2 months ago
በምርጫ ክልል ደረጃ የውጤት ይፋ የማድረግ ሂደት መዘግየቱ ተገለጠ፤
* 313 ምርጫ ክልሎች እስካሁን ውጤት አላሳወቁም
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ከተካሄደባቸው 1 ሺህ 138 የምርጫ ክልሎች ውስጥ እስካሁን ውጤት ይፋ ያደረጉት 8 መቶ 25ቱ ብቻ መሆናቸውንና ቀሪዎቹ 3 መቶ 13 የምርጫ ክልሎች አሁንም በድምፅ ማዳመር ሂደት ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በርካታ የምርጫ ክልሎች ውጤቱን ይፋ ለማድረግ ወደኋላ መቅረታቸውን ገልጸው ለዚህም እንደ ሲዳማና አዲስ አበባ ያሉ አካባቢዎችን በምሳሌነት አንስተዋል።
በሲዳማ ክልል ካሉ 19 የምርጫ ክልሎች ውስጥ እስካሁን ውጤት የተለጠፈው በሁለቱ ብቻ ሲሆን፣ ለዚህም በሀዋሳ ያሉ 303 የምርጫ ጣቢያዎች መብዛትና የዕጩዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆን በማዳመር ሥራው ላይ መዘግየት መፍጠሩ ተብራርቷል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በአዲስ አበባ ከሚገኙ 33 የምርጫ ክልሎች ውስጥ 11ዱ ብቻ ውጤት ይፋ አድርገው ወደ ማዕከል የላኩ ሲሆን፣ የዋና ከተማው መዘግየትም ከሌሎች ክልሎች ጋር ተመሳሳይ በሆኑ ምክንያቶች የመነጨ መሆኑ ተጠቁሟል።
በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ 22 የምርጫ ክልሎች ውስጥ ውጤት ይፋ ያደረጉት ሁለቱ ብቻ ሲሆኑ፣ ለዚህ መዘግየት ደግሞ የምርጫ ጣቢያዎቹ ከምርጫ ክልሉ ማዕከል ያላቸው ርቀት ከፍተኛ መሆኑ በምክንያትነት ተጠቅሷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#የኢትዮጵያምርጫ #የምርጫውጤት #የምርጫቦርድ #ወሮሜላተወርቅ #የድምፅማዳመር

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በድል መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ
#ethiopia | ከፍተኛ የዕጩ ተወዳዳሪዎች ቁጥር የተመዘገበበት ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ በስኬታማ ሁኔታ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በየምርጫ ጣቢያዎቹ የተሰጡ ድምጾችን የማደመርና ውጤቱን ይፋ የማድረግ ተግባር በመከናወን ላይ ይገኛል።
በየምርጫ ጣቢያው የተሰበሰበው ድምፅ በይፋ ከተለጠፈ በኋላ ውጤቱ ተጠቃሎ ወደ የምርጫ ክልሉ ይላካል። በምርጫ ክልል ደረጃም የድምፅ ማጠቃለል ሥራው ከተከናወነ በኋላ ውጤቱን በይፋ ለማወጅና ለማረጋገጥ ወደ ዋናው መሥሪያ ቤት የማረጋገጫ ማዕከል እንዲመጣ ይደረጋል።
ውጤቶቹ ወደ ማረጋገጫ ማዕከሉ በሚደርሱበት ወቅት የእያንዳንዱ ምርጫ ክልል መረጃ በተናጠል ተለይቶ የሚታይ ሲሆን ተወዳዳሪዎች ያገኙት የድምፅ መጠን በዝርዝር የማጣራት ሥራ በትኩረት ይከናወናል።
ሰብሳቢዋ አክለውም በማዕከሉ ውስጥ ከተመዘገበው አጠቃላይ የመራጭ ሕዝብ ቁጥር አንጻር ጸንተው የሚደመሩ፣ ዋጋ የሌላቸው እና ጥቅም ላይ ያልዋሉ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የመለየት ተግባር በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚሠራ አስታውቀዋል።
ቦርዱ ይህንን የማረጋገጥ ሒደት በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ሰብሳቢዋ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገልጸዋል።
#ምርጫቦርድ #ምርጫ #የምርጫውጤት #የኢትዮጵያምርጫ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
u12e8u1353u122du1272u12ceu127d u12e8u1200u1233u1265 u1219u130du1275 u1366 u12e8u121bu1295u1290u1275 u1325u12ebu1244 u12a5u1293 u122bu1235u1295 u1260u122bu1235 u121bu1235u1270u12f3u12f0u122d | u1260u121du122du132b u1266u122du12f5 u12e8u1270u12d8u130bu1300u12cd u12c8u1233u129d u12adu122du12adu122du1362
#nebe #ethiopiaelection #politicaldebate #selfdetermination #identitypolitics #ethiopianpolitics #nationalelectionboard #federalism #democracyethiopia #amharicnews #u12a2u1275u12eeu1335u12eb #u121du122du132bu1266u122du12f5 #u12e8u1353u122du1272u12ceu127du12adu122du12adu122d ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የፓርቲዎች የሀሳብ ሙግት ፦ የማንነት ጥያቄ እና ራስን በራስ ማስተዳደር | በምርጫ ቦርድ የተዘጋጀው ወሳኝ ክርክር።
#nebe #ethiopiaelection #politicaldebate #selfdetermination #identitypolitics #ethiopianpolitics #nationalelectionboard #federalism #democracyethiopia #amharicnews #ኢትዮጵያ #ምርጫቦርድ #የፓርቲዎችክርክር
3 months ago
የሐሳብ ፍልሚያ በዴሞክራሲ መድረክ
**********
ሐሙስ ምሽት 2፡30 በኢቢሲ ይጠብቁን !
#ethiopianbroadcastingcorporation #democracy #ክርክር #ምርጫቦርድ #ኢትዮጵያ
5 months ago
🗳️ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ9 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ባለው ሂደት 9 ሚሊዮን 360 ሺህ 994 መራጮች በዲጂታል እና በማንዋል መመዝገባቸውን አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ምሽቱን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የምዝገባ ሂደቱ ያለበትን ደረጃና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በዝርዝር አብራርተዋል።
ዋና ዋና መረጃዎች፦
* የጣቢያዎች ሁኔታ፦ በሀገሪቱ ካሉ ከ52 ሺህ በላይ ጣቢያዎች ውስጥ 46,757 የሚሆኑት ሥራ የጀመሩ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 6,395 ጣቢያዎች በቁሳቁስ መዘግየት ምክንያት እስካሁን ሥራ አልጀመሩም።
* የገጠሙ ተግዳሮቶች፦ የቁሳቁስ ስርጭቱን ካስተጓጎሉ ምክንያቶች መካከል የተሽከርካሪ እጥረት፣ የነዳጅ እጥረት፣ የዝናብ ሁኔታ፣ በአፋር ክልል ያጋጠመ የቁሳቁስ መቃጠል እና የአንዳንድ ክልል አመራሮች የትብብር ማጣት ተጠቅሰዋል።
* የምዝገባ እንቅፋቶች፦ በመራጮች ምዝገባ ወቅት የመብራት እና የኢንተርኔት መቆራረጥ እንዲሁም የመራጮች የመረጃ አሰጣጥ ስህተቶች (የስም ቅደም ተከተል አለመጠበቅ) እንደ ዋና ችግር ተነስተዋል።
* የፓርቲዎች ክርክር፦ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ክርክር መድረክ ዝግጅት የሚከታተል የባለሙያዎች ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።
የመራጮች ምዝገባ ሂደት እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ቦርዱ በድጋሚ አሳስቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #ምርጫ2018 #ብሔራዊምርጫቦርድ #የመራጮችምዝገባ #ዴሞክራሲ #ethiopiaelection2018 #nebe #electionupdate

ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከ10 ሺህ በላይ እጩዎች ለውድድር ቀረቡ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑን ገለጸ። ትናንት ማምሻውን በሰጠው መግለጫ፣ ለዘንድሮው ምርጫ በአጠቃላይ 10 ሺህ 934 እጩ ተወዳዳሪዎች መመዝገባቸውን ይፋ አድርጓል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደገለጹት፣ የምዝገባ ሂደቱ በዲጂታል ስርዓት የተከናወነ ሲሆን ተወዳዳሪዎቹ የቀረቡት በሁለት ዘርፍ ነው፦
* ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፦ 2 ሺህ 198 እጩዎች
* ለክልል ምክር ቤቶች፦ 8 ሺህ 736 እጩዎች
የተሳታፊዎች ስብጥር፦
* በድምሩ 47 የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን፣
* በተጨማሪም 73 የግል እጩዎች ለውድድር መቅረባቸው ታውቋል።
ቦርዱ አክሎም፣ የእጩዎች ዝርዝር ነገ ይፋ እንደሚደረግና ከዜጎች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ይህም የምርጫውን ግልጽነትና ተዓማኒነት ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ተጠቁሟል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #ምርጫ2018 #ብሔራዊምርጫቦርድ #ዴሞክራሲ #ዜና #ethiopia #election2026

Comments