7 days ago
ኬንያ እና ኢትዮጵያ እየተማማሩ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ደረጀ ድጉማ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከኬንያ የሕዝብ ጤና እና ሙያዊ ደረጃዎች መምሪያ ዋና ጸሐፊ ሜሪ ሙቶኒ ጋር የምክክር ስብሰባ አካሄዱ።
የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ ኬንያ የእናቶችና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል በሰው ሰራሽ አስተዋጽኦ (AI) የታገዘ አልትራሳውንድ ቴክኖሎጂን (AI-POCUS) በመተግበር ረገድ ያካበተችውን ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ማጋራት ነው።
በስብሰባው ወቅት ኬንያ በዲጂታል ጤና ፈጠራ፣ በመልካም አስተዳደር እና የኤአይ አልትራሳውንድ አገልግሎትን በማስፋፋት ረገድ ያስመዘገበችው እድገት የቀረበ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ በመዘርጋት የእናቶችና ሕፃናትን ሕክምና ለማጠናከር ለምናደርገው ዝግጅት ትልቅ ጥቆማ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
ይህ ውይይት ኢትዮጵያና ኬንያ በዲጂታል ጤና መፍትሔዎች፣ በእውቀት ሽግግር እና በቀጣናው ጠንካራ የጤና ስርዓት በመገንባት የእናቶችና ሕፃናትን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ያላቸውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም ያረጋገጡበት ሆኖ አልፏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

20 days ago
ቻይና የመጀመሪያውን የጭንቅላት ቺፕ ገበያ ላይ አዋለች
ቻይና በዓለም መጀመሪያ የሆነውን ለንግድ የቀረበ የጭንቅላት ቺፕ ንቅለ-ተከላ በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ አዲስ ታሪክ ሰርታለች።
“NEO” የተሰኘው ይህ ቺፕ በሻንጋይ ሁዋሻን ሆስፒታል በአደጋ ምክንያት እጁ ሽባ በሆነ ታካሚ ላይ ተገጥሟል።
ይህ ቴክኖሎጂ የአሜሪካው ቢሊየነር ኤሎን ማስክ ኩባንያ ከሆነው “ኒውራሊንክ” ቀድሞ የንግድ ፈቃድ በማግኘት በሆስፒታሎች ውስጥ ጥቅም ላይ መዋል መጀመሩ ትልቅ ስኬት ሆኗል።
ኒውራክል ሜዲካል ቴክኖሎጂ በተባለ የሀገር ውስጥ ኩባንያ የተሰራው ይህ መሣሪያ፣ ከሌሎች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች በተለየ የሰውን የአንጎል ህዋስ ሳይጎዳ ከውጪው ክፍል ላይ በመጣበቅ የአንጎል መልዕክቶችን ወደ እጅ እንቅስቃሴ የመቀየር አቅም አለው።
የቻይና መንግሥት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማነቃቃትና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ዓለምን ለመምራት በፈረንጆቹ 2030 ላይ ሁለት ወይም ሦስት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የቢሲአይ ኩባንያዎችን ለመፍጠር አቅዶ እየሠራ ይገኛል።
ይህ ቴክኖሎጂ ወደፊት ሽባ ለሆኑ እና ለተለያዩ የአንጎል ሕመምተኞች ትልቅ ተስፋ ሆኗል።
Seledadotio

1 month ago
ቴክኖ ኢትዮጵያ የሀገሪቱን ቱሪዝም በሞባይል ፎቶግራፍ ለማስተዋወቅ የ10 ቀናት የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ከፈተ
#fastmereja I ቴክኖ ኢትዮጵያ የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህቦች በሞባይል ፎቶግራፍ ጥበብ ለማስተዋወቅ ያለመ የ10 ቀናት የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን እና የማስተዋወቂያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል። ኩባንያው ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ ኤግዚቢሽን፣ የሀገሪቱን የተፈጥሮ ውበት፣ ታሪካዊ ቅርሶች እና ባህላዊ እሴቶች የሚያሳዩ ከ100 በላይ በሞባይል ስልክ የተነሱ ድንቅ ፎቶግራፎችን ለዕይታ አብቅቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነው የዚሁ ኤግዚቢሽን የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ቴክኖ ኢትዮጵያ ይህንን ዝግጅት ያዘጋጀው ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ ከቦርድ ሴልፎን አዲስ አበባ እንዲሁም ከህፃናትና ወጣቶች ቲያትርና ሲኒማ አዳራሽ ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ የቀረቡት ምስሎች በሙሉ በኩባንያው የቅርብ ጊዜ ምርት በሆነው "TECNO CAMON 50 Pro" ስማርት ስልክ ብቻ የተነሱ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም የሞባይል ስልኩን የፎቶግራፍ ጥራትና የቴክኖሎጂ ደረጃ ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተመልክቷል። ስልኩ 50 ሜጋ ፒክስል (50MP) የካሜራ ሲስተም እና AI ቴክኖሎጂዎችን ያካተተ እንደሆነም ተጠቁሟል።
የዚህ መርሃ ግብር ዋነኛ አካል የሆነው በቴክኖ ኢትዮጵያ፣ በአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ በቪዚት አዲስ አበባ እና በህፃናትና ወጣቶች ቲያትርና ሲኒማ መካከል በጋራ ለመስራት ተስማምቷል። ይህ ስምምነት የቴክኖሎጂ፣ የፎቶግራፍ እና የፈጠራ ስራዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች በአገር ውስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ በጋራ ለማስተዋወቅ ያለመ እንደሆነ ስምምነቱን የፈረሙት አካላት አስታውቀዋል። #ሳይ_ቴክ

'Trust' እና 'Google TV' የተባሉ መተግበሪያዎች የባንክ አካውንትን ለአደጋ እያጋለጡ ነው
#fastmereja I በኢንተርኔት ማስፈንጠሪያዎች (links) አማካይነት ወደ ስልኮች በመግባት የባንክ ሂሳብን የሚያጠፉ "Trust"፣ "Google TV" እና "Known" የተባሉ አደገኛ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።
እነዚህ መተግበሪያዎች በተለይ በGoogle Chrome፣ Telegram እና WhatsApp መድረኮች ላይ የሚጋሩ ሲሆን፥ ተጠቃሚዎች ሳያውቁ የገንዘብ ዝውውር በመፈጸም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ።
ይህ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሳይበር ጥቃት በስፋት እየተስተዋለ የመጣው ተጠቃሚዎች ከተላኩላቸው አጠራጣሪ ሊንኮች ላይ መተግበሪያዎቹን ሲያወርዱ መሆኑ ታውቋል። መተግበሪያዎቹ አንዴ ስልክ ላይ ከተጫኑ በኋላ ከሞባይል ባንኪንግ ጋር የተያያዙ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በመስረቅ ገንዘብ የመውሰድ አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።
ህብረተሰቡ ከዚህ መሰሉ የሳይበር ዘረፋ ራሱን ለመጠበቅ መተግበሪያዎችን ከታመኑ ምንጮች (እንደ Play Store ወይም App Store) ብቻ ማውረድ እንዳለበት ባንኩ አሳስቧል።
ከተጠቀሱት የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመክፈት እና በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ላይ የባዮሜትሪክ (የፊት ወይም የአሻራ) እና የፒን (PIN) የደኅንነት ማረጋገጫዎችን አጣምሮ መጠቀም ለአደጋው የመጋለጥ እድልን በእጅጉ እንደሚቀንስ ተነግሯል።
#ሳይ_ቴክ

2 months ago
የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ፍጹም ፍትሃዊ እና ከስህተት የጸዱ ለማድረግ፣ ሙሉ በሙሉ በባትሪ ኃይል የሚሰራ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ኳስ ጥቅም ላይ ሊውል መሆኑ ተመልክቷል።
ዘንድሮ ውድድሩን በጋራ የሚያስተናግዱት አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ከመላው ዓለም የሚመጡ ስፖርተኛችንና የእግር ኳስ አፍቃሪያንን ለመቀበል የመጨረሻ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ ይገኛሉ።
ይህ የዓለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስት ሀገራት በአንድ ጊዜ የሚስተናገድ ከመሆኑም በላይ በስፖርቱ ዓለም አዲስ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ የሚከፍትበት ሆኗል።
ከ1970 ጀምሮ ለዓለም ዋንጫ ኳሶችን እያመረተ የሚገኘው አዲዳስ ኩባንያ፣ ዳኞችን በከፍተኛ ሁኔታ ለመርዳት የሚያስችል “ኮኔክቲድ ቦል ቴክኖሎጂ” (Connected Ball Technology) የተገጠመለትንና ትሪዮንዳ የተሰኘውን አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ኳስ ይፋ አድርጓል።
የአዲዳስ ቃል አቀባይ እንደገለጹትብበኳሱ ውስጥ የተገጠመው መመርመሪያ (Sensor) ያለ ባትሪ ኃይል መስራት ስለማይችል ኳሱ ከእያንዳንዱ ጨዋታ በፊት የግድ ቻርጅ መደረግ ይኖርበታል።
ኳሱ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ሙሉ ጨዋታውንና ከዚያ በላይ በብቃት ማገልገል እንዲችል በጨዋታው ዕለት በስታዲየሙ ውስጥ በተዘጋጀ ልዩ የኃይል መሙያ መደርደሪያ (Cradle) ላይ ቻርጅ ይደረጋል።
ለዚህም በኢንደክሽን አማካኝነት በገመድ አልባ ሥርዓት ቻርጅ የሚደረግ ከፍተኛ ጥራት ያለው ባትሪ ጥቅም ላይ ውሏል።
ይህ ባትሪ ሙሉ በሙሉ ለመሙላት 90 ደቂቃ አካባቢ የሚፈጅ ሲሆንንበጨዋታ ላይ እያለ እስከ 6 ሰዓታት የማገልገል አቅም አለው።
ይህም የአንድን ከፍተኛ የደረጃ ጨዋታ ክፍለ-ጊዜ እጥፍ መቆየት የሚችል ያደርገዋል። በተጨማሪም ኳሱ ከሜዳ ውጭ በሚሆንበት ጊዜ ራሱን ወደ እረፍት ሁነታ (Hibernation mode) በመቀየር ባትሪው ሳይባክን ለቀናት እንዲቆይ ያደርጋል።
በኳሱ ውስጥ በልዩ የመደገፊያ ስርዓት (Suspension system) ተይዞ የተገጠመ 500Hz inertial measurement unit (IMU) የተሰኘ የቪዲዮ ረዳት ዳኝነት (VAR) መረጃዎችን የሚልክ ስስ የኮምፒውተር ቺፕ ይገኛል።
ይህ ሴንሰር እያንዳንዱን የኳስ ንክኪ በከፍተኛ ፍጥነት የሚከታተል ሲሆን የሚከተሉትን ውሳኔዎች በሜዳ ላይ በሴኮንዶች ውስጥ ለመወሰን ይረዳል፦
* ከጨዋታ ውጪ (Off-side) የሆኑ አቋቋሞችን በትክክል መለየት፣
* ኳስ በእጅ መነካቱን (Handballs) ማረጋገጥ፣
* እና ሌሎች አወዛጋቢ ሁነቶችን በቪዲዮ ረዳት ዳኝነቱ (VAR) አማካኝነት በፍጥነት መፍታት።
አዲዳስ እና የቴክኖሎጂ አጋሩ ኪኔክሶን (Kinexon) እንዳስታወቁት፣ ይህ ቴክኖሎጂ ቀደም ሲል በሁለት የፊፋ ውድድሮች እንዲሁም በዩሮ 2024 እና 2025 ላይ የተሞከረ ሲሆን፣ በጨዋታ መሃል ባትሪ አልቆበት የተቀየረ አንድም ኳስ አጋጥሞ አያውቅም።
ባለፈው የ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ ላይም ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ውሎ የነበረ ቢሆንም፣ የዘንድሮው የ2026ቱ ኳስ ግን የሴንሰር አቀማመጥ ለውጥ ተደርጎበታል። በቀደመው ኳስ ሴንሰሩ የተቀመጠው በኳሱ መሃል ላይ ሲሆን፣ በዘንድሮው ስሪት ግን ሴንሰሩ የተገጠመው በኳሱ የጎንዮሽ አካል (Side) ላይ ተቀብሮ ነው።
ኳሱ ከቴክኖሎጂው ባሻገር፣ ሶስቱን አስተናጋጅ ሀገራት ለማክበርና ለመወከል ሲባል በደማቅ ቀይ፣ አረንጓዴ እና ሰማያዊ ቀለማት የተሸለመ ሲሆን፤ የካናዳው የሜፕል ቅጠል (Maple leaf)፣ የሜክሲኮው ንስር (Eagle) እና የአሜሪካው ኮከብ (Star) ምልክቶች በሥነ-ጥበባዊ መልኩ ተካተውበታል።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
ሜታ የቲክቶክ እና የዩቲዩብ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ወደ ፌስቡክ ለመሳብ ወርሃዊ ክፍያ አቀረበ
ሜታ የታወቁ የቪዲዮ ፈጣሪዎችን ከሌሎች ተቀናቃኝ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ወደ ፌስቡክ ለማምጣት "Creator Fast Track" የተሰኘ አዲስ መርሃ-ግብር ይፋ አድርጓል። ኩባንያው ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የነበሯቸውን ቪዲዮዎች በፌስቡክ ላይ መልሰው እንዲለጥፉ በማድረግ ብቻ ወርሃዊ የገንዘብ ክፍያ እንደሚፈጽም አስታውቋል።
የክፍያ ዝርዝር
የተመረጡ ፈጣሪዎች እንደ ተከታዮቻቸው ብዛት የሚከተለው ክፍያ ይቀርብላቸዋል፡
📌 100,000 ተከታዮች ያሏቸው፦ በወር $1,000።
📌 ከ1 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሏቸው፦ በወር $3,000።
📌 ከገንዘቡ ባሻገር፣ ፌስቡክ ለቪዲዮዎቹ ሰፊ ተደራሽነት (Boost) እንዲያገኙ ያደርጋል።
ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
ፕሮግራሙ በአሁኑ ወቅት ጥብቅ መስፈርቶችን ያስቀመጠ ሲሆን፣ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡
📍በአሜሪካ ወይም በካናዳ የሚኖሩ እና ዕድሜያቸው 18 ዓመት የሞላቸው።
📍በኢንስታግራም፣ ቲክቶክ ወይም ዩቲዩብ ቢያንስ 20,000 ተከታዮች ሊኖራቸው ይገባል።
📍 ቢያንስ ለ30 ቀናት የቆየ የፌስቡክ ገጽ ያላቸው እና ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ምንም ዓይነት "Reels" ያልለቀቁ።
📍 ባለፉት 60 ቀናት ውስጥ ቢያንስ 30,000 የቪዲዮ እይታ ያላቸው።
ይህ እርምጃ ሜታ በ2025 ለፈጣሪዎች የከፈለውን የክፍያ መጠን 3 ቢሊዮን ዶላር በማድረስ የ35 በመቶ ጭማሪ ካሳየ በኋላ የመጣ ነው። ሜታ በተለይ ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ ካለበት የፖለቲካ ጫና እና የሕግ እገዳ ስጋት ጋር ተያይዞ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አማራጭ እንዲፈልጉ እያበረታታ ይገኛል።
via_ሳይ_ቴክ
seledadotio

#fastmereja I ሜታ የታወቁ የቪዲዮ ፈጣሪዎችን ከሌሎች ተቀናቃኝ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ወደ ፌስቡክ ለማምጣት "Creator Fast Track" የተሰኘ አዲስ መርሃ-ግብር ይፋ አድርጓል። ኩባንያው ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የነበሯቸውን ቪዲዮዎች በፌስቡክ ላይ መልሰው እንዲለጥፉ በማድረግ ብቻ ወርሃዊ የገንዘብ ክፍያ እንደሚፈጽም አስታውቋል።

ላኪፔይ በAI የታገዘና በድምፅ የሚሰራውን መተግበሪያ በይፋ አስመረቀ
#fastmereja | የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ወደ አዲስ ከፍታ ያሸጋግራል የተባለለት ላኪፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) የተጠቀመ አዲስ መተግበሪያውን ዛሬ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በይፋ አስመርቋል። ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በዚህ የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ፣ ተቋሙ "ራስ" የተሰኘውንና በድምፅ ትዕዛዝ የሚሰራ የAI ረዳት ማስተዋወቁ የዕለቱ ደማቅ ክስተት ሆኗል።
የላኪፔይ አዲሱ መተግበሪያ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ታሪክ ፈርቀዳጅ የተባለለትን አገልግሎት ይዞ ቀርቧል። ደንበኞች በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች በድምፃቸው ብቻ በማዘዝ የተለያዩ የክፍያና የባንክ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ። ይህ አሰራር በተለይ መተግበሪያዎችን ለመጫን ለሚቸገሩ ወይም ማንበብና መጻፍ ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ አካታችነትን የሚያረጋግጥ ነው።
በዚሁ መተግበሪያ አጠቃቀም ላይ የኦሮሚያ ባንክ ቀዳሚ ስትራቴጂካዊ አጋር በመሆን እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ላኪፔይ "ላንዲ ግሎባል" ከተሰኘ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋም ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል። ይህም ደንበኞች በቪዛ (Visa) እና በማስተርካርድ (MasterCard) አማካኝነት ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን በቅልጥፍና እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል።
መተግበሪያው ከገንዘብ ዝውውር ባለፈ የሚከተሉትን አዳዲስ አገልግሎቶች አካትቷል፦ የህንጻ አስተዳደር እና የአከራይ ተከራይ ማገናኛ ማህደር። የንግድ ተቋማት ከደንበኞቻቸው ጋር በቪዲዮ ተገናኝተው የገበያ ተደራሽነታቸውን የሚያሰፉበት ነፃ የቪዲዮ ግንኙነት አገልግሎት።
ላኪፔይ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ አ.ማ በየካቲት ወር 2025 (እ.ኤ.አ) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሥርዓት አከናዋኝ ፈቃድ ማግኘቱ ይታወሳል። ተቋሙ አሁን ላይ ይዞት የቀረበው የAI ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ይበልጥ እንደሚያቀጣጥለው ይጠበቃል።
#ቢዝነስ #ሳይ_ቴክ

አዋሽ ባንክ ሦስት አዳዲስ የዲጂታል መተግበሪያዎችን ስራ አስጀመረ
#fastmereja I አዋሽ ባንክ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማዘመንና ተደራሽነቱን ለማስፋት የነደፋቸውን ሦስት አዳዲስ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ዛሬ መጋቢት 03 ቀን 2018 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በይፋ ስራ ማስጀመሩን አስታወቀ።
ባንኩ ስራ ያስጀመራቸው ሦስቱ መተግበሪያዎች አዋሽ ረሚት (Awash Remit)፣ አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ (Awash E-Ticketing) እና አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት (Awash E-Property Management) የተሰኙ ናቸው።
አዋሽ ረሚት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በቀጥታ፣ በፍጥነትና በደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ገንዘብ እንዲልኩ የሚያስችል ነው። ደንበኞች በቪዛ (Visa) ወይም በማስተር ካርድ (MasterCard) በመጠቀም በቀጥታ ወደ አዋሽ ባንክ ሂሳብ ወይም ወደ አዋሽ ብር ፕሮ (Awash Birr Pro) ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
አዋሽ ኢ-ቲኬቲንግ ኮንሰርቶችን፣ ስፖርታዊ ኩነቶችንና የተለያዩ ስብሰባዎችን የሚያዘጋጁ አካላት ቲኬቶችን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን እንዲሸጡና እንዲያስተዳድሩ ያስችላል። መተግበሪያው የወረቀት ቲኬቶችን በዲጂታል ኮድ (QR Code) የሚተካ በመሆኑ ለአዘጋጆችም ሆነ ለታዳሚዎች ከፍተኛ ምቾት ይሰጣል።
አዋሽ ኢ-ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት የህንፃ ባለቤቶችና ተከራዮች የኪራይ ውልን፣ የክፍያ ሁኔታንና የፋይናንስ ክትትልን በዲጂታል መንገድ እንዲያከናውኑ የተዘጋጀ ነው። መተግበሪያው የመኖሪያ ቤቶችን፣ የንግድ ቦታዎችንና የመኪና ማቆሚያዎችን በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር ይረዳል።
አዋሽ ባንክ በመግለጫው እንዳመለከተው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከሐምሌ እስከ ታኅሣሥ 2025 ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በባንኩ የዲጂታል የክፍያ ሥርዓት የተከናወነው የገንዘብ ዝውውር መጠን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገልጿል።
ባንኩ በቀጣይም የደንበኞቹን እርካታ ለማሳደግ ተጨማሪ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ለማልማት እየሰራ መሆኑን ገልጾ፣ ህብረተሰቡ እነዚህን አዳዲስ አገልግሎቶች እንዲጠቀም ጥሪ አቅርቧል።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የF35 RC ጀት በረራ ተሳካ
#fastmereja I ወጣቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያ ኢብራሂም አሊ (Ibrahim Ali)፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውን የF35 RC የጀት ሞዴል በተሳካ ሁኔታ ማብረር መቻሉን አስታወቀ።
ወጣቱ የፈጠራ ሰው ይህ ውጤት የተመዘገበው ተከታታይ ጥረትና ትግል ከተደረገ በኋላ መሆኑን ገልጾ፤ "ይህ የጀት ፕሮጀክት ከ8 ሙከራዎች በኋላ በ9ኛው በተሳካ ሁኔታ ከመሬት ተነስቶ በረረ" ሲል የጉዞውን ፈታኝነት አስረድቷል።
ከትንሽ ጅማሮ ወደ ትልቅ የአየር ቴክኖሎጂ ኃይል
ኢብራሂም አሊ ለስራው መነሻ ያደረገው የቱርክን የድሮን ቴክኖሎጂ አብዮት የመራውን የሰልቹክ ባይራክታር (Selçuk Bayraktar) ታሪክ መሆኑን ገልጿል። ባይራክታር እ.ኤ.አ. በ2005 በትንሽ የድሮን ፕሮቶታይፕ ጀምሮ ዛሬ ቱርክን በዘርፉ የዓለም ኃያል እንዳደረጋት ሁሉ፣ የእሱም ራዕይ ኢትዮጵያን በአየር ቴክኖሎጂ ጠንካራ ኃይል ማድረግ እንደሆነ ገልጿል።
"ዛሬ በትንንሽ የሪሞት ኮንትሮል ጀቶች እንጀምራለን፤ ነገ ግን የኢትዮጵያን አየር ኃይልና አቪዬሽን ቴክኖሎጂ ለማጠናከር የሚረዳ ትልቅ ተቋም እንገነባለን" ሲል የወደፊት ተስፋውን አጋርቷል።

"ዘማይ ጉዞ" በ1,680 የኤሌክትሪክ መኪኖች የሜትር ታክሲ አገልግሎት ስራ ሊጀምር ነው።
#fastmereja I ዘማይ ኢምፖርት ኤክስፖርት በኢትዮጵያ አዲስ የሆነውንና በራሱ መኪኖችና አሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚሰጠውን "ዘማይ ጉዞ" የተሰኘ የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር ዛሬ የካቲት 25/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ማዶ ሆቴል በሰጠው መግለጫ በይፋ አስተዋውቋል።
በአሁኑ ወቅት 1,680 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለሥራ ዝግጁ ማድረጉን የዘማይ ጉዞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ የትናየት ሺበሺ ገልጸዋል።
አገልግሎቱ እንደ ደንበኛው ምርጫ ኢኮኖሚ፣ ቪአይፒ እና ዲፕሎማት ተብለው በሦስት ደረጃዎች ተከፍለዋል። የመነሻ ዋጋ 100 ብር ሲሆን፣ በኪሎሜትር ደግሞ 12 ብር ሆኖ ተቆርጧል። ይህም ለተጠቃሚው እጅግ አዋጭ ያደርገዋል ተብሏል።
ዘማይ ጉዞ የራሱ የሆነ የገመድ አልባ (Wireless) የቻርጅ ስቴሽን፣ ዘመናዊ ጋራዥ እና ስቲም መኪና ማጠቢያ አገልግሎቶችን አሟልቶ ይገኛል።
ዘማይ ጉዞ ለበርካታ ዜጎች አዲስ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። "ዘማይ" የሚለው ቃል በራያ አካባቢ "አማች" ማለት እንደሆነ ተገልጿል።
ዘማይ ጉዞ በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ ተነግሯል።
#ሳይ_ቴክ #ቢዝነስ

6 months ago
ኢትዮ ቴሌኮም የሀገሪቱን የሚዲያ ስነ-ምህዳር የሚቀይር የ“ቴሌስትሪም” አገልግሎትን ይፋ አደረገ
📅 የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 አዲስ አበባ
ኢትዮ ቴሌኮም የሀገሪቱን የሚዲያ ስነ-ምህዳር በእጅጉ የሚያዘምን የ“ቴሌስትሪም” (teleStream) የይዘት ስትሪሚንግ አገልግሎት እና የመደበኛ ብሮድባንድ አገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀላጥፍ የዲጂታል አሰራር በይፋ ማስጀመሩን አስታወቀ።
ኩባንያው ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ይፋ እንዳደረገው፣ ይህ አዲስ አገልግሎት የኩባንያውን “የቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂን እውን ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራት አካል መሆኑን ገልጿል።
የ“ቴሌስትሪም” ተጠቃሚዎች ያለ ሳተላይት ዲሽ ጥገኝነት ጥራት ያላቸው የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ይዘቶችን በቤታቸው ባለው የብሮድባንድ ኢንተርኔት ዋይ ፋይ በቀላሉ እንዲመለከቱ ያስችላል። በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ ከ60 በላይ የቀጥታ ስርጭት ቻናሎችን እና ከ350 በላይ በፍላጎት የሚታዩ ቪዲዮዎችን ይዟል።
አገልግሎቱ ለግለሰቦች እስከ 4K የሚደርስ ጥራት ያለው የምስል ስርጭት የሚያቀርብ ሲሆን፣ ለሚዲያ ተቋማት ደግሞ ለሳተላይት ኪራይ የሚከፍሉትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት ስርጭታቸውን በሀገር ውስጥ መሰረተ-ልማት ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ እንዲያከናውኑ ይረዳቸዋል። በተጨማሪም ይዘቶችን በሀገር ውስጥ በቴሌ ክላውድ በማስተናገድ የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ከ“ቴሌስትሪም” በተጨማሪ ኩባንያው የመደበኛ ኢንተርኔት አገልግሎት አሰጣጥን “ንክኪ-አልባ” የሚያደርግ አዲስ የዲጂታል ሲስተም (Operation Support System) ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም ደንበኞች ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መሄድ ሳይጠበቅባቸው በቴሌብር ሱፐርአፕ አማካኝነት አዲስ የዋይፋይ ጥያቄዎችንና የብልሽት ምዝገባን ማከናወን ይችላሉ። ለአገልግሎቱም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (Fayda) እና የቴሌብር አካውንት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
ኩባንያው አያይዞም ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት አገልግሎት በቀጥታ ደንበኛው እስከሚፈልግበት ክፍል ድረስ ለማቅረብ የሚያስችለውን የ“ፋይበር ቱ ዘሩም” (FTTR) አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል። ይህም እንደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ስማርት ሆም ላሉ የላቁ የዲጂታል አገልግሎቶች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።
#fastmereja | #ሳይ_ቴክ

8 months ago
የሰው ልጅን አስተሳሰብ ወደ ተግባር የሚቀይረው ረቂቅ ቺፕ ይፋ ተደረገ
በሳይንሱ ዓለም ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረውና ቢአይኤስሲ (BISC) ተብሎ የሚጠራው አዲስ የአእምሮ ውስጥ ቺፕ በታህሳስ 2025 በይፋ ለዓለም ቀርቧል። ይህ ቴክኖሎጂ ከሰው ፀጉር በበለጠ የሚቀጥን ሲሆን ያለምንም የሚታይ ገመድ ወይም የውጭ መሣሪያ የሰውን ልጅ የውስጥ ሃሳብ በቀጥታ ወደ ተግባር የመተርጎም ልዩ አቅም አለው።
በኔቸር ኤሌክትሮኒክስ (Nature Electronics) ላይ የወጣው ይሄው ጥናት እንደሚያመለክተው መሣሪያው በአእምሮ እና በኮምፒውተር መካከል ያለውን ግንኙነት እጅግ ፈጣንና ስውር በሆነ መንገድ ያከናውናል።
ቺፑ በአእምሮ ውስጥ የሚፈጠሩ የኤሌክትሪክ ምልክቶችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ወደ እንቅስቃሴ የሚቀይር ሲሆን ይህም በተለይ አካል ጉዳተኞች በሃሳባቸው ብቻ የተለያዩ መሣሪያዎችን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል።
ከቀድሞዎቹ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች በተለየ መልኩ ይህ ቺፕ በራስ ቅል ላይ ምንም ዓይነት ትልቅ ቀዳዳ ወይም ግዙፍ ሃርድዌር የማይጠይቅ በመሆኑ የቴክኖሎጂውን ስውርነትና ምቾት ወደ ላቀ ደረጃ አሳድጎታል።
መረጃዎችን በከፍተኛ ፍጥነትና በገመድ አልባ ዘዴ ወደ ውጭ የሚያስተላልፈው ይህ ግኝት በሰው ልጅ እና በዲጂታል ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ ታላቅ የፈጠራ ውጤት ተብሎ ተመዝግቧል።

11 months ago
ፈናን ፔይ የዲጅታል ክፍያ ስርዓት በይፋ ስራ ጀመረ
#fastmereja I በፈናን ፔይ ሶሉሽንስ አክሲዮን ማህበር የበለፀገው ፈናን ፔይ አስፈላጊውን መስፈርት አሟልቶ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጠው የዲጅታል ክፍያ ስርዓት በይፋ ሥራ መጀመሩ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ተገልጿል።
ፈናን ፔይ የዲጅታል ክፍያ ስርዓት በአገልግሎት ሰጪዎችና በደንበኞቻቸው መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀልጣፋ የመስመር (online/electronic payment) ላይ ግብይቶችን ለማመቻቸት የተነደፈ የክፍያ ዘዴ ነው ተብሏል።
ፈናን ፔይ በባንክ ሥራ ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተመሠረተ ከመሆኑ አንፃር ቴክኖሎጂው አስተማማኝ መሆኑን በተግባር ጭምር ተረጋግጧል ተብሏል።
የፋይናንስ ተቋማት በገንዘብ ዝዉዉር ላይ የሚያስከፍሉትን ከፍተኛ የሆነ ኮሚሽን የሚያስቀር የዲጅታል የክፍያ ስርዓት ፈናን ፔይ ድርጅቶች እስከ 0 በመቶ (ኮሚሽን እንዳይከፍሉ) የሚደረግበትን አሰራር የሚያበረታታ ነው። ይህ ዜሮ በመቶ ኮሚሽን የሚወሰነው ድርጅቶች ባላቸው አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና ብቃት ሲሆን ይህንን ማሳካት ለማይችሉ ተቋማት ሲስተሙ በራሱ በሚሰጠው አማራጮች በድርድር ገበያው ላይ ካለው ኮሚሽን አነስተኛውን የኮሚሽን ክፍያ እንዲከፍሉ በአማራጭነት በማቅረብ ነው ተብሏል።
ፈናን ፔይ ባለፉት ስድስት የሙከራ ወራት ወቅት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የክፍያ ዝውውሮችን በተሳካ ሁኔታ በማድረግ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ማከናወኑ ተነግሯል።
ባለፉት ስድስት የሙከራ ወራት ወቅት በሁሉም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመዘኛ መስፈርቶች ውጤታማ በመሆን የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ሆኖ እንዲያገለግል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እውቅናን አግኝቷል።

የህግ አገልግሎትን በማዘመን በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ይፋ ሆነ
#fastmereja I ኢትዮ ሌጋል ሺልድ የጥብቅና ማህበር ከገበያ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር የሕግ አገልግሎትን የሚያዘምንና ለሁሉም ተደራሽ የሚያደርግ በAI የታገዘ የህግ ቴክኖሎጂ የህግ ባለሙያዎች፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች፣ የመንግስት ባለድርሻ አካላትና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
የሕግ ቴክኖሎጂን (LegTech) በመጠቀም በኢትዮጵያ የጥብቅና አገልግሎትን ዘመናዊ ለማድረግ እና ተደራሽነትን ለማስፋት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ የህግ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ጠበቃን ባይተካም አገልግሎቱን ለማዘመንና ያለውን የስራ ጫና ለማቅለል የሚረዳ ቴክኖሎጂ እንደሆነና በዌብሳይት ጠበቃ በመምረጥ የህግ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት ነው ተብሏል።
ይህ አገልግሎት የህግ ባለሙያዎችንና ደንበኞችን በቀጥታ የሚያገናኝ ከመሆኑ ባሻገር የሕግ አገልግሎትን ለሁሉም ማህበረሰብ የመክፈል አቅም እና የቦታ ርቀት ውስንነት ሳይገደብ ተደራሽ የሚያደርግ በመሆኑ በዘርፉ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ተነግሯል።
በመርሀገብሩ ላይ "በቴክኖሎጅ የታገዘ የህግ አገልግሎት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ፣ የህግ ቴክኖሎጂ ለፍትህ ተደራሽነትና ለዘርፉ እድገት ስላለው አስተዋጽኦ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄዷል።

1 year ago
አውስትራሊያ የሌሊት የመንገድ ደህንነትን ለማሻሻል የሚያበሩ መንገዶችን እየገነባች መሆኑ ተገለጸ
አውስትራሊያ በምሽት የመንገድ ደህንነትን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሻሻል ያለመ አዲስና ፈጠራ ያለው ፕሮጀክት መጀመሯ ተነግሯል።
ፕሮጀክቱ በጨለማ ውስጥ በራሳቸው የሚያበሩ መንገዶችን መገንባትን የሚያካትት ሲሆን፣ ይህም በተለይ የመንገድ መብራት በሌለባቸው አካባቢዎች ታይነትን እንደሚያሳድግ ይጠበቃል ተብሏል።
በመኪናዎች ብርሃን ብቻ በመተማመን ከሚነዱ ባህላዊ መንገዶች በተለየ መልኩ፣ እነዚህ አዳዲስ መንገዶች በቀን ውስጥ የፀሐይ ብርሃንን የሚወስዱ እና በምሽት ላይ አረንጓዴ ብርሃን የሚያመነጩ ልዩ ቁሶችን በመጠቀም የተገነቡ ናቸው ተብሏል።
ይህም ለአሽከርካሪዎች የመንገዱን ዳርቻዎች፣ መስመሮች እና አቅጣጫዎች በግልፅ እንዲያዩ ያስችላቸዋል የተባለ ሲሆን የትራፊክ አደጋዎችን የመቀነስ እና አጠቃላይ የመንዳት ልምድን የማሻሻል ተስፋ አለው ተብሎለታል።
የአውስትራሊያ መንግስት ይህንን ቴክኖሎጂ በመንገድ አውታረመረቡ ውስጥ በማስፋፋት ለዜጎች ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አማራጭ ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።
ይህ እርምጃ ሀገሪቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የትራፊክ ደህንነትን ለማስጠበቅ ከምታደርጋቸው ጥረቶች አንዱ አካል ነው ተብሏል።
የፕሮጀክቱ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ይህ ፈጠራ የአሽከርካሪዎችን ንቃት ከማሳደጉም ባሻገር በመብራት ላይ የሚወጡ ወጪዎችን በመቀነስ ለአካባቢ ጥበቃም የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል ነው የተባለው።
በቀጣይ በሌሎች የዓለም ክፍሎችም ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ ይሆናሉ ተብሏል።

Comments