካሜራ ሌንስ የኢትዮጵያን ጥንታዊነት ብቻ ሳይሆን አዲሱን የቴክኖሎጂ ምዕራፍም ጭምር የገለጠ ሆኗል።
በአዲስ አበባ ቆይታው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን በጎበኘበት ወቅት፥ ይህን በቴክኖሎጂ የተቃኘ ቦታ ሳየው ተደምሜያለሁ፤ አፍሪካ ተቀይራለች፣ አዲሱን ገፅታዋን ለዓለም የሚያሳይ ቦታ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብሏል።
አዲስ አበባ በቅርቡ ከ30 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡና በጥምረት ከ470 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ያሏቸው ከ200 በላይ የዲጂታል ፈጣሪዎች የተሳተፉበትን የአፍሪካ ማኅበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ጉባኤን ማስተናገዷ የይዘት ፈጣሪዎች የዲፕሎማሲ ዋና ከተማ አድርጓታል።
በጉባኤው ላይ በቀረቡ መረጃዎች መሠረት ስለ አፍሪካ የሚሰራጩ የተዛቡና አሉታዊ ትረካዎች በአህጉሪቱ ላይ በየዓመቱ እስከ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ የኢኮኖሚ ኪሳራ ያደርሳሉ።
ዲላን ፔጅ እና መሰል የይዘት ፈጣሪዎች ይህንን የተዛባ ምስል ለመስበር 'ሳይነገራችሁ በዓይናችሁ እዩት' በሚል መርህ እየመጡ ነው።
የዲላን ፔጅ ጉዞ ስኬታማ እንዲሆን እንደ አዶናይ ያሉ የሀገር ውስጥ ይዘት ፈጣሪዎች የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው።
የተጽእኖ ፈጣሪዎች ጉብኝት የዲጂታል ዲፕሎማሲና የሀገር ገፅታ ግንባታ ወሳኝ ተግባር ሲሆን፥ የወቅቱ የሀያላን ሀገራት ፉክክር ገር ኃይል መሆኑን ላጤነ ዲፕሎማሲው ይገለጥለታል።
ገር ዲፕሎማሲ ሰዎችን ሳያስገድዱ፣ ወደውና ፈቅደው አንተ የምትፈልገውን ነገር እንዲያደርጉ የማድረግ ብቃት መሆኑን የጽንሰ ሀሳቡ ፈጣሪ አሜሪካዊው ጆሴፍ ናይ ያስረዳሉ።
ለጆሴፍ ምስጋና ይግባውና ሀገራት ከጦር መሳሪያ እሽቅድምድሞሽ ወደ ለስላሳው አቀራረብ ፊታቸውን እንዲያዞሩ አድርጓል።
ከአሜሪካ ገር መንገዶች መካከል ሆሊውድ፣ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ብራንዶች (አፕል, ጎግል, ማይክሮሶፍት)፣ ምግቦች (ማክዶናልድ፣ ኮካ ኮላ) እና ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ይጠቀሳሉ።
ለደቡብ ኮሪያ "ሃሊዩ" ወይም የኮሪያ ማዕበል። ይህም የኬ-ፖፕ ሙዚቃ፣ የኮሪያ ፊልሞችና ድራማዎች እንዲሁም የውበት ምርቶች፤ ለብሪታንያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ፣ ቢቢሲ እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ገሩ መንገዳቸው ነው።
ሳዑዲ ዓረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እንደ ማንችስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድ የእግር ኳስ ክለቦችን በመግዛት እንዲሁም የዓለም ዋንጫዎችን በማዘጋጀትና እንደ ሮናልዶ ታዋቂ ተጫዋቾችን ወደ ሀገራቸው በማምጣት የዓለምን ትኩረት በመሳብ የሀገራቸውን ገጽታ እያደሱ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያም ምድረ ቀደምት፣ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክት የአድዋ ድል፣ የፓን-አፍሪካኒዝም ማዕከል መሆኗ፣ የቡና መገኛነቷ፣ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎቿን በማስተዋወቅ የራሷን የዲጂታል ለስላሳ ኃይል እየገነባች ትገኛለች።
በዚህም በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ፈጣን የኢኮኖሚ መነቃቃትን ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ ይህንን ወርቃማ የዲጂታል ዲፕሎማሲ ዕድል በመጠቀም፣ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ምሰሶዎቿን ለማጠናከር በጥበብና በስልታዊ መሪነት ልትራመድበት ይጠበቃል።
ዲጂታሉ ዓለም በሮችን ከፍቷል፤ የኢትዮጵያን መልኮች በአዲሱ ነጋሪት ማስተጋባት የዛሬ ስራ ነው ።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

3 months ago
“በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት ግንባታ በእጅጉ ተደንቂያለሁ”
#ethiopia | በኢትዮጵያ ያለውን የመሰረተ ልማት ግንባታና የሕንጻ ጥበብ በመመልከት በጣም መደነቁን ታዋቂው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ አይሾው ስፒድ ገለጸ።
የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ አይሾው ስፒድ ለ30 ቀናት በአፍሪካ የነበረውን ቆይታ በተመለከተ በሰጠው ቃለ መጠይቅ፤ በኢትዮጵያ ያየው የመሰረተ ልማት ግንባታ እጅግ አስገራሚ መሆኑን ገልጿል።
በጉዞው ካያቸው ሀገራት ሁሉ የኢትዮጵያ የሕንጻ ጥበብ ምርጡ መሆኑን ጠቅሶ፤ የሕንጻዎቹ ጥበብ የወደፊቱን ጊዜ ቀድሞ የተነበየና የራሱ የሆነ አፍሪካዊ ወይም ኢትዮጵያዊ ቅኝት እንዳለው አስረድቷል።
አዲስ አበባ ከተማን ያደመቁት ዘመናዊ ሕንጻዎችና ግዙፍ የዲጂታል ስክሪኖች ከተማዋን ልዩ እንዳደረጓት የገለጸው አይሾው ስፒድ፤ የሕንጻዎቹ አወቃቀር ከሌላው ዓለም የተለየና የሀገሪቱን ማንነት የሚገልጽ መሆኑን ተናግሯል።
ይህ ልዩ የሕንጻ ጥበብና ፈጣን የመሰረተ ልማት ዕድገት ለሀገሪቱ ገጽታ ግንባታ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም በንግግሩ አመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #epa #ኢትዮጵያ #አይሾው_ስፒድ #መሰረተ_ልማት #ሕንጻ_ጥበብ #አዲስ_አበባ #ishowspeed

4 months ago
የአይሾው ስፒድ የጋና ጉብኝትና የሺአ ቅቤ ሙዚየሙ ድንገተኛ ስኬት
#fastmereja I ታዋቂው ዩቲዩበር አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) በቅርቡ በጋና ያደረገውን ጉብኝት ተከትሎ፣ የሃማማት ሞንቲያ የሺአ ቅቤ ሙዚየም (Hamamat Montia Shea Butter Museum) እስከ መጋቢት 16 ቀን 2026 ድረስ ሙሉ በሙሉ መያዙ (Sold Out) ተነገረ።
ሙዚየሙ በአይሾው ስፒድ የቀጥታ ስርጭት ላይ ከታየ በኃላ በ24 ሰዓታት ውስጥ እስከ መጋቢት ወር ድረስ ያሉት ቀጠሮዎች በሙሉ ተይዘዋል። ስርጭቱ ከ50 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾችን ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ ይህም ለሙዚየሙ ዓለም አቀፍ እውቅናን አትርፎለታል።
የሙዚየሙ ባለቤት ሃማማት ሞንቲያ እንደገለጸችው፣ የስፒድ ጉብኝት ሙዚየሙ ታስቦ የማይታወቅ ከፍተኛ ታዋቂነት እንዲያገኝ ረድቶታል።
ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ ዓይነቱ በነፃ የተገኘ ማስታወቂያ በተለመደው የግብይት መንገድ ቢሆን ኖሮ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ሊያስወጣ ይችል ነበር።

አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) የጋና ፓስፖርት ሊሰጠው ነው
#fastmereja I ታዋቂው አሜሪካዊ የኢንተርኔት ሰው Darren Watkins Jr. (በተለዋጭ ስሙ አይሾው ስፒድ) በቅርቡ በጋና ባደረገው ጉብኝት ወቅት እናቱ ጋናዊት መሆኗን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ መንግስት የጋና ፓስፖርት እንዲሰጠው ወስኗል።
ስፒድ በጋና በነበረው ቆይታ እናቱ የጋና ተወላጅ መሆኗን ለተከታዮቹ ገልጿል። ይህም "ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ" በማለት ደስታውን እንዲገልጽ አድርጎታል።
የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ሳሙኤል ኦኩዴቶ አብላክዋ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስፒድ ለጋና በጎ ገጽታን በመገንባት ረገድ ያሳየው ተነሳሽነት የሚደነቅ በመሆኑ የጋና ፓስፖርት እንዲሰጠው ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ማጽደቁን አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ ስፒድን ለጋና "ተገቢ አምባሳደር" ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ በዲጂታል ሚዲያ ያለውን ግዙፍ ተፅዕኖ ለሀገሪቱ ገጽታ ግንባታ እንደሚጠቅም ገልጸዋል።
ስፒድ ይህንን ውሳኔ ያገኘው ኢትዮጵያን ጨምሮ 20 የአፍሪካ ሀገራትን ለ28 ቀናት በጎበኘበት "Speed Does Africa" በተሰኘው ታሪካዊ ጉዞው ማጠቃለያ ላይ ነው።
ይህ እርምጃ ጋና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ጋናውያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የምታደርገው ጥረት አካል ተደርጎ ተወስዷል። ስፒድ በአሁኑ ወቅት በዩቲዩብ (YouTube) ብቻ ከ50 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን፣ የአፍሪካ ጉዞው በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ነበር።

5 months ago
የደሃ ሃገር ወጣት I ShowSpeed ን አይኮርጅም !
(የኔ ምልከታ) #ethiopia | አይሾውስፒድ 'Contentless Content' ይዞ ጥድፊያና ሁካታ ወዳድ የዓለም ዜጎችን እያስከተለ ያለ ለጋ ወጣት ነው፡፡ ዓለም የጥድፊያ እና ሁካታ (speed and chaos) መድረክ ናትና ሁካታ ወዳድ ዜጎች ቢኖሯት አይገርምም፡፡ ስፒድም መቶ ቀርቶ ሁለት መቶ ሚሊዮን ተከታይ ቢኖረውም አይደንቅም፡፡ ፍላጎት ባለበት አቅርቦት አትራፊ ነው፡፡
ባልቲሞር ውስጥ በሚገኘው የጥንቱ የቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን በ1692 ዓ.ም ተጠቅልሎ የተገኘ ዴዜዴራታ የሚባል መመሪያ እንዲህ ይላል፡፡ "በዚህ ዓለም ጥድፊያና ሁካታ ሳትበገር በርጋታ ኑር"
ዴዜዴራታ ካዛሬ 300 ዓመት በፊት የዓለምን ‘የጥድፊያና ሁካታ’ መንደርነት መዝኖ ነው በዚህ ውስጥ ለመኖር እርጋታ በጣም አስፈላጊ መሆኑን የመከረው፡፡ ረጋ ያሉ ብቻ ጥድፊያውንና ይዞት የሚመጣውን ደራሽ በዘዴ ያልፉታል፡፡
ስፒድ [ኮንቴንት ከተባለ] ኮንቴንቱ 'ጥድፊያ እና ሁካታ' ብቻ ናቸው፡፡ 'በክዋኔም፣ በንግግርም “ጥድፊያ”ን በማሳየት ነው ብራንዱን የቀረጸው ፡፡ ያንን ደግሞ ከጩኸት (ሁካታ) ጋር አስተሳስሮታል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ኢነርጂ (ጉልበት) ጨምሮበታል፡፡ እነዚህ ሶስቱ ሲቀናጁ የርሱን ኮንቴንት ፈጥረዋል፡፡
ስለዚህ መረጋጋት የስፒድ መለያ አይደለም፡፡ ይጮሃል እንጂ አያወራም፣ ይሮጣል እንጂ አይቆምም፡፡ ዘፈቀደ እንጂ የተሰተረ ነገር (setup) አይወድም፡፡ በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ምንም መስራት አይችልም፡፡ ትክክለኛው የዚህ ዓለም ጥድፊያና ሁካታ መገለጫ ይሄ ልጅ ነው፡፡
ይህ ልጅ በልጅነቱ ወላጆቹ ‘ስፒድ’ የሚል ቅጥያ ስም ያወጡለት አለነገር አይመስለኝም፡፡ በተፈጥሮው Hyperactive የሚባል አይነት ሰው እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ ሰውነቱ የሚያመነጨው የሚያስጨንቅ ኢነርጂ አለው፡፡ ያንን ኢነርጂውን በጩኸት እና በጥድፊያ ያወጣዋል፡፡ እሱን የሚያረጋጋውም ይኸው ነው፡፡
ባለሙያ ባልሆንም ጥቂት በማውቃት ሳይንስ ልክ …ስፒድ በግልጽ የሚታይ ADHD የተባለ የትኩረት ማጣት እና መቅበጥበጥ (አለመረጋጋት) የሚያስከትል Disorder እንዳለበት የሚያሳብቁ ምልክቶችን አይቼበታለሁ፡፡ ተረጋግቶ ቁጭ አለ ስትለው ድንገት እንደእንቁራሪት እንጣጥ ይላል፡፡ ስላሴ ቤተክርስቲያን ሲገባ የሆነውንና ያሳየውን ድርጊት ካያችሁት በቂ ነው፡፡ ያንን የተረጋጋ ስፍራ ለሰከንዶች መልመድ ተቸገረ፡፡ ራሱን ለመቆጣጠር ሲሞክር ይታያል፡፡ ውስጡ እምቢ ሲለውና ሲዘል አያችሁት፡፡ ብቻውን ጣቶቹን እየፈተለ በማይሰማ ድምጽ እያነበነበ ነበር፡፡ ከዚያ እንደወጣ የተጠራቀመ ኢነርጂውን እንዴት እንዳወጣውም ታዝባችኋል፡፡
ስፒድ ኮንተንቱን እንዲሰራ የሚመቸው ጫጫታና ጩኸት እንጂ ዝምታና እርጋታ አለመሆኑን ግብጽ ጊዛ ፒራሚዶች ውስጥ ከነበረው ‘ቶታል ሸትዳውን’ ትረዳላችሁ፡፡ የርሱ ተከታዮችም የሚፈልጉት ሁካታ ስለጠፋ ያኔ ቁጥራቸው ዝቅተኛ ነበር፡፡
በዚህ ዘመን የሰለጠነ ሃገር ውስጥ በተለይ በምዕራቡ ስልጣኔ ውስጥ ላለ ዜጋ እርጋታና ቁምነገር ቦታ የላቸውም፡፡ ምክንያቱም ያንን የርጋታ 'ስቴጅ' በትውልድ ቅብብል አልፎት መጥቷል፡፡ የህዝቡ ኑረት ከባህል፣ ወግ እና ልማድ አፈትልኮ ወጥቶ በግል አዳሪነት ላይ ተመስርቷል፡፡ ማህበረሰባዊ ደንብ የሚባል ነገር የለም፡፡ እንደእብድ ውሻ መክለፍለፍን ከምንም በላይ ዋጋ ሰጥቶ ያያል፡፡ አብርሃም ማስሎው የሰው ልጅ ፍላጎቶችን በ5 ደረጃዎች የተነተነበት ‘ማስሎው ቲየሪ’ እንደሚነግረን ከሆነ አብዛኛው በምዕራቡ ስልጣኔ ውስጥ የሚኖረው ዜጋ አሁን ያለበት ደረጃ 4ኛው “እውቅናና ክብርን ለማግኘት” የመፈለግ’ ደረጃ ነው፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት ያሉትን ሶስት ደረጃዎች በአብዛኛው አሟልቶ ‘ሳቹሬት’ አድርጓል፡፡ምግብ መጠለያ ሰላም ፍቅር ወዘተ አያሳስቡትም፡፡ ስለዚህ ዛሬ ለእርጋታና ስክነት ቦታ የለውም፡፡
ይኼ የዕድገት ‘ኢቮሉሽን’ ይዞት የመጣ ክስተት ነው፡፡ በዚህ የ GEN Z ዘመን ስክነት አይፈለግም፡፡ ባህሉና ስሪቱ ፍጥነት እና ጥሶ መሄድ ብቻ ነው ፡፡ አለም ዴዜዴራታ በተጻፈበት ዘመን ከተገለጸችበት በከፋ ሁካታና ጥድፊያ ውስጥ ናት፡፡ ስፒድ ይህንን የትውልዱን ይዘት ይዞ ቢመጣ፣ ሚሊዮን ቀርቶ ቢሊዮን ተከታዮችን ቢያፈራም አይደንቅም፡፡
እኔን ብዙዎቻችን ካደግንበት እና ከኖርንበት ባህል እና አስተዳደግ አንጻር አይደለም የአዲሱን ዘመን ጥድፊያ እና ሁካታ እየመንኩ ያለሁት፡፡ “ገና ባልደረስንበት ደረጃ ላይ ስንንጠላጠል ያልረገጥናቸው ደረጃዎች እንዳይክዱን እንጠንቀቅ” ነው እያልኩ ያለሁት፡፡ ማንንም በማይጠቅም የዲጂታል ጩኸት ላይ የተጠለፈውን ትውልድ የምመክረውም ይህንኑ ነው፡፡እንዳለመታደል ደንብና ህግ በሌለባት ሃገር ኢንተርኔት ይዞት የመጣውን ሁሉ ‘አዳፕት’ እንዲያደርግ ክፍቱት የተተወ የወጣት ጭንቅላት ስለስራ ማሰብ እየተሳነው እያየን ነው፡፡
ድሆች ነን፡፡ እንደህዝብም እንደሃገርም ከጩኸትና ሁካታ በፊት ገና ብዙ መስራት ያለብን የቤትስራዎች ይጠብቁናል፡፡ ከላይ በገለጽኩት ምክንያት ስፒድን የሚከተለውን 90 ምናምን ሚሊዮን የሞላለት የሰለጠነ ሃገር ህዝብ አይተን ‘ዘመኑ የሚጠይቀው ይህንን ነው’ ማለትና ያንኑ እዚህ አምጥቶ ‘ባህል’ ለማድረግ መሞከር ልክ አይደለም፡፡ የሰለጠነው ዓለም ዛሬ "ባዶ ቅል እና የሚንሸዋሸው ናስ' ለሚያወጣው ትርጉምየለሽ ድምጽ በጣም ያጋደለው እኛ ዛሬ ያለንበትን ደረጃ ለፍቶበት፣ ፈጥሮበት፣ ሰርቶበትና ተጠቅሞበት አልፎ ነው፡፡
ሰርቶ፣ ፍሬውን አፍርቶ፣ ጎተራ ከትቶ፣ ራሱን ከድካም አላቅቆ፣ ለልጆቹ ቀላል ህይወትን ሰጥቶ ያለፈ የቀደመ ትውልድ ነው ይህን ‘የአይሾው ስፒድ’ ተከታይ የሆነ ሚሊዮን ግሪሳ ወጣት የፈጠረው፡፡ ለብዙ መቶ አመታት በፈጠራ አዕምሮውን አስጨንቆ፣ በጠንካራ ጉልበት ፋግሮ ሃገር ሰርቷል፡፡ ስርዓት ገንብቷል፡፡ ለሚቀጥሉት ብዙ መቶ አመታት እሱና ትውልዱ የሚኖሩበትን ትሩፋት አጠራቅሟል፡፡ በዚህ ሳቢያ ዛሬ ጥያቄው እንደኛ ምግብና ሰላም ሳይሆን ‘መታወቅ’ ብቻ ነው፡፡'አይረቤ ጉዳይ ላይ' ተጠምዶ የምታዩት የልፋቱን ገጽ ስላለፈውና የእረፍቱ ገጽ ላይ ስለደረሰ ነው፡፡ ‘ኢቮሉሽኑ’ እዚህ አድርሶታል፡፡
እናም እንዳትሳሳቱ! የሰለጠነው አለም ህዝብ በጩኸትና ሁካታ ተጠምዶ ስታዩት ስሪቱ ከጅምሩ ይህ ሆኖ አይደለም፡፡ መዝናናትን የቅንጦት አድርጎ እስኪቆጥር ድረስ ላቡ ጠብ እስኪል ሰርቶ፣ ‘ኮንፋይንድ' ብቻውን አውርቶ ነው፡፡ ዛሬ በአደባባይ እንደውሻ መጮህን የሚያደንቀውና የሚያዳንቀው ያንን ደረጃ ስላለፈው ነው፡፡
እኛ ግን ገና ነን፡፡ በአይረቤ የባዶ ቅል ጩኸት ለመመሰጥ ገና ነን፡፡ ገና ምግብ አጥተን እየራበን ነው፡፡ ገና ስራ አጥተን እየደኸየን ነው፡፡ ገና ትምህርት አጥተን እየደነቆርን ነው፡፡ ገና ሰላም አጥተን እየተዋከብን ነው፡፡ ገና ገና ገና ብዙ ገናዎች አሉን፡፡ ያለንበት ደረጃ ሁሉን ትተን ለመዝናናትና ለመንዘፍዘፍ የሚያበቃን አይደለም፡፡
ስለዚህ ስፒድን ምሳሌ እያደረጋችሁ “ዘመኑ የቁምነገር አይደለም ፣ የትምህርት አይደለም፣ የስራ አይደለም፣ የልፋት አይደለም፣ የአቋራጭ 'ኮንተንት አልባነት ዘመን ነው “ የምትሉ ሰዎች ከዚህ ጠማማ መፈክራችሁን ተግ በሉ !
የቆማችሁበትን የአሸዋ መድረክ ስታዩት ዛሬ የምታዘናጉትና የምታዳንቁት የዲጂታል ትውልዱ ‘አልባሌነት’ የሚያስከፍለን የነገ ዋጋ ይገባችኋል፡፡ የቤትስራውን ጨርሶ ከሚዝናና አስተማሪ ጋር ዝላይ የሚጫወት ተማሪ መጨረሻው ተማሪም አስተማሪም እንዳይሆን በዚያው ተሰባብሮ መቅረት ብቻ ነው፡፡ እነሱና እና የሌለ ልዩነት ላይ ነን፡፡ አይናችሁን ግለጡ፡፡ አሁን ባለንበት ደረጃ ከአይሾው ስፒድ ወጣቶቻችን የሚወስዱት ትምህርትም የሚቀስሙት ልምድም የለም፡፡
ወጣቶች የስፒድን 'ኮንቴንት' እንደትሬንድ ይዘው ጥድፊያና ሁካታ ውስጥ መግባት ልክ ነው ብለው ማሰባቸውን አታበረታቱ፡፡ እንደውሻ እየጮህን ሃገራችንን እናስጠራለን ያለ ጨበሬ አይቻለሁ፡፡ በምታዳንቁት የዲጂታል ትውልድ ዘንድ እንግዲህ ሃገር ማስጠራት ትርጉሙ ይህ ነው፡፡
ሃገር ተረካቢ ናቸው ሲባሉ ትምህርትም ስራም ትተው ቤት የተቀመጡና ምንም ሳይሰሩ ስኬትን በላይክ እና ኮሜንት ብቻ የሚመዝኑ የድቡሽት ላይ ጎጆዎች በዝተዋል፡፡ በመሰረቱ እነሱም ስፒድ ለማንም ምንም አይጠቅሙም፣ ጠቅመውም አያውቁም፡፡ ከጠቀሙ ለራሳቸው ብቻ ነው፡፡ ተከታዮቻቸው ላይ እንጀራ ይጋግራሉ፡፡ አለቀ!!
ሃገር የሚያተርፈውና ራሱም የሚተርፈው ትውልድ በዲጂታሉ አለም መማርና ከረሱ አልፎ የሌሎችን ሀይወት መለወጥ የሚችል ኮንቴነት ይዞ የሚመጣው የነቃ ትውልድ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የደሃ ሃገር ወጣት ስፒድን አይኮርጅም፡፡ ስፒድ አባቶቹ የሰሩለት የተጠናቀቀ ሃገር ያለው ልጅ ነው፡፡ ሌላ ስራ የለበትም፡፡ እኛ ገና ራሳችን ሃገራችንን እንድንሰራ የምንጠበቅ የደሃ አባቶች ልጆች ነን፡፡ ከጥድፊያና ሁካታ በፊት በጣም ብዙ ስራ አለብን፡፡ ሃገርን ድቡሽት ላይ የሚገነባ ነገ መጠለያ ያጣል፡፡
ይመቻችሁ !!
መላኩ ብርሃኑ

ዓለም አቀፉ የዩቲዩብ ኮከብ አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) በአዲስ አበባ፡ የዓድዋ መታሰቢያን በባዶ እግሩ ጎብኝቷል
ታዋቂው አሜሪካዊ የዩቲዩብ ኮከብ እና የቀጥታ ስርጭት አቅራቢ ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር (በቅፅል ስሙ አይሾው ስፒድ) በኢትዮጵያ እያደረገ ባለው ጉብኝት መላውን የኢንተርኔት ዓለም ትኩረት ስቧል።
ወጣቱ ኮከብ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን እየጎበኘ የሚገኝ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ ለሚሊዮን ተከታዮቹ እያስተዋወቀ ይገኛል።
የ21 ዓመቱ አይሾው ስፒድ ወደ አዲስ አበባ ሲደርስ በቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ ጉብኝት "Speed Does Africa" በሚል መጠሪያ በ20 የአፍሪካ ሀገራት እያደረገ ያለው ሰፊ ጉዞ አካል ነው። ስፒድ በኬንያ በነበረው ቆይታ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 300 ሺህ አዲስ ተከታዮችን ማግኘቱ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ላይ የዩቲዩብ ተከታዮቹ ቁጥር 48 ሚሊዮን ደርሷል።
ከጉብኝቱ እጅግ አስገራሚ ትዕይንቶች አንዱ ስፒድ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን በባዶ እግሩ መጎብኘቱ ነው።
ለኢትዮጵያ ታሪክ ያለውን አክብሮት በገለጸበት በዚህ ቆይታው፣ በመታሰቢያው ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ሲመለከት የነበረውን ስሜት በቀጥታ ስርጭት (Live Stream) ለተከታዮቹ አጋርቷል። ስርጭቱን በአንድ ጊዜ ከ 191 ሺህ በላይ ሰዎች ሲከታተሉት ተመልክተናል።
በአትሌቲክስ ስሟ በገነነችው ኢትዮጵያ ከታዋቂ አትሌቶች ጋር ጊዜውን ያሳለፈው ስፒድ፣ "ኢትዮጵያ የፈጣን ሰዎች ሀገር መሆኗን አውቃለሁ" በማለት አድናቆቱን ገልጿል።
በቆይታውም፦
👉የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ ፍቅሩን ገልጿል፤
👉ባህላዊ ልብሶችን በመልበስና እስክስታ በመለማመድ ተሳታፊ ሆኗል፤
👉የኢትዮጵያን ባህላዊ ምግቦች በተለይም 👉👉እንጀራን በመቅመስ ምስክርነቱን ሰጥቷል።
በማህበራዊ ሚዲያ ከ60 ሚሊዮን በላይ አጠቃላይ ተከታዮች ያሉት የዚህ ወጣት ጉብኝት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ትልቅ ዕድል ተደርጎ ተወስዷል። የሀገሪቱን ገጽታ፣ እንግዳ ተቀባይነት እና ዘመናዊ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
አይሾው ስፒድ በቀጣይ ቀናትም ሌሎች ታሪካዊ ቦታዎችንና የቱሪስት መስህቦችን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል።

Sponsored by
Surafel
Comments