1 month ago
በድሬዳዋ ከተማ 548 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ሊወጣ ነው
#ethiopia | የድሬዳዋ አስተዳደር በኢንዱስትሪ መንደር ሳይት ሶስት የገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች የባለቤትነት ዕጣ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ እንደሚያወጣ አስታወቀ።
የድሬዳዋ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢማጅ አብደላ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣ በዕለቱ ለዕጣ የሚቀርቡት በአጠቃላይ 548 ቤቶች ሲሆኑ፣ መስፈርቱን አሟልተው የቆጠቡ ከ7,000 በላይ ቆጣቢዎች በሂደቱ ይሳተፋሉ ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የዕጣ አወጣጡን ሂደት ሙሉ በሙሉ ግልጽና ተአማኒ ለማድረግ፣ ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አፕሊኬሽን እንደሚጠቀም አስታውቋል።
ዕጣው አወጣጥ ሂደትም ለሴቶች 30 በመቶ፣ ለመንግስት ሠራተኞች 20 በመቶ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 2 በመቶ ቅድሚያ የሚሰጥበት አሠራር መዘርጋቱ ተጠቁሟል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በ2019 ዓ.ም. አራት ነጥብ አምስት ሄክታር መሬት ላይ "ሳይት አራት" የተሰኘ ዘመናዊ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አቶ ኢማጅ አክለው ገልጸዋል።
#ድሬዳዋ #የጋራመኖሪያቤት #የቤትዕጣ #ኢትዮጵያ #ልማት #diredawa #ethiopia #housingdevelopment

3 months ago
የአልቲማ ሪል እስቴት የሽያጭ ኤክስፖ ሊጠናቀቅ የጥቂት ሰዓታት ዕድል ብቻ ቀረው
#ethiopia | በአዲስ አበባ እምብርት መስቀል ፍላወር ዋና መንገድ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባ የሚገኘው የፕሪምየም ሳይት የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ኤክስፖ ነገ ይጠናቀቃል።
አልቲማ ሪል እስቴት ለደንበኞቹ ባዘጋጀው በዚህ ልዩ የሽያጭ መርሃ ግብር ላይ የ20 በመቶ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን በ5 በመቶ ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት መሆን የሚያስችል ዕድል ተመቻችቷል።
ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ክፍሎችን ከ530,000 ሺህ ብር ጀምሮ በሚከፈል ቅድመ ክፍያ የራስዎ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን ይህም ለትውልድ የሚተርፍ ቋሚ ቅርስ ዛሬውኑ ለማስቀመጥ መልካም አጋጣሚ ነው።
ቤቶቹን በተባለው ጊዜ በማስረከብ የሚታወቀው አልቲማ ሪል እስቴት ይህ የማይደገም ዕድል ሳያመልጥዎ እንዲጠቀሙ ጥሪውን ያቀርባል።
#አልቲማሪልእስቴት #ቤትሽያጭ #መስቀልፍላወር #ኢንቨስትመንት #የመኖሪያቤት #አዲስአበባ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
ቤቶች በ24 ሰዓት ውስጥ መታተም ጀመሩ
#ethiopia | ለዓመታት የሚፈጀውና አድካሚው የቤት ግንባታ ሂደት በቴክኖሎጂ ታግዞ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ግዙፍ የ3D ፕሪንተሮች የሰውን ልጅ የመኖሪያ ቤት ሕልም በሰዓታት ውስጥ እውን ማድረግ ጀምረዋል።
ቴክኖሎጂው እንዴት ይሠራል?
* ግዙፍ የሮቦት እጅ፦ እንደ ቢሮ ፕሪንተር የሚሠራው ይህ ቴክኖሎጂ፣ በኮምፒውተር የተነደፈውን ፕላን መሠረት በማድረግ ግድግዳዎችን ይገነባል።
* ልዩ ድብልቅ፦ ከቀለም ይልቅ ልዩ የኮንክሪት ድብልቅን በመጠቀም ሲሚንቶውን በንብርብር ያፈስሰዋል።
* ፈጣን የግንባታ ጊዜ፦ ሮቦቱ ያለ ዕረፍት ስለሚሠራ የአንድን መካከለኛ ቤት ግድግዳዎች ከ12 እስከ 24 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ያስረክባል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ተሞክሮ
ይህ ቴክኖሎጂ በተለያዩ አህጉራት በተግባር ላይ መዋል ጀምሯል፦
* አሜሪካ (ቴክሳስ)፦ በዓለም ትልቁ የ3D ቤቶች መንደር ተገንብቶ ለነዋሪዎች ተላልፏል።
* አውሮፓ (ጀርመንና ኔዘርላንድስ)፦ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለ ሁለት ፎቅ የታተሙ ቤቶች ተገንብተው ነዋሪዎችን ተቀብለዋል።
* አፍሪካ (ኬንያና ማላዊ)፦
ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ትምህርት ቤቶችንና መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ረገድ ቀዳሚ ሆነዋል።
* ሜክሲኮ፦ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች የሚሆኑ የመኖሪያ መንደሮች ተገንብተዋል።
የቴክኖሎጂው ጥቅሞችና ተግዳሮቶች
* ጥቅሞች፦ የሰው ኃይል ፍላጎትን እስከ 80 በመቶ ይቀንሳል፣ የግንባታ ወጪን ያቃልላል፣ እንዲሁም የግንባታ ትርፍራፊን በማስቀረት ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ ነው።
* ተግዳሮት፦ ማሽኖቹን ወደ ግንባታ ቦታ ለማጓጓዝ ያለው ወጪ በአሁኑ ወቅት እንደ ተግዳሮት ይነሳል።
ባለሙያዎች እንደሚገምቱት በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ ይህ ቴክኖሎጂ የግንባታ ዘርፉን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የሰዎችን የመጠለያ ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።
ይሄ ነገር ወደ ሃገራች ኢትዮጵያ መች ይሆን የሚመጣው?
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #3dግንባታ #ቴክኖሎጂ #ቤትግንባታ #አዲስፈጠራ #ኢኮኖሚ #መኖሪያቤት

Sponsored by
Surafel
Comments