በድሬዳዋ ከተማ 548 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ሊወጣ ነው
#ethiopia | የድሬዳዋ አስተዳደር በኢንዱስትሪ መንደር ሳይት ሶስት የገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች የባለቤትነት ዕጣ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ እንደሚያወጣ አስታወቀ።
የድሬዳዋ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢማጅ አብደላ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣ በዕለቱ ለዕጣ የሚቀርቡት በአጠቃላይ 548 ቤቶች ሲሆኑ፣ መስፈርቱን አሟልተው የቆጠቡ ከ7,000 በላይ ቆጣቢዎች በሂደቱ ይሳተፋሉ ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የዕጣ አወጣጡን ሂደት ሙሉ በሙሉ ግልጽና ተአማኒ ለማድረግ፣ ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አፕሊኬሽን እንደሚጠቀም አስታውቋል።
ዕጣው አወጣጥ ሂደትም ለሴቶች 30 በመቶ፣ ለመንግስት ሠራተኞች 20 በመቶ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 2 በመቶ ቅድሚያ የሚሰጥበት አሠራር መዘርጋቱ ተጠቁሟል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በ2019 ዓ.ም. አራት ነጥብ አምስት ሄክታር መሬት ላይ "ሳይት አራት" የተሰኘ ዘመናዊ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አቶ ኢማጅ አክለው ገልጸዋል።
#ድሬዳዋ #የጋራመኖሪያቤት #የቤትዕጣ #ኢትዮጵያ #ልማት #diredawa #ethiopia #housingdevelopment

27 days ago