Logo
FastMereja
የህግ አገልግሎትን በማዘመን በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ይፋ ሆነ
#fastmereja I ኢትዮ ሌጋል ሺልድ የጥብቅና ማህበር ከገበያ ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር የሕግ አገልግሎትን የሚያዘምንና ለሁሉም ተደራሽ የሚያደርግ በAI የታገዘ የህግ ቴክኖሎጂ የህግ ባለሙያዎች፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች፣ የመንግስት ባለድርሻ አካላትና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።

የሕግ ቴክኖሎጂን (LegTech) በመጠቀም በኢትዮጵያ የጥብቅና አገልግሎትን ዘመናዊ ለማድረግ እና ተደራሽነትን ለማስፋት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የህግ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ጠበቃን ባይተካም አገልግሎቱን ለማዘመንና ያለውን የስራ ጫና ለማቅለል የሚረዳ ቴክኖሎጂ እንደሆነና በዌብሳይት ጠበቃ በመምረጥ የህግ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት ነው ተብሏል።

ይህ አገልግሎት የህግ ባለሙያዎችንና ደንበኞችን በቀጥታ የሚያገናኝ ከመሆኑ ባሻገር የሕግ አገልግሎትን ለሁሉም ማህበረሰብ የመክፈል አቅም እና የቦታ ርቀት ውስንነት ሳይገደብ ተደራሽ የሚያደርግ በመሆኑ በዘርፉ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነ ተነግሯል።

በመርሀገብሩ ላይ "በቴክኖሎጅ የታገዘ የህግ አገልግሎት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ፣ የህግ ቴክኖሎጂ ለፍትህ ተደራሽነትና ለዘርፉ እድገት ስላለው አስተዋጽኦ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄዷል።
#ሳይ_ቴክ

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.