2 months ago
የእውቅናና የ"አሸም" መርሀ ግብር
- በከምባታ ዞን በሀሚዶ ቀበሌ
#ethiopia | የሐገራችን ኢትዮጵያ ሕዝብ በባሕሉ የሚሠራን ሰው የሚያበረታታበት የራሱ የሆነ የነበረ ታሪክ ወግና ባህል አለው።
የከምባታ ሕዝብም የዚሁ አካል የሆነውን ጠንካራ የስራና የተግባር ሰውን የሚያበረታታበት የ"አሸም" ስርዓት ይከውናል።
ወጣቱ ሞዴል አርሶ አደር አቶ አብነት ዴላሞ በከምባታ ዞን በአዲሎ ዙሪያ ወረዳ በሀሚዶ ቀበሌ እየሰራ ባለው እጅግ ታሪካዊ እንዲሁም ከፍ ያለ እሴት ጨምሮ ለከወነው የግብርና ስርዓት የዞኑ ተወላጅ የሆኑ ወዳጆቹና የተለያዩ ስራ ወዳድ አካላት በብሔረሰቡ ባህል መሠረት የእውቅናና የ"አሸም" መርሐ ግብር አሰናድተዋል።
💐ግንቦት 30/2018 ዓ.ም በከምባታ ዞን በአዲሎ ዙሪያ ወረዳ በሀሚዶ ቀበሌ!!!💐
➽ሞዴል አርሶ አደር አብነት ዴላሞን ለእውቅና ካበቁት ተግባራት በወፍ በረር የተወሰኑትን እናነሳለን:-
➟አቶ አብነት ዴላሞ በከተማ ከሚኖርበት ኑሮ ወደ ገጠሪቱ የሐገራችን ከፍል በመግባት ግብርናን እጅግ ድንቅ በሆነ መልኩ በማዘመን ለአከባቢው፣ ለዞኑ፣ ለክልሉ አልፎም በሐገር ደረጃ አራዓያ(ሞዴል) ተደርጎ የሚያስቆጥረውን ተግባራት እውን በማድረግ የሚታይና የሚጨበጥ ስራን በመስራቱ
➟የጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር አብይ አህመድ ኢንሼቲቭ አካል የሆኑትን
●የአረንጓዴ አሻራ
●የሌማት ትሩፋት
●የበጋ መስኖ
●እንዲሁም በአከባቢው ኗሪ የሆኑ 400 አርሶ አደሮችን በማደራጀት እጅግ ሰፊ ተግባራትን እየከወነ ይገኛል።
➟ሌላው ሞዴል አርሶ አደሩ አቶ አብነት ዴላሞ በማሳው ቅጥር ግቢ ዘመናዊ የሆነ የግብርና ምርምር ማዕከል ያደራጀ ሲሆን ለዚህም ያመች ዘንድ
●የአርሶ አደር ማሰልጠኛ
●ለልማት ጣቢያ ሠራተኞች ማረፊያ
●ለግብርና ተመራማሪዎች የምርምር ማዕከል
●ለተመራማሪዎች የማደራያና ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሾችን በመገንባት እጅግ አመርቂ ተግባራትን ከውኗል።
➽ሌላው በ2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ4 ዞኖች ያስጀመሩትን የገጠር ኮሪደር አራዓያ በመውሰድ ሞዴል አርሶ አደሩ ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት በአከባቢው የሚገኙ ሀብቶችን በመጠቀም ተግባራዊ አድርጓል።
●ይህም የገጠር ኮሪደር ዲዛይንና አካል የሆነው መኖሪያ ቤት ከነሙሉ ክብሩ በነገው ዕለት የሚመረቅ ይሆናል።
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከዚህ ቀደም ወደ አብነት ዴላሞ ማሳ ለጉብኝት በተገኙበት ወቅት በስፍራው የታየው እጅግ አስገራሚ የግብርና ስርዓት ወደ ሌሎች የሐገራችን ስፍራዎችም እንዲሸጋገር ጥብቅ የአደራ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።
በቀጣይነትም ወጣት አብነት ዴላሞ(ሞዴል አ.አ) በሐገር አቀፍ ደረጃ የአርሶ አደሮች የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ለመግንባት ውጥን ይዞ ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ የፋይናንስ ምንጭ በማፈላለግ ላይ እንደሚገኝ የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ።
ይህንንም ራዕዩን ለማሳካት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቢደግፉት ለግብርናው እድገት የእራሱን አሻራ እንዲያሳርፍና የድርሻውን እንዲወጣ በቂ አቅም እንዳለው በስፍራው ተገኝተው የተመለከቱ ሁሉ የሚመሠክሩት ሀቅ ነው።
በእውቅናና በ"አሸም" መርሀ ግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ክቡር እንግዶችና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የወጣት አብነት ዴላሞ(ሞዴል አ.አ) ወዳጆች፣ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች የሚገኙ ይሆናል!!!!
➽የሚሠሩ እጆች ሁሉ እውቅና ይገባቸዋል!!!
➽አሸም ወጣት አብነት ዴላሞ(ሞዴል አ.አ)!!!
Via Henok Tadesse Sedebo
#ከምባታ #ግብርና #አሸም #እውቅና #የገጠርኮሪደር #ልማት #ሞዴልአርሶአደር #ማዕከላዊኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago
ከበረሃማነት ወደ ምድር ገነት፦
የአርሶ አደር አብነት ዴላሞ አስደናቂ የስኬት ጉዞ!
#ethiopia | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን የሚገኘው ወጣት አርሶ አደር አብነት ዴላሞ፣ ፈተናን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር የግብርናን ትርጉም የቀየረ ብርቱ ወጣት ነው።
በአንድ ወቅት የገነባው ግዙፍ የውሃ ገንዳ ፈርሶ ንብረቱ ቢወድም፣ ተስፋ ሳይቆርጥ ተነስቶ ዛሬ ለሀገር ሞዴል የሚሆን ስራ ሰርቷል።
የአብነት ስኬት ምንጮች፦
ተቀናጀ ግብርና፦ በ10 ሄክታር መሬት ላይ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የቡናና ቅመማ ቅመም ልማትን በማቀናጀት ውጤታማ ሆኗል።
አግሮ-ቱሪዝም (Agro-Tourism)፦
ግቢውን በውብ አበቦችና ዛፎች አስጊጦ፣ ለተመራማሪዎችና ለእንግዶች የሚያገለግሉ ዘመናዊ መኝታ ቤቶችን፣ የስብሰባ አዳራሽና ሎጅ መሰል አገልግሎቶችን በመገንባት የገጠር ኮሪደር ልማትን በተግባር አሳይቷል።
ለ10 ወጣቶች በቋሚነት እንዲሁም እስከ 80 ለሚደርሱ ወጣቶች በጊዜያዊነት የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ከ400 በላይ አርሶ አደሮችን በቴክኖሎጂና በምክር ይደግፋል።
በ50 ሄክታር መሬት ላይ ትልቅ የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደረግበት የተቀናጀ የግብርና ማዕከል ለመገንባት በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በግንቦት 2017 ዓ.ም የአብነትን የስራ ቦታ ጎብኝተው፣ እንዲህ ያሉ ወጣቶች የሀገርን የብልጽግና ጉዞ ዕውን እንደሚያደርጉ መመስከራቸው ይታወሳል።
አዘጋጅ፡- ሰለሞን ደምሰው
ፎቶ፡- ጌታቸው ምትኩ
#getu #abnetdelamo #modelfarmer #agriculture #ethiopia #agriculturaltransformation #ከማምረትበላይ #beyondproduction #agrotourism #ethiopiaagriculture #greenlegacy #successstory #jobcreation #kembata #ethiopia #አርሶአደር #ስኬት #ግብርና #አረንጓዴአሻራ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

11 months ago
ከነብር ጋር ታግለው ልጆቻቸውን ከጥቃት ያተረፉት አባት
#ethiopia | በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከገባው ነብር ጋር ትግል የገጠሙ አባት ሕይወታቸው በተዓምር ተርፏል። እኝህ ጀግና አባት ሙስጠፋ ረሺድ ይባላሉ። ሙስጠፋ ረሺድ የተለመደ የእርሻ ሥራቸውን አከናውነው እቤታቸው ከባለቤታቸው እና ከሁለት አዳጊ ልጆቻቸው ጋር ቁጭ ብለው የእለት ሥራቸውን ያውጋሉ። ይሄ ያልታሰበ እና ምንም ያልጠበቁት ክስተት የገጠማቸው ምሽት 1፡30 ላይ ነው። አባወራው እንደሚሉት ምሽት 1፡30 አካባቢ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ከገባው ነብር ታግለው ልጆቻቸውን እና ባለቤታቸውን ቢያተርፉም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ከጀርመን ድምጽ የአማርኛ ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
ክስተቱ በምስራቅ ሀራርጌ ጉርሱም ወረዳ ጎባ ቀበሌ ባሳለፍ ነው ሳምንት የደረሰ ነው፡፡ ጀግናው ባለታሪክ ሙስጠፋ ረሺድ ይባላሉ በምስራቅ ሀራርጌ ጉርሱም ወረዳ ጎባ ቀበሌ አርሶአደር ናቸው ፡፡ ለቤተሰቦቻቸው ለማዳን ተጋድሎ የፈጸሙት ባለታሪክ ሙስጠፋ እንደ ሁልጊዜውም በሰርክ ተግባራቸው ላይ ውለው ደክመዋቸው ወደ ቤት ስመለሱ ነው በህልማቸውም በእውናቸውም ይገጥመኛል ብለው የማያስቡት ታሪክ የገጠማቸው፡፡ ይሄ ድንገተኛ ታሪክ ሲገጥማቸው የሁለት ታዳጊ ልጆች አባት የሆኑት ሙስጠፋ ከባለቤታቸው ጋር ሆነውየቀን ውሎአቸውን እያወጉ በቤታቸው ውስጥም ነበሩ፡፡ ባለታሪኩ እና እኝህ ጀግና አባት ሙስጠፋ ረሺድ የገጠማቸውን ዱብ እዳ እንደሚከተለው ለሬዲዮው አስረድተዋል።
“ያጋጠመኝ ነገር ያው ፈጣሪ ኑር ካለ ያኖርሃል ነው እንጂ ሕይወትን የሚያስቀጥል ነገር እንኳ አልነበረም፡፡ አስፈሪው የዱር እንስሳ ነብር የሚባለው ነበር ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አከባቢ በግምት ከምሽቱ 1፡30 አከባቢ ከቤተሰቦቼ ጋር ቤት ውስጥ እያለን ነው ድንገት መጥቶ ወደ ቤት ዘልቆ የገባብን፡፡ ምንም ዝግጅት ሳታደርግ፣ ከታዳጊ ልጆችህና ከቤትህ እማወራ ፊት ቁጭ ብለህ እንዲህ ዓይነት ምራቅ የሚያደርቅ ክስተት ቢገጥምህ ምን እንደምታደርግ አስብ፡፡ እቤትህ የገባው ነገር ስታየው የሚስፈራ ቁጡ የዱር እንስሳ ነው ፣ በእጅህ ደግሞ ምንም ነገር የለም ፡፡
በዚያ ላይ በእርሻ ሥራ ስለፋ ነው የዋልኩት፡፡ ክስተቱም የተፈጠረው ልክ እግሮቼን ታጥቤ አረፍ ስል ነው ፡፡ ነብሩ ዘለል አለና ቤት ውስጥ ባለች አልጋ ነገር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ነብር ልጆች ያጠቃል ሲባል ስሰማ ስላደኩ ልጆቼን እንዳያጠቃብኝ ስጋት ገባኝ እና ልጆቼ እና ባለቤቴን እንዳያጠቃብኝ አንድ እርምጃ መውሰድ እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡ በሀገራችን በባህሉ ማድረግ ያለብንን ነገር ሁሉ ማድረግ ያዝን። ነብሩም እንዲወጣም በሀገሬው ባህል ለመነው። ግን እሱ ወይ ፍንክች። ጭራሽ ከማን ልጀምር ብሎ ነው መሰል ልጆቼ ላይ ትኩረት ማድረግ ጀምሯል። ይሄን ግዚ በአቅራቢያዬ ያገኘሁትን ዱላ ነገር አንስቼ ላስወጣው ወስኜ ስነሳ ግን ዘሎ ተከመረብኝ” ሲል አቶ ሙስጠፋ የገጠመውን ፊልም መሰል ክስተት ከነስሜቱ ማስረዳት ቀጠለ፡፡ ነብር ለወትሮ ፍየሎችን ለማደን ወደ ሰው ቤት እንደሚገባ የሚታወቅ ቢሆንም አንድ ፍየል እንኳ በሌለበት በአቶ ሙስጠፋ ቤት ይህ የዱር እንስሳ ለምን ወደ ገጠራማው የሰዎች መኖሪያ ቤት እንደገባም እንግዳ ነገር መሆኑንም ተጎጂው አስረድተዋል፡፡
ዱላ በመነሳቱ የተቆጣው የሚመስለው ነብሩም በሁለት ልጆች አባት ከአቶ ሙስጠፋ ጋር እልህ አስጨራሽ ትግል መግጠም ያዘ አቶ ሙስጠፋም ቤተሰቦቻቸውን ለማዳን የሞት ሽረት ትግላቸውን ተያያዙት ነበሩም በአደን የጠገበ ነበርና በንክሻ እና መቧጨር ጉዳት ማድረሱን ተያያዘ፡፡ “ቤት ውስጥ ፍየል የለም፡፡ እኔና ቤተሰቦቹ ነበርን ቤት ውስጥ ያለ ነው የሚሉት አቶ ሙስጠፋ፡፡ በእርግጥ አከባቢችን ደን አለ፤ ግን ነብር ወደ ሰው ቤት እንዲህ ገብቶ ሰው ላይ በማነጣጠር ጥቃት ስያደርስ እምብዛም የተለመደ ነገር አልነበረም ይላሉ ፡፡ ክስተቱንም ሲያስታውሱ እኔ የሞት ሞቴን ተነስቼ ባልጋፈጠው ግን ልጆቼን ላይ አነጣጥሮባቸው ስለነበር ጉዳት ማድረሱ አይቀርም ነበር ይላ። በትግላቸው ወቅት የነበረውንም ነገር ሲናገሩ፤ ዘሎ እንደወጣብኝም አናቴን በመቧጨር እና በተለይም ግራ እጄን በመንከስ በጣም ነው የጎዳኝ፡፡ አሁን እራሴን ላይ ያለው ጉዳት ተሸሎኛል፤ ግራ እጄን ግን ምንም ማንቀሳቀስ አልቻልኩም፡፡በሕዝቡ እርዳታ ሀኪም ቤት ሄጄ ህክምና ባገኝም አሁንም ውስጡን እያመመኝ ነው” በማለት ጀግና አባ ወራ በዱር እንሰሳው የደረሰበትን ጉዳት ያስረዳል፡፡
ከነብር ጋር የነበረው ትግል እጅግ ፈታኝ እና ከአቅሜ በላይ ነው የሚሉት አቶ ሙስጠፋ፤ ጎረቤቶቻቸው ባይደርሱላቸው ናሮ የእሳቸው እና የመላው ቤተሰቦቹ ሕይወት አደጋ ላይ ወድቀው እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ ነብሩን ለመግጠም ያነሳሁት ዱላ የት በትግላችን ወቅት የት እንደደረሰም ሳላውቅ ነብሩ አናቴ ላይ እንደሰፈረ ብቻ ነው የማስታውሰው የሚሉት ተጎጂው። ጎረቤቶቻቸው እንዴት ደርሰው እንደገላገሏቸውም ሲያስታውሱ እንዲህ ይላሉ:-
“ የእኛን ግብግብ እና ጩህት የሰማው ጎረቤት ያለ የሌለ ነገሩን ይዞ ወደ እኔ መምጣት ጀመረ፤ ሰው እንደደረሰልኝ ያየው አጅሬ ግን ቤቱን ለቆ ከመውጣት ይልቅ ወደ ቤቱ ጣሪያ ዘሎ ወጣ፡፡ አጅሬ በቃ የፈለገው ሰው ላይ ጥቃት ማድረስ ነው የሚመስለው፡፡ በተለይም ሕጻናቱን ፡፡ እነ የያዝኩትን ዱላ የት እንኳ እንደገባ አላስታውስም፡፡ ነብሩን ከላዬ ላይ ለመወርወር ስታገል ግንድ ጋር እንደመታገል ነው የሆነብኝ። አውሬው በጣም ጠንካራ ነው፡፡ ሰዎች ስደርሱልኝ ለቆኝ ወደ ጣሪያ ወጣ፡፡ በር ብንከፍትም አልወጣ አለ፡፡ ከዚያን በኋላ ነው ጣሪያው ላይ እንዳለ በጥይት ገድለውት እፎይ ያልነው” ብለዋል፡፡ ያጋጣሚ ነገር ሆኖ እንጂ እንዲህ ያለ ብዙ ጊዜ በአካባቢያችን አይሰማም የሚሉት መስጠፋ ልጆቻቸውንና ባለቤታቸውን ለማዳን ሲሉ መስዋእትነት ቢከፍሉም በሠሩት ሥራ ግን ደስተኛ መሆናቸውን ያስረዳሉ፡፡ በአቶ ሙስጠፋ ቤት ከገጠመው ክስተት ወዲህ ማህበረሰቡ ላይ በተፈጠረው የስጋት ከመሸ ሁሉም ሰው በሩን በመዝጋት እንደሚቀመጥም አቶ ሙስጠፋ አስረድተዋል፡፡ ድርጊቱ በወረዳው መግጠሙን ያረጋገጠው የጉርሱም ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን የጥንቃቄ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡ እንደ ወረዳው ኮሚኒኬሽን ገለጻ፤ በቅርቡም ከአንድ ወር ግድም በፊት በዚሁ ተመሳሳይ ዞን ሸነን ዱጎ ወረዳ ነብር በእኩለ ሌሊት በእንቅልፍ ላይ ባሉ አንድ ቤተሰብ አባላት ላይ ባደረሰው ጥቃት የአንድ ታዳጊ ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት ማድረሱ አስረድቷል፡፡

1 year ago
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተከሰተ ድርቅ 32 ሺህ ሰዎች በምግብ እጥረት ሲጎዱ ከ1200 በላይ እንስሳት ሞቱ፤ በ ደቡብ ጎንደርም ከ175ሺህ በላይ ሰዎች ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል!
በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ በሚገኙ ስድስት ቀበሌዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተ ድርቅ 32 ሺህ ሰዎች በምግብ እጥረት ሲጎዱ፤ ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ እንስሳት መሞታቸውን የዞኑ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ከፍያለው ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
የዝናብ እጥረቱ በምዕራብ በለሳ ወረዳ ከሚገኙ 32 ቀበሌዎች ቆላማ በሆኑ አከባቢዎች መከሰቱን የገለጹት አቶ ዋሲሁን ችግሩ በይበልጥ በስድስት ቀበሌዎች ማለትም በሳሚ፣ ላቫ ማርያም፣ አሳውጋሪ፣ ጃንዳብ፣ ላየ እና ሴራ በተባሉ ቀበሌዎች አስከፊ መሆኑን ተናግረዋል።
ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ቆይታ ያደረጉ በምዕራብ በለሳ ወረዳ አርባያ ከተማ ዙርያ አርሶአደር፤ “መንግስት በሁለት ወር የሚሰጠን ማሽላ አለች በሷ ነው እንግዲህ እንዳይሞትም እንዳይዳንም ሆነን የምንኖረው። የሚለበስ የለም ራቁት ነው። ዞሮ ዞሮ ግን መቼም መኖር ከተባለ እስኪሞቱ ድረስ የበላም ኑሮ ነው ያልበላም ኑሮ ነው" ሲሉ በአከባቢው ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ በክልሉ ደቡብ ጎንደር ዞን 7 ወረዳዎች በሚገኙ 57 ቀበሌዎች 175ሺህ በላይ ወገኖች ለድርቅ መጋለጣቸውን የደቡብ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
Seledadotio

Sponsored by
Surafel
Comments