የእውቅናና የ"አሸም" መርሀ ግብር
- በከምባታ ዞን በሀሚዶ ቀበሌ
#ethiopia | የሐገራችን ኢትዮጵያ ሕዝብ በባሕሉ የሚሠራን ሰው የሚያበረታታበት የራሱ የሆነ የነበረ ታሪክ ወግና ባህል አለው።
የከምባታ ሕዝብም የዚሁ አካል የሆነውን ጠንካራ የስራና የተግባር ሰውን የሚያበረታታበት የ"አሸም" ስርዓት ይከውናል።
ወጣቱ ሞዴል አርሶ አደር አቶ አብነት ዴላሞ በከምባታ ዞን በአዲሎ ዙሪያ ወረዳ በሀሚዶ ቀበሌ እየሰራ ባለው እጅግ ታሪካዊ እንዲሁም ከፍ ያለ እሴት ጨምሮ ለከወነው የግብርና ስርዓት የዞኑ ተወላጅ የሆኑ ወዳጆቹና የተለያዩ ስራ ወዳድ አካላት በብሔረሰቡ ባህል መሠረት የእውቅናና የ"አሸም" መርሐ ግብር አሰናድተዋል።
💐ግንቦት 30/2018 ዓ.ም በከምባታ ዞን በአዲሎ ዙሪያ ወረዳ በሀሚዶ ቀበሌ!!!💐
➽ሞዴል አርሶ አደር አብነት ዴላሞን ለእውቅና ካበቁት ተግባራት በወፍ በረር የተወሰኑትን እናነሳለን:-
➟አቶ አብነት ዴላሞ በከተማ ከሚኖርበት ኑሮ ወደ ገጠሪቱ የሐገራችን ከፍል በመግባት ግብርናን እጅግ ድንቅ በሆነ መልኩ በማዘመን ለአከባቢው፣ ለዞኑ፣ ለክልሉ አልፎም በሐገር ደረጃ አራዓያ(ሞዴል) ተደርጎ የሚያስቆጥረውን ተግባራት እውን በማድረግ የሚታይና የሚጨበጥ ስራን በመስራቱ
➟የጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር አብይ አህመድ ኢንሼቲቭ አካል የሆኑትን
●የአረንጓዴ አሻራ
●የሌማት ትሩፋት
●የበጋ መስኖ
●እንዲሁም በአከባቢው ኗሪ የሆኑ 400 አርሶ አደሮችን በማደራጀት እጅግ ሰፊ ተግባራትን እየከወነ ይገኛል።
➟ሌላው ሞዴል አርሶ አደሩ አቶ አብነት ዴላሞ በማሳው ቅጥር ግቢ ዘመናዊ የሆነ የግብርና ምርምር ማዕከል ያደራጀ ሲሆን ለዚህም ያመች ዘንድ
●የአርሶ አደር ማሰልጠኛ
●ለልማት ጣቢያ ሠራተኞች ማረፊያ
●ለግብርና ተመራማሪዎች የምርምር ማዕከል
●ለተመራማሪዎች የማደራያና ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሾችን በመገንባት እጅግ አመርቂ ተግባራትን ከውኗል።
➽ሌላው በ2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ4 ዞኖች ያስጀመሩትን የገጠር ኮሪደር አራዓያ በመውሰድ ሞዴል አርሶ አደሩ ደረጃውን የጠበቀ መኖሪያ ቤት በአከባቢው የሚገኙ ሀብቶችን በመጠቀም ተግባራዊ አድርጓል።
●ይህም የገጠር ኮሪደር ዲዛይንና አካል የሆነው መኖሪያ ቤት ከነሙሉ ክብሩ በነገው ዕለት የሚመረቅ ይሆናል።
የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከዚህ ቀደም ወደ አብነት ዴላሞ ማሳ ለጉብኝት በተገኙበት ወቅት በስፍራው የታየው እጅግ አስገራሚ የግብርና ስርዓት ወደ ሌሎች የሐገራችን ስፍራዎችም እንዲሸጋገር ጥብቅ የአደራ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።
በቀጣይነትም ወጣት አብነት ዴላሞ(ሞዴል አ.አ) በሐገር አቀፍ ደረጃ የአርሶ አደሮች የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ለመግንባት ውጥን ይዞ ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ የፋይናንስ ምንጭ በማፈላለግ ላይ እንደሚገኝ የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ።
ይህንንም ራዕዩን ለማሳካት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ቢደግፉት ለግብርናው እድገት የእራሱን አሻራ እንዲያሳርፍና የድርሻውን እንዲወጣ በቂ አቅም እንዳለው በስፍራው ተገኝተው የተመለከቱ ሁሉ የሚመሠክሩት ሀቅ ነው።
በእውቅናና በ"አሸም" መርሀ ግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ክቡር እንግዶችና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የወጣት አብነት ዴላሞ(ሞዴል አ.አ) ወዳጆች፣ ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች የሚገኙ ይሆናል!!!!
➽የሚሠሩ እጆች ሁሉ እውቅና ይገባቸዋል!!!
➽አሸም ወጣት አብነት ዴላሞ(ሞዴል አ.አ)!!!
Via Henok Tadesse Sedebo
#ከምባታ #ግብርና #አሸም #እውቅና #የገጠርኮሪደር #ልማት #ሞዴልአርሶአደር #ማዕከላዊኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago