የሰው ልጅን አስተሳሰብ ወደ ተግባር የሚቀይረው ረቂቅ ቺፕ ይፋ ተደረገ
በሳይንሱ ዓለም ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረውና ቢአይኤስሲ (BISC) ተብሎ የሚጠራው አዲስ የአእምሮ ውስጥ ቺፕ በታህሳስ 2025 በይፋ ለዓለም ቀርቧል። ይህ ቴክኖሎጂ ከሰው ፀጉር በበለጠ የሚቀጥን ሲሆን ያለምንም የሚታይ ገመድ ወይም የውጭ መሣሪያ የሰውን ልጅ የውስጥ ሃሳብ በቀጥታ ወደ ተግባር የመተርጎም ልዩ አቅም አለው።
በኔቸር ኤሌክትሮኒክስ (Nature Electronics) ላይ የወጣው ይሄው ጥናት እንደሚያመለክተው መሣሪያው በአእምሮ እና በኮምፒውተር መካከል ያለውን ግንኙነት እጅግ ፈጣንና ስውር በሆነ መንገድ ያከናውናል።
ቺፑ በአእምሮ ውስጥ የሚፈጠሩ የኤሌክትሪክ ምልክቶችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ወደ እንቅስቃሴ የሚቀይር ሲሆን ይህም በተለይ አካል ጉዳተኞች በሃሳባቸው ብቻ የተለያዩ መሣሪያዎችን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል።
ከቀድሞዎቹ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች በተለየ መልኩ ይህ ቺፕ በራስ ቅል ላይ ምንም ዓይነት ትልቅ ቀዳዳ ወይም ግዙፍ ሃርድዌር የማይጠይቅ በመሆኑ የቴክኖሎጂውን ስውርነትና ምቾት ወደ ላቀ ደረጃ አሳድጎታል።
መረጃዎችን በከፍተኛ ፍጥነትና በገመድ አልባ ዘዴ ወደ ውጭ የሚያስተላልፈው ይህ ግኝት በሰው ልጅ እና በዲጂታል ዓለም መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ ታላቅ የፈጠራ ውጤት ተብሎ ተመዝግቧል።
seledadotio

8 months ago