Logo
Getu Temesgen
በምርጫ ክልል ደረጃ የውጤት ይፋ የማድረግ ሂደት መዘግየቱ ተገለጠ፤

* 313 ምርጫ ክልሎች እስካሁን ውጤት አላሳወቁም
#ethiopia | ​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ ከተካሄደባቸው 1 ሺህ 138 የምርጫ ክልሎች ውስጥ እስካሁን ውጤት ይፋ ያደረጉት 8 መቶ 25ቱ ብቻ መሆናቸውንና ቀሪዎቹ 3 መቶ 13 የምርጫ ክልሎች አሁንም በድምፅ ማዳመር ሂደት ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።

​የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በርካታ የምርጫ ክልሎች ውጤቱን ይፋ ለማድረግ ወደኋላ መቅረታቸውን ገልጸው ለዚህም እንደ ሲዳማና አዲስ አበባ ያሉ አካባቢዎችን በምሳሌነት አንስተዋል።

​በሲዳማ ክልል ካሉ 19 የምርጫ ክልሎች ውስጥ እስካሁን ውጤት የተለጠፈው በሁለቱ ብቻ ሲሆን፣ ለዚህም በሀዋሳ ያሉ 303 የምርጫ ጣቢያዎች መብዛትና የዕጩዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆን በማዳመር ሥራው ላይ መዘግየት መፍጠሩ ተብራርቷል።

​በተመሳሳይ ሁኔታ በአዲስ አበባ ከሚገኙ 33 የምርጫ ክልሎች ውስጥ 11ዱ ብቻ ውጤት ይፋ አድርገው ወደ ማዕከል የላኩ ሲሆን፣ የዋና ከተማው መዘግየትም ከሌሎች ክልሎች ጋር ተመሳሳይ በሆኑ ምክንያቶች የመነጨ መሆኑ ተጠቁሟል።

​በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ 22 የምርጫ ክልሎች ውስጥ ውጤት ይፋ ያደረጉት ሁለቱ ብቻ ሲሆኑ፣ ለዚህ መዘግየት ደግሞ የምርጫ ጣቢያዎቹ ከምርጫ ክልሉ ማዕከል ያላቸው ርቀት ከፍተኛ መሆኑ በምክንያትነት ተጠቅሷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#የኢትዮጵያምርጫ #የምርጫውጤት #የምርጫቦርድ #ወሮሜላተወርቅ #የድምፅማዳመር

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.