4 hours ago
የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሚያሰራውን ቤተሰሊሆም አጠቃላይ ሆስፒታል ህንፃ ግንባታን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡
ከሁሉ አሰቀድመን እግዚአብሔር አምላካችን ለ2018 ዓ.ም ጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሁላችንንም በሰላም በጤና ስላደረሰን እናመሰግነዋለን፡፡የተከበራችሁ አበው መነኮሳት፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት እና ዲያቆናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ ምዕመናን እና ወጣቶች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች እንዲሁም ይህን መልእክት ለመላው ዓለም ለማስተላለፍ የተገኛችሁ የሚድያ አካላት በሙሉ በእግዚአብሔር ስም የከበረ ሰላምታችንን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከሆነው ከየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እናቀርባለን፡፡
“በኂሩተ ጻድቃን ትረትዕ ሀገር”
“በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል”
ምሳ 11፥10
እግዚአብሔር በንጉሱ ሰሎሞን ላይ አድሮ የተናገረውን መነሻ በማድረግ ልማት ለቤተከርስቲያን ፣ልማት ለሀገር፣ልማት ለማኅበረ ስብእ አስፈላጊ መሆኑን በማሰብ በአዲስ አበባ ሀገረ ስበከት በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለሚገነባው ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል የህንፃ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የቀጥታ ስርጭት መርሃ ግብር የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡ የእግዚአበሔር ሰላም ከሁላችንም ጋር ይሁን፡፡ አሜን።
1. ታሪካዊ ዳራ እና የልማት መነሻ
ከአክሱም ዘመነ መንግሥት (በአባ ሰላማ ዘመን) የጀመረውና ከ1600 ዓመታት በላይ የዘለቀው የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ የኢትዮጵያን ጥንታዊነትና የአዲስ አበባን ከተማ አመሰራረት የሚተርክ ህያው ቅርስ ነው።ይህ ታሪካዊ ደብር በአብርሃ ወአጽብሃ፣ በዳግማዊ አጼ ምኒልክና በንግሥት ጣይቱ፣ እንዲሁም በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በርካታ የታሪክና የፈተና ምዕራፎችን አልፎ ዛሬ ላይ ደርሷል።
ደብሩ ከሃይማኖታዊ አገልግሎቱ ባሻገር፣ የአዲስ አበባ የመጀመሪያው የቀብር ቦታ በመሆን የሊቃውንቱና የካህናቱ እንዲሁም የታላቁ ሐኪም ወርቅነህ እሸቴን፣ የኢትዮጵያ ታላላቅ ጄነራሎችና ፊት አውራሪዎችን ዓጽም በክበር ማረፊያ ሆኗል፡፡ የጸሎትና ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሁም ለአካባቢው አብያተ ክርስቲያናት መመስረት ባደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይታወቃል። ዛሬ ይህ ታሪካዊ ደብር ጥንታዊ ታሪኩንና መንፈሳዊ ታላቅነቱን በዘመናዊ ማህበራዊ ልማት ለመድገም፣አካላዊ ፈውስን በሳይንሳዊ ሕክምና የመንፈሳዊ ፈውስን በፀሎትና በጠበል የሚያዋህድ ታላቅ የልማት ፕሮጀክት ይፋአድርጓል።
2. የሆስፒታሉ ይዘት፣ ራዕይና ሰብዓዊ ተልዕኮ
ቤተክርስቲያኑ ባለ 15 ወለል ማለትም (2 Basement+G+ 12ወለል) የሆነውን «ቤተሰሊሆም ጠቅላላ ሆስፒታል» ህንፃ ግንባታ የጀመረ ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የመሰረት ቁፋሮና የአፈር ናዳ መከላከያ (ሾሪንግ) ሥራ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
ይህ በ1000 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ባለ 250 የህሙማን ሕክምና መስጫ አልጋ አቅም የሚኖረው ዘመናዊ ሆስፒታል፤ የተመላላሽ ክሊኒኮችን፣ የፅኑ ሕክምና (ICU)፣ የቀዶ ጥገና ክፍሎችን እንዲሁም ለእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ ለልብ ሕክምናና ለተላላፊ በሽታዎች መከላከያ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ማዕከላትን ያካትታል። ተቋሙ የጤና አጠባበቅን እንደ ንግድ ሳይሆን እንደ ሰብዓዊና መንፈሳዊ አገልግሎት በመመልከት፣ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት በሙሉ ጥራት ያለው፣ ተደራሽና አቅምን ያገናዘበ የሕክምና አገልግሎት ያቀርባል።
3. የግንባታ ወጪ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ
በህንፃ ባለሙያዎች ጥናት መሠረት ለህንፃ ግንባታው አጠቃላይ ወጪ ብር 405,040,000 (አራት መቶ አምስትሚሊዮን አርባ ሺህ ብር) እንደሚሆን ተገምቷል።ይህ ወጪ በየጊዜው በሚታየው የዋጋ ንረት ምክንያት ሊጨምር እንደሚችል ይታሰባል፡፡
ይህንን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈንና ቀጣዩን ወሳኝ የግንባታምዕራፍ ለመጀመር ቤተ ክርስቲያኑ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚኖሩ ምዕመናንን፣ የንግዱን ማህበረሰብና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ የሀብት ማሰባሰቢያ ስልት ቀይሷል።
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና የልማት ኮሚቴው ምዕመናን በሰጦታቸው ከእግዚአብሔር የሚያገኙትን በረከት በማሰብ፦ «ይህ ታላቅ የማህበራዊና የጤና ልማት ፕሮጀክት ፍጻሜ እንዲያገኝ የዓላማው ደጋፊዎች ሁሉ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉና አሻራቸውን እንዲያኖሩ በሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ስም እንማጸናለን» ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል።
የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ዝርዝር፦
• ቀን፦ ነሐሴ 8፣ 9 እና 10 ቀን 2018 ዓ.ም
• ሰዓት፦ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ
የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ አማራጮች፦
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብቁጥር፦
1000000764087 እንዲሁም
አጭር ቁጥር 1277
• አባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር፦ 1227
• አዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
013521784586601
• ስዊፍት ኮድ AWINETAA
• ወገን ፈንድ 👉 https://www.wegenfund.com/...
ለተጨማሪ መረጃ፦
• ስልክ ቁጥር፦
0945881188 እና 0945771188
• Email፦ Seyoumwgebrielgmail .com
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

21 hours ago
በአሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ የአማዞን ሶፍትዌር መሐንዲስ በሌክ ታሆ በውሃ አደጋ ሕይወቱ አለፈ
#ethiopia | በአሜሪካ የቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚሠራው የ32 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ የአማዞን (Amazon) ሶፍትዌር መሐንዲስ ያዴሳ እሚሩ አጋ (Yadessa Emiru Aga) በካሊፎርኒያና ኔቫዳ ድንበር በሚገኘው ታዋቂው ሌክ ታሆ (Lake Tahoe) በውሃ አደጋ ሕይወቱ ማለፉን የአሜሪካ የዜና አውታሮች ዘግበዋል።
በሪፖርቶቹ መሠረት፣ አደጋው እ.ኤ.አ. ጁላይ 27 ቀን 2026 በሌክ ታሆ ምስራቃዊ ዳርቻ በሚገኘው ሳንድ ሃርበር (Sand Harbor) ተከስቷል።
ያዴሳ ወደ ሀይቁ ውስጥ ከገባ በኋላ ድንገት ምላሽ ሳይሰጥ ቀርቶ በውሃ ውስጥ ጠልቆ መታየቱ ተገልጿል።
በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በፍጥነት ወደ ዳርቻ ቢያወጡትም፣ የፖሊስና የሕክምና ቡድኖች ያደረጉት የሕይወት ማዳን ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
የዋሾ ካውንቲ ሸሪፍ መሥሪያ ቤት ክስተቱን እንደ "በአጋጣሚ የተከሰተ የመስጠም አደጋ" እየመረመረው ሲሆን፣ የሞት ትክክለኛ መንስኤ በሕክምና ምርመራ ውጤት እንደሚገለጽ ተነግሯል።
ከአደጋው በኋላ ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ የመጨረሻ ሰዓቶቹ ምን እንደነበሩ ለማወቅ ጥረት እያደረጉ ነው።
በተለይም በአደጋው ወቅት በሳንድ ሃርበር የነበሩ ሰዎች ያነሱትን ፎቶ፣ ቪዲዮ ወይም የዓይን እማኝነት መረጃ እንዲያጋሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ ወደ ኢትዮጵያ የአስከሬን መጓጓዣና የቀብር ወጪ ለመሸፈን የGoFundMe የድጋፍ ዘመቻ መጀመሩም ተዘግቧል።
የያዴሳ የLinkedIn መረጃ እንደሚያሳየው፣ ከ2022 ጀምሮ በአማዞን የሶፍትዌር ልማት መሐንዲስ (Software Development Engineer) በመሆን በአውስቲን፣ ቴክሳስ ይሠራ ነበር። ከዚያ በፊትም በአዲስ አበባ በሶፍትዌር ልማት ዘርፍ ሰርቶ እንደነበር ተገልጿል።
ባለሙያዎች ሌክ ታሆ በግልጽ ውሃና በውብ ተፈጥሮው ቢታወቅም፣ የውሃው ከፍተኛ ቀዝቃዛነት በድንገት የሰውነት ምላሽን በመቀየር ለመስጠም አደጋ እንደሚያጋልጥ ያስጠነቅቃሉ።
በዚህ ሀይቅ በየዓመቱ በአማካይ 6 እስከ 7 የመስጠም አደጋዎች እንደሚመዘገቡም ተጠቁሟል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

2 days ago
በሀገር ውስጥ አቅም ውስብስብ የልብ ቀዶ ጥገናን በተሳካ ሁኔታ ማካሄድ መቻሉ ተገለፀ
****************
በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ለሁለት ሕፃናት ህይወታቸውን የሚታደግ ውስብስብ የልብ ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ ማካሄዱን ገለፀ።
ቀዶ ጥገናው የተደረገው ለ6 ዓመት እና ለ8 ወር ሕፃናት ሲሆን፣ ከቀዶ ጥገና ህክምናው በኋላ የህጻናቱ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ህክምናውን በዶክተር ፍፁም አርጋው የሚመራ የሀገር ውስጥ የልብ ቀዶ ጥገና ቡድን የመራው ሲሆን፣ በዶክተር ሜሮን ተስፋዬ የሚመራው የፅኑ ህክምና ቡድንም ለህፃናቱ ማገገሚያ የሚሆን ልዩ ክትትል እያደረገ መሆኑን ከማዕከሉ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
እንዲህ ያሉ ውስብስብ የልብ ቀዶ ጥገናዎች በሀገር ውስጥ መከናወናቸው የህፃናትን ሕይወት ከመታደግ ባለፈ የሀገሪቱን የልብ ሕክምና አቅም እየጎለበተ ስለመሆኑ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ7,000 በላይ ታካሚ ሕፃናት የልብ ቀዶ ጥገና ለማግኘት በረጅም የተጠባባቂነት ሰልፍ ላይ ይገኛሉ።
እንደዚህ ያሉ ውስብስብ ቀዶ ጥገናዎች በውጭ ሀገራት ለማካሄድ እስከ ሺዎች ዶላር የሚጠይቁ በመሆናቸው፣ ማዕከሉ በነጻ የሚሰጠው ይህ አገልግሎት ለታካሚ ቤተሰቦች ከፍተኛ የፋይናንስ እፎይታን ሰጥቷል።
ከዚህም በላይ የውጭ ሀገር የበጎ አድራጎት ቡድኖችን ሳይጠብቁ በሀገር ውስጥ የልብ ስፔሻሊስቶች አቅም ብቻ መከናወኑ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን የሕክምናና የቴክኖሎጂ አቅም ወደ አዲስ ደረጃ ማሸጋገሯን ማሳያ መሆኑ ተጠቅሷል።
በኢንቲሀድ አብራር

በትግራይ «70 ካሬ» የተፈናቃዮች ማዕከል በጣለው ከባድ ዝናብ እና ንፋስ ከ20 በላይ ጊዜያዊ መጠለያዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ፡፡
የምዕራብ ትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት (ፅላል) አስተባባሪ አቶ ዘበኖም ኪዱ ለትግራይ ቲቪ እንደገለጹት፤ ትላንት በጣለው ከባድ ዝናብ እና ንፋስ መጠለያዎቹ ከጥቅም ውጪ ከመሆናቸውም በላይ በንብረት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሷል።
በተጨማሪም አደጋው በሰዎች ላይ አካላዊ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ በተለይም አረጋውያን ላይ ጉዳት በመድረሱ ለሕክምና እርዳታ ወደ ጤና ተቋም መወሰዳቸውን አስተባባሪው ጨምረው ገልጸዋል።
በደረሰው አደጋ ምክንያት ተፈናቃዮቹ ለበለጠ እንግልት እና ችግር መጋለጣቸውን የጠቆሙት አቶ ዘበኖም፣ የሰብአዊነት ስሜት ያለው አካል ሁሉ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የተፈናቀለው ሕዝብ በከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ያመለከተው የምዕራብ ትግራይ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት፣ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ የሚሆነው ተፈናቃዮች ወደ ቀደመ መኖሪያቸው የሚመለሱበት ሁኔታ ሲመቻች ብቻ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥቷል ሲል ዘገባው መልክቷል።
Seledadotio

ኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል በዓመት ከ79 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ህክምና መስጠቱን ገለጸ
#ethiopia | ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ወደውጭ ሀገር በሚወስዱ የህክምና ጥገኝነትን በመቀየር፣ በሀገር ውስጥ ዘመናዊ ህክምና መስጠት የሚያስችል አገልግሎት መዘርጋቱን አስታወቀ።
ኢትዮ-ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሰጠው መግለጫ ላይ እንደተገለጸው ሆስፒታሉ በመሥራቹና ባለራዕዩ ሲኢኦ አቶ ብርሃን ተድላ እየተመራ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለታካሚዎች ጥራቱን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ በተለይም በያዝነው 2018 ዓ.ም ብቻ ከ79 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት በመስጠትና ከ4 ሺ 500 በላይ የቀዶ ህክምናዎችን በማካሄድ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል።
ሆስፒታሉ እነዚህን ሀገር በቀል አቅሞች በመገንባቱ ቀደም ሲል ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ይሄዱ የነበሩ ታካሚዎችን ቁጥር በመቀነስ የውጭ ምንዛሬን ከማስቀረት ባሻገር የታካሚዎችን ችግር መቅረፍ ችሏል።
በመግለጫው ወቅት የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር፣ የአጠቃላይ እና ደረት አካባቢ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ተባባሪ ኘሮፌሰር ስዩም ካሣ መርኔ እንደገለጹት፣ ተቋሙ በኢንተርቬንሽናል ካርዲዮሎጂ መስክ ያለ ኦፕሬሽን በደም ስሮች በኩል በሚደረግ ህክምና ጨምሮ በአዋቂና በልጆች የልብ ሕክምና በአጠቃላይ ከ735 በላይ ታካሚዎችን መታደግ ችሏል። አክለውም ይህ አገልግሎት ዓመቱን ሙሉ ሌሊትና ቀን ሳይቋረጥ የሚሰጥ በመሆኑ፣ ከውጭ ሀገር በሚመጡ ጊዜያዊ ዘመቻዎች ላይ ብቻ ጥገኛ የነበረውን አሰራር መቀየር መቻሉን ገልጸዋል።
ሆስፒታሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በመታገዝ ወደውጪ ሀገር የሚያስኬዱ በተለይ የልብ ሕክምናዎችን 90 በመቶ በሆስፒታሉ መስጠት መቻሉን ጠቅሰዋል።
እንደ ዶክተር ስዩም ገለጻ፣ ሆስፒታሉ በኒውሮሰርጀሪ፣ በኦፕን ካርዲያክ፣ በአጥንትና ስፓይን፣ በኩላሊት፣ በሳምባ፣ የአንጎል፣ የዳሌና የጉልበት ቅየራ እንዲሁም በሚኒማሊ ኢንቬሲቭ (ላፓሮስኮፒክና ቶራኮስኮፒክ) እና ከ46 በላይ ሰብስፔሻሊቲ ህክምና ዘርፎች የላቀ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፣ የሬዲዮሎጂ ክፍሉም የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የህክምና ምርመራ ጥራቱን በማሳደግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የሆስፒታሉ የውስጥ ደዌና የአዋቂዎች ኢንተርቬንሽናል የልብ ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ከፈለኝ ደጀኔ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ ከተሰሩት 321 የሕፃናት የልብ ህክምናዎች መከናወናቸውን ጠቁመው 90 የሚጠጋ ድንገተኛ የልብ ደምስር መዘጋት አደጋ ያጋጠማቸውና ታካሚዎች በ24 ሰዓት ድንገተኛ አደጋዎች አገልግሎት ህይወታቸው መታደግ ተችላል ብለዋል። ከእነዚህም ውስጥ ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚኾኑ የውጭ ሀገር ዜጎችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል።
የሆስፒታሉ የቺፍ ኦፕሬሽንስ ዳይሬክተር፣ የአንገትና ጭንቅላት ሰብ-ስፔሻሊስት ዶክተር መለስ ገበየሁ እንደገለጹት ደግሞ፣ ተቋሙ ከንግድ ዓላማው ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ትልቅ ስራ እየሰራ ይገኛል። በሆስፒታሉ ባለቤትና ዋና ስራአስፈጻሚ አቶ ብርሃን ተድላ አማካይነት በተቋቋመው "Heart to Heart Children's Aid" የተሰኘ ፋውንዴሽን በኩል ትልቅ ሥራዎች መከናወናቸውን አስታውሰዋል።
ሜዲካል ዳይሬክተሩ በመጨረሻም ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደሥራ መግባቱና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት መድረስ የቻለው በተቋሙ መስራችና ሲኢኦ አቶ ብርሃን ተድላ የቅርብ ጠንካራ አመራርና ክትትል፣ በሰራተኞችና ባለሙያዎች ትጋት መኾኑን በመጥቀስ ምስጋና አቅርበዋል።
ሆስፒታሉ ለ 333 ጊዜያዊና ቋሚ ሰራተኞች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲኾን ከእነዚህ መካከል 86 ያህሉ ሰብስፔሻስት ሐኪሞች መኾናቸው ተነግሯል።
#ethioistanbulhospital #cardiologyservices
#pediatriccardiolog #healthsectorethiopia
#medicaltourismethiopia#hearttoheartchildrensaid

ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ወደውጭ ሀገር በሚወስዱ የህክምና ጥገኝነትን በመቀየር፣ በሀገር ውስጥ ዘመናዊ ህክምና መስጠት የሚያስችል አገልግሎት መዘርጋቱን አስታወቀ።

የጨጓራ ህመም ተገቢዉን ህክምና ካላገኘ የምግብ መተላለፊያ ቱቦን በመዝጋት ለከፋ የጤና ችግር ሊያጋልጥ ይችላል ተባለ
የጨጓራ ህመምን በቤት ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች ማከም አንዱ አማራጭ ቢሆንም ደረጃዉ ከፍ ሳይል ተገቢዉን የህክምና አገልግሎት ካላገኘ ለከፋ የጤና ችግር እንደሚያጋልጥ ተገልጿል።የጨጓራ ህመም ተገቢዉን የህክምና እርዳታ ካላገኘ እና ወደ መጨረሻዉ ደረጃ ከፍ ካለ ቁስለቱ እስከ መድማት ደርሶ ደም ማስመለስን ሊያስከትል ይችላል ።
የጨጓራ ቁስለት በከፍተኛ ደረጃ ተባብሶ የጨጓራ ግድግዳን ሙሉ በሙሉ በመብሳት ቀዳዳ በሚፈጥርበት ወቅት በሆድ ዕቃ ውስጥ ከባድ ኢንፌክሽንን ስለሚያስከትል አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ማግኘት ተገቢ ነዉ ተብሏል ።በተጨማሪም ጨጓራ ከትንሹ አንጀት ጋር የሚገናኝበት ቦታ ላይ በተደጋጋሚ ጉዳት ሲደርስበት ቦታዉ ይጠብና የምግብ መተላለፊያ ቱቦን በመዝጋት ለከፋ የጤና ችግር ስለሚያጋልጥ ተገቢዉን የህክምና እገዛ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የዉስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ዶክተር አምደመስቀል መርሻ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል ።
የህክምና ባለሙያው አክለዉም በአንዳንድ ሰዎች ላይ በጨጓራ ባክቴሪያ አማካኝነት ወደ ካንሰር የመቀየር ዕድል ሊኖረዉ እንደሚችል አስገንዝበዋል።ለህመም ማስታገሻ ተብለዉ የሚወሰዱ እንደ አይቡፕሮፌን እና አስፕሪን ያሉ መድሃኒቶች ለረጅም ጊዜ የሚወሰዱ ከሆነ ለጨጓራ ቁስለት ሊያጋልጡ ይችላሉ በማለት የህክምና ባለሙያው ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

Sponsored by
Surafel
3 days ago
ይህን እሽግ እንደተራ መክሰስ ለገበያ ማቅረብ ወንጀል ነው!
#ethiopia | በከባድ የምግብ እጥረት የተጎዱ ሕፃናትን ሕይወት ለማዳን የሚሰጠው አጣዳፊ የምግብ መድኃኒት (RUTF) ወይ በተለምዶ ስሙ ፕላምፕሌት በገበያ ላይ ለንግድ መቅረቡና ለክብደት መጨመሪያ መዋሉ ከፍተኛ የሞራልና የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ወንጀል መሆኑ ተገለጸ።
በሞት አፋፍ ላይ የሚገኙ ሕፃናትን ለማዳን በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀውን ይህን ሕይወት አድን እሽግ እንደ ተራ መክሰስ ለገበያ ማቅረብ በእርግጥም ህክምናው ለሚገባቸው ሕፃናት የሚደርሰውን እርዳታ በመንጠቅ ሕይወታቸውን ለሞት አደጋ የሚያጋልጥ ተግባር ነው።
በሌላ በኩል ይህ ምርት በካሎሪ፣ በቅባትና በቫይታሚኖች እጅግ የበለፀገ በመሆኑ ጤናማ ሰዎች ሳያስፈልጋቸው ሲመገቡት ለከፍተኛ የኩላሊትና የጉበት ጫና፣ ለደም ስኳርና ቅባት መዛባት እንዲሁም ለቫይታሚን መርዝነት ያጋልጣቸዋል።
በመሆኑም በነፃ ወይም በሕክምና ተቋማት በኩል ለተቸገሩ ሕፃናት የተላከን እርዳታ መሸጥም ሆነ መግዛት በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል በመሆኑ፣ ሕይወት አድን መድኃኒቶች የንግድ ዕቃ አለመሆናቸውን ተረድቶ ኅብረተሰቡ ከዚህ ድርጊት ሊቆጠብ እንደሚገባ መልእክት ተላልፏል።
(via ጤና)
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

በእንግሊዝ ቻናል ውስጥ እሳት ከተነሳበት ጀልባ ከ150 በላይ ሰዎች ተረፉ
#ethiopia | ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ ለመሻገር ሲሞክር የነበረ ትንሽ ጀልባ በእንግሊዝ ቻናል ውስጥ በሞተሩ ላይ እሳት ከተነሳ በኋላ 157 ስደተኞች በሕይወት ታድነዋል።
አደጋው ማክሰኞ ጠዋት በፈረንሳይ የፍለጋና የማዳን ቀጠና ውስጥ ተከስቷል።
በማዳን ዘመቻው የፈረንሳይ የባህር ጠባቂዎች፣ የብሪታንያ የድንበር ጥበቃ ጀልባዎች፣ የባህር ሕይወት አድን ቡድኖች (RNLI) እና ሄሊኮፕተሮች ተሳትፈዋል።
ከተረፉት መካከል 103 ሰዎች በፈረንሳይ መርከቦች ሲድኑ፣ 54 ደግሞ በብሪታንያ ኃይሎች ተወስደዋል።
ባለሥልጣናት እስካሁን የሞት ወይም ከባድ ጉዳት መኖሩን አላረጋገጡም። ሁሉም የተረፉት ወደ ሰሜን ፈረንሳይ የሚገኘው ቡሎኝ-ሱር-መር ወደብ ተወስደው የሕክምና ምርመራ ተደርጎላቸዋል።
ይህ ክስተት በእንግሊዝ ቻናል ላይ በትንንሽ ጀልባዎች የሚደረጉ አደገኛ ስደተኞች ጉዞዎች አሁንም ከፍተኛ አደጋ እንዳላቸው በድጋሚ አሳይቷል።

4 days ago
በአሜሪካ በሳይክሎስፖሪያሲስ (Cyclosporiasis) ወረርሽኝ የመጀመሪያ ሞት ተመዘገበ
#ethiopia | አሜሪካ ውስጥ በCyclospora cayetanensis ተውሳክ የሚከሰተው የሳይክሎስፖሪያሲስ (Cyclosporiasis) ወረርሽኝ ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚህ በሽታ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በሚሺጋን ግዛት መሞታቸውን የግዛቱ የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ይህ በአሜሪካ ታሪክ ከዚህ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የተመዘገበ የመጀመሪያው የሞት ክስተት ነው።
ባለሥልጣናቱ እንደገለጹት፣ ሁለቱም ሟቾች ከዚህ ቀደም ከባድ የጤና ችግሮች የነበሯቸው ሲሆን፣ በተደጋጋሚ ተቅማጥና በውኃ እጥረት (dehydration) ምክንያት የነበራቸው ሁኔታ ተባብሶ ለሞት እንዳደረሳቸው ተገልጿል። የግል መረጃቸው አልተገለጸም።
በሚሺጋን ግዛት ብቻ እስካሁን ከ11,000 በላይ ተጠርጣሪ ወይም የተመዘገቡ ኬሶች ሲኖሩ፣ 193 ሰዎች ሆስፒታል ገብተዋል። በመላው አሜሪካ ደግሞ ከ6,700 በላይ በላብራቶሪ የተረጋገጡ ኬሶች ተመዝግበዋል፣ ተጨማሪ ብዙ ሺህ ጉዳዮችም እየተመረመሩ ይገኛሉ።
የበሽታው ምንጭ ምንድን ነው?
የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል (CDC) እና የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን (FDA) እያካሄዱት ባለው ምርመራ፣ ወረርሽኙ በዋነኝነት ከተበከለ የአይስበርግ ሰላጣ (iceberg lettuce) ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተጠርጥሯል። ሆኖም ምርመራው አሁንም በመቀጠል ላይ ሲሆን የመጨረሻ ማረጋገጫ አልተሰጠም።
የበሽታው ምልክቶች
ከባድ የውኃ ተቅማጥ
የሆድ ህመም
ማቅለሽለሽ
ድካም
የምግብ ፍላጎት መቀነስ
አንዳንድ ጊዜ ትኩሳት
በጤናማ ሰዎች ላይ በአብዛኛው ሕክምና በመውሰድ ይድናል፤ ነገር ግን አረጋውያን፣ የበሽታ መከላከያ አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች እና ሌሎች ከባድ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች ለከፍተኛ አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ።
የጤና ባለሥልጣናት የሰጡት ምክር
ጥሬ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን በደንብ በማጠብ ይጠቀሙ።
የተጠረጠሩ የሰላጣ ምርቶችን አይጠቀሙ።
ተቅማጥ ከቀጠለ ወይም የውኃ እጥረት ምልክቶች ከታዩ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም ይሂዱ።

በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሚገኘው በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ የርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ምዕመናን ሕይወት ማለፉንና በሰባት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ አስተዳደር መምሪያ አስታወቀ።
በአደጋው በ5 ሰዎች ላይ ከፍተኛ እና በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ መለስተኛ የአካል ጉዳት መድረሱን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር መምሪያ ገልጿል።
መምሪያው በአደጋው ህይወታቸውን ባጡ እና ጉዳት በደረሰባቸው ወገኖች የተሰማውን መሪር ኀዘን የገለጸ ሲሆን፣ አደጋው ከተከሰተ በኋላ በስፍራው በመገኘት የተቀናጀ የነፍስ አድኖና የሕክምና እርዳታ ድጋፍ ላደረጉት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ የማነብርሀን ተስፋ፣ የአመራር አካላት፣ ለፀጥታ ኃይሎች፣ ለሕክምና ባለሙያዎችና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል።
በተጨማሪም በአደጋው ስፍራ በመገኘት ለሞቱት ጸሎተ ፍትሐት፣ ለተጎዱት ጸሎትና ለተከፉ ወገኖች የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌልና አባታዊ ቃለ በረከት እየሰጡ ለሚገኙት ለብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ ያለውን አክብሮት ገልጻል።

በኦቶና ሆስፒታል የላብራቶሪ መሳሪያዎችን ሊሰርቅ የነበረ የጥበቃ ሰራተኛ እጅ ከፍንጂ ተያዘ
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል (ኦቶና) ሦስት ወሳኝ የላብራቶሪ ማይክሮስኮፖችን አውጥቶ ለመሰወር ሲሞክር የነበረ የጥበቃ ሰራተኛ በተረኛ ጥበቃዎች ብርቱ ክትትልና ተጋድሎ እጅ ከፍንጂ መያዙ ተገለጸ።
በትላትናው እለተ የተፈጸመው ይህ ድርጊት ተራ የሕክምና ዕቃ ስርቆት ሳይሆን፣ የሺዎችን ሕይወት እና የሆስፒታሉን ዕለታዊ የሕክምና አገልግሎት ቀጥተኛ አደጋ ላይ የጣለ ከባድ ወንጀል መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ተጠርጣሪው ግለሰብ የሕክምና መገልገያዎቹን ደብቆ ከሆስፒታሉ ግቢ ሊያወጣ ሲል በተረኛ ባልደረቦቹ ንቁ ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል። ድርጊቱ በግለሰቡ ብቻ የተፈጸመ ሳይሆን በጀርባ ያሉ አመቻቾችና አቀናባሪዎች እንዳሉበት በመጠረጠሩ፣ ወንጀሉን ያስተባበሩ አካላት በሙሉ ተለይተው ተገቢው የሕግ ትርጉም እንዲሰጣቸውና አስተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ ጉዳዩ በትኩረት እየተከታተለ ይገኛል።
በአንድ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ ማይክሮስኮፕ ማለት የተደበቁ በሽታዎችን አውጥቶ በማሳየት የሕሙማንን ሕይወት የሚያስጥል ዋና መመርመሪያ መሳሪያ ነው።
እነዚህን መገልገያዎች ማጣት በሕሙማን ላይ የሚከተሉትን ከባድ የጤና አደጋዎች ያስከትላል፦
እንደ ወባ፣ ቲቢ እና የተለያዩ ከባድ የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖችን በፍጥነት በመመርመር አስቸኳይ የሕክምና ውሳኔ ለመስጠት ያገለግላሉ።
የደም ማነስን (Anemia) እና የደም ካንሰርን (Leukemia) በጥንቃቄ ለይቶ ለማወቅ ወሳኝ መገልገያዎች ናቸው።
እነዚህ መሳሪያዎች ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ የላብራቶሪ ውጤቶች ይዘገያሉ፤ ይህም በተለይ በፅኑ ሕሙማን፣ በሕፃናትና ነፍሰ ጡራት ሕይወት ላይ የቀጥታ አደጋ ይደቅናል።
የሕዝብና የመንግሥት ሀብት የሆኑትን የሕክምና መገልገያዎች ከስርቆትና ከእጅ አዙር ሴራ መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው።
በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የታየው የተረኛ ጥበቃዎች ንቅናቄ የሚደነቅ ሲሆን፣ የወንጀሉ ተሳታፊዎች በሙሉ ለሕግ እንዲቀርቡ የጀመረው ክትትል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
Via ጉርሻ page

ትርፍ አንጀት ምንድን ነው?
በተለምዶ ትርፍ አንጀት እየተባለ የሚጠራው ችግር የሚከሰተው አፔንዲክስ (ትርፍ አንጀት) ሚባለው ትንሽ የአንጀት አካል ሲያብጥ ወይም ሲቆጣ ነው። ይህ ችግር በፍጥነት ካልታከሙ ሊፈነዳ እና አደገኛ ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል።
የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና ምንድን ነው?
የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና ትርፍ አንጀት ለማስወገድ የሚደረግ ቀዶ ጥገና ሲሆን ለትርፍ አንጀት ችግር በጣም የተለመደው ሕክምና ነው። ቀዶ ሕክምናው በክፍት (open) መንገድ ወይም በላፓሮስኮፒ ሊሰራ ይችላል።
🚨 የትርፍ አንጀት አደገኛ ምልክቶች፡
👉 ከታች በቀኝ በኩል ባለው የሆድ ክፍል ላይ ድንገተኛ እና ከባድ ህመም ፣
🔹ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ፣
🔹ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት፣
🔹 የምግብ ፍላጎት ማጣት እና
🔹 በእንቅስቃሴ የሚባባስ ህመም ሲኖር በፍጥነት ወደ ህክምና መሄድ ያስፈልጋል።
✨ የትርፍ አንጀት ቀዶ ህክምና ለምን ያስፈልጋል?
✅ ትርፍ አንጀት እንዳይፈነዳ እና
✅ ከባድ ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር እንዲሁም
✅ በፍጥነት ለማገገም ይህ ቀዶ ህክምና ያስፈልጋል።
ከቀዶ ጥገናው በኋላ ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
🔹 በቀላሉ ሊፈጩ የሚችሉ ምግቦችን መመገብ፣
🔹 ረጋ ያለ እንቅስቃሴ ማድረግ፣
🔹 እረፍት ማድረግ እና
🔹 ውሃ በደንብ መጠጣት ቶሎ ለማገገም ይረዳል።

5 days ago
አሜሪካ የዓመቱ ምርጥ መምህር ካለች በኋላ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸው ኢትዮጵያዊው መምህር
#ethiopia | በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ኢትዮጵያዊው ዶክተር በርሃኑ ገረሱ ክብረት ከአሜሪካ የፋርማሲ ኮሌጆች ማህበር የ"ዓመቱ ምርጥ መምህር" ሽልማት ተቀብለው በመመለስ ላይ እያሉ በዳላስ-ፎርት ዎርዝ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት እንደገለጸው ዶክተር በርሃኑ እ.ኤ.አ በሰኔ 2021 በሕጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ ቢሆንም የተቀመጠላቸው የቪዛ ጊዜ እ.ኤ.አ ግንቦት 31 ቀን 2024 ካበቃ በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ መቆየታቸውን ተከትሎ በኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ አስታውቋል።
የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ በሰጠው መግለጫ ድርጊቱ እጅግ እንዳሳሰበውና ዶክተር በርሃኑ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ የሚወደዱና ውጤታማ መምህር መሆናቸውን ገልጿል።
ከዚህ ቀደም በዊልያም ፓተርሰን ዩኒቨርሲቲ በሱሰኝነት መንስኤዎችና ሕክምና ዙሪያ በምርምር የሰሩት ዶክተር በርሃኑ ያለባቸው የቪዛ ስጋት በፍጥነት ተፈትቶ ወደ ተቋሙ ተመልሰው አጠቃላይ የማስተማርና የምርምር ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ ዩኒቨርሲቲው ተስፋ ማድረጉን አስታውቋል።

6 days ago
ከጋብቻ ውጭ የወለደችውን ልጅ በወላጆቿ ግቢ ውስጥ በድብቅ የቀበረችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች
በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ውስጥ ከጋብቻ ውጭ በጤና ተቋም በሰላም የተገላገለችውን ልጅ ወላጆቿ ግቢ ውስጥ በድብቅ የቀበረችው ግለሰብ በእስራት ተቀጥታለች።
የጮራ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር በለጠ ጉታ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ተከሳሽ ሙሚሻ ሱልጣን የአስራ ዘጠኝ አመት ታዳጊ ወጣት መሆኗን ገልጸዋል።
ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ በሰላም ከጤና ጣቢያ ልጇን ተገላግላ ወደ ቤት ስትገባ ወላጆቿ ከጋብቻ ውጭ በመውለዷ ባደረሱባት ቁጣ ተፅዕኖ ስር ወድቃ በነጋታው አስር ሰዓት ላይ የወለደችውን ጨቅላ ወንድ ልጅ አፍና ገድላዋለች። አስክሬኑን ካርቶን ውስጥ ሸሽጋ በማቆየት ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ማንም ሳያያት ልትቀብር ስትል በአካባቢው ማህረሰብ ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች።
የአራስ ልጇን አስክሬን ወደ ደልቢ ጤና ጣቢያ በመላክ ተከሳሿ ላይ አስፈላጊውን የምርመራ መዝገብ በሰውና በሕክምና ማስረጃ በማጠናከር ለአቃቢ ህግ ተላልፏል። አቃቢ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን መዝገብ ተመልክቶ በህፃን መግደል ወንጀል ክስ መስርቶባታል።
በአቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው የቡኖ በደሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሿ አስባ የፈፀመችው የወንጀል ድርጊት በመሆኑ በአስራ አምስት አመት እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን ኢንስፔክተር በለጠ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

7 days ago
ዜና እረፍት | ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ – የምሕረት፣ የጀግንነትና የአገር አገልግሎት ተምሳሌት አረፈች
#ethiopia | የኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ ፕሮፌሽናል ነርሶች መካከል አንዷ፣ የኮሪያ ጦርነት ዘማች፣ የቀይ መስቀል በጎ ፈቃደኛ እና ዓለም አቀፍ የነርስነት ክብር ተሸላሚ የነበሩት መቶ አለቃ ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ በ96 ዓመታቸው አርፈዋል።
ሲስተር ብርቅነሽ በአዲስ አበባ ከአቶ ከበደ ዘውገ እና ከወ/ሮ አልመዝ የግሉ ተወለዱ። ወላጆቻቸውን በለጋ ዕድሜያቸው በሞት ካጡ በኋላ፣ በአያታቸው ወ/ሮ ላቀች ጻታ እጅ አደጉ። የአባታቸው የአርበኝነት ታሪክ በመታሰቡ፣ በእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በነጻ እንዲማሩ እድል አግኝተዋል።
በኋላም በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሆስፒታል (አሁን የካቲት 12 መታሰቢያ ሆስፒታል) በነበረው የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የነርሶች ትምህርት ቤት ተምረው፣ ከሀገሪቱ የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ፕሮፌሽናል ነርሶች መካከል በክብር ተመርቀዋል።
በ1943 ዓ.ም. ከሦስተኛው ቃኘው ሻለቃ ጋር ወደ ኮሪያ በማቅናት፣ ከሁለት ጥቁር አፍሪካዊ ሴት ነርሶች አንዷ ሆነው ታሪክ ሠርተዋል። ከሲስተር አስቴር አያና ጋር በመሆን የኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ የቀይ መስቀል ዘማቾች በመሆን በተባበሩት መንግሥታት ሥር በኮሪያ ጦርነት ውስጥ ለወታደሮች ሕክምና እና ሰብዓዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። ከሕክምና ሥራቸው በተጨማሪ ለኢትዮጵያውያን ወታደሮች የትርጉም አገልግሎትም አበርክተዋል።
ከኮሪያ በኋላ በጃፓን ወታደራዊ ሆስፒታል እንዲሁም በኢትዮጵያ በክብር ዘበኛ ሆስፒታል፣ በጳውሎስ ሆስፒታል፣ በድሬዳዋና በአዲስ አበባ በሚገኙ የጤና ተቋማት ለብዙ ዓመታት በታማኝነት አገልግለዋል።
ለሰብዓዊ አገልግሎታቸው ዓለም አቀፍ ዕውቅና በማግኘት፣ በነርስነት ሙያ ከፍተኛ ክብር የሆነውን Florence Nightingale Award የተሸለሙ ጥቂት አፍሪካውያን ሴቶች መካከል አንዷ ሆነዋል።
የአገር አገልግሎታቸውን ለማክበር፣ እናት ባንክ በቦሌ ቡልቡላ የሚገኘውን አንድ ቅርንጫፍ በስማቸው ሰይሟል፤ ይህም ለሀገር ያበረከቱትን የማይረሳ አስተዋፅኦ የሚያሳይ የክብር ምልክት ነው።
መቶ አለቃ ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በ96 ዓመታቸው አርፈዋል። ከባለቤታቸው ከጄኔራል ደስታ ገመዳ ጋር ያፈሯቸውን አራት ልጆችና ስምንት የልጅ ልጆች ትተው አልፈዋል።
ሲስተር ብርቅነሽ ከበደ በጀግንነታቸው፣ በሰብዓዊነታቸው እና ለሀገራቸው ባበረከቱት አገልግሎት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለዘላለም የሚታወሱ ባለውለታ ሆነው ይኖራሉ።
ነፍሳቸውን በሰላም ያሳርፍ።
#tizbit Assefa

8 days ago
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን
– “ማንም የላት” ከተሰኘው የኅብረት ዜማ ጋር በተያያዘ
ከተመስገን ኡካሬ (የሐጌ ልጅ)
#ethiopia | "ማንም የላት" የተሰኘው የኅብረት ዜማ ሙዚቃ ብቻ አይደለም፤ የህሊና ጥሪ፣ የማህበራዊ ኃላፊነት ማንቂያ እና የሰብአዊነት መልዕክት ነው። ይህ ስራ የአካል ጉዳተኞችንና የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያላቸውን ወገኖች በርኅራኄ ከመመልከት ይልቅ፣ እንደ ሙሉ መብት ባለቤቶች እንድናያቸው ያስጠይቃል።
ሙዚቃው የሚያነሳው ዋና ጥያቄ አካል ጉዳተኝነት ሳይሆን፣ እኛ እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው የመዳረሻ እጥረት ነው። ትራንስፖርት፣ ትምህርት፣ ስራ፣ የህዝብ አገልግሎቶች እና ማህበራዊ ተሳትፎ ለሁሉም እኩል ተደራሽ ናቸው ወይ? የሚለውን ጥያቄ በጥልቅ ያቀርባል።
የኅብረት ዜማዎች ሁልጊዜም የዘመናቸውን ማህበራዊ ጉዳይ ያንጸባርቃሉ። "ማለባበስ ይቅር"፣ "ስደት"፣ "ሰላም ለሀገራችን" እና ሌሎችም እንደ ነበሩት ሁሉ፣ "ማንም የላት" ደግሞ የዚህ ዘመን የህሊና ጥሪ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ ስራ በስሜት ብቻ የተሞላ አይደለም፤ መፍትሄ የሚፈልግ ጥያቄ ያቀርባል። "ማንም የላት" የሚለውን አባባል "እኛም አለን" በሚል ተግባራዊ መልስ እንድንተካው ይጋብዘናል።
በዚህ ዜማ ላይ የተሳተፉት ድምፃዊ ማስተዋል እያዩ፣ ድምፃዊት ሀና ግርማ፣ ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) እና ድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ እያንዳንዳቸው መልዕክቱን በሚመጥን ስሜት አቅርበዋል።
ግጥሙን ናትናኤል ግርማቸው፣ ዜማውን አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ ቅንብሩን ደግሞ ታምሩ አማረ (ቶሚ) በሙያዊ ብቃት አስውበውታል። የግጥሙ፣ የዜማው፣ የድምፅ አቀራረቡና የቅንብሩ መዋሃድ ሙዚቃውን ከመዝናኛነት በላይ ወደ ማህበራዊ ንቅናቄ አሳድጎታል።
ይህ ዜማ የሚያስታውሰን አንድ እውነት አለ፤ ሰብአዊነት በቃላት ሳይሆን በተግባር ይለካል። አካል ጉዳተኞች ርኅራኄ አይፈልጉም፤ እኩል ዕድል፣ ተደራሽነትና ክብር ይፈልጋሉ።
ይድረስ ለአራቱ ድምፃውያን፤ ለህዝብ የሚያስብ፣ ህሊናን የሚያነቃ እና ማህበረሰብን ወደ በጎ ለውጥ የሚጋብዝ ስራ ስላቀረባችሁ ምስጋና ይገባችኋል። ይህ ዜማ በሙዚቃ ታሪክ ውስጥ እንደ ዜማ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ማህበራዊ ጥሪ የሚታወስ ስራ ይሆናል።
አቶ ሳሚ ተድላ ( የተድላ አምቡላንስ መሥራችና ባለቤት ) "ማንም የላት" የተሰኘው የኅብረት ዜማ ፕሮውዲሰር ምስጋና ይገባቸዋል።
በተለይም ጥበብንና በጎ አድራጎትን አጣምሮ በመያዝ፣ አቅም የሌላቸውንና ረዳት ያጡ ወገኖችን ድምፅ ለማሰማት ያደረጉት ጥረትና ያወጡት ወጪ የሚወደስ ነው።
በተጨማሪም በተድላ አምቡላንስ በኩል የሚያደርጉት ድገስ የሕክምና አገልግሎትና የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ ትልቅ አክብሮትና ምስጋና የሚያሰጣቸው ያደርጋቸዋል። እንደዚህ ያሉ በጎ አድራጊ ባለሃብቶችና ድርጅቶች ለሌላውም አርአያ የሚሆኑ ናቸው።

ሐዋሳ በከባድ ዝናብ ተመታች‼️
👉ጎርፍና ኃይለኛ ንፋስ ከዝናብ ጋር በቀጣይ ቀናቶችም ሊቀጥሉ ይችላሉ።
አሁን ባለው የክረምት ወቅት ሀዋሳን ጨምሮ በዙሪያዋ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እየጣለ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ባለስልጣን በሰጠው መረጃ መሠረትም የዝናቡ መጠን በቀጣዮቹ ቀናት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።
በከተማዋ እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ፣ በረዶና ኃይለኛ ንፋስ በአንዳንድ አካባቢዎች ዛፎችንና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በመጣሉ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አስከትሏል። በተጨማሪም በመሠረተ ልማት ላይ በደረሰ ውድመት ምክንያት በአንዳንድ የከተማዋ ክፍሎች የመብራት አገልግሎት ተቋርጧል።
የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ፤ በተጎዱ አካባቢዎች ፈጥኖ በመድረስ ተጎጂዎችን ወደ ሕክምና የማድረስና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በመለየት ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ ሥራዎችን አስጀምሯል።
በቀጣይም የክረምቱ ወቅት እስኪያልቅ ድረስ መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ፣ ጉዳቱን ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስችሉ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች ተጠናክረው እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በመሆኑም በቀጣዮቹ ቀናት ኃይለኛ ንፋስ የታጀበ ዝናብና የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስተዳደሩ ያሳስባል።
በተለይም ዛፎች፣ ያረጁ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እና አጥሮች ሊወድቁ ስለሚችሉ፣ በዝናብ ወቅት ከእነዚህ አካባቢዎች በመራቅ ራሳችሁንና ቤተሰቦቻችሁን እንድትጠብቁ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
ሐዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን

9 days ago
የ16 ዓመቱ ታዳጊ የ10 ዓመቱን ህጻን አዳነ፤
* በትራምፕ ሊሸለም ነው!
#ethiopia | በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኘው የሴንታ ክሩዝ ሲብራይት (Seabright) የባህር ዳርቻ የ16 ዓመቱ ታዳጊ ላይፍጋርድ ራይደር ዊሊያምስ በኃይለኛ ማዕበል ተወስዶ ለሞት የተጋለጠን የ10 ዓመት ህጻን በጀግንነት በማዳኑ በመላው አሜሪካ ትልቅ አድናቆት እያገኘ ነው።
በምስክሮች በተቀረጸው ቪዲዮ መሠረት፣ ህጻኑ በድንገት በተነሳ ኃይለኛ ማዕበል ወደ ባህሩ ከተወሰደ በኋላ ራይደር ሳይዘገይ ወደ ውሃው ዘልቆ በመግባት ህጻኑን አጥብቆ ይዞ ከተደጋጋሚ ከባድ ማዕበሎች ጋር በመታገል እስከ ዳርቻ ድረስ ማድረስ ችሏል። በኋላም ሌላ ላይፍጋርድ በመድረስ ህጻኑ በደህና ወደ ዳርቻ ተወስዶ በሕክምና ከታየ በኋላ ለወላጆቹ ተሰጥቷል።
የማዳኑ ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ ሚሊዮኖች ተመልካቾች ታዳጊውን "እውነተኛ ጀግና" በማለት ሲያወድሱት ታይቷል።
አባቱም ልጁ ከልጅነቱ ጀምሮ በውሃ ስፖርቶችና በላይፍጋርድ ስልጠና የተዘጋጀ መሆኑን ገልጾ፣ "ልጁን ፈጽሞ አልለቀቀውም" ብሏል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልእክት፣ ራይደርንና ቤተሰቡን እንዲሁም ያዳነውን ህጻን ወደ ነጩ ቤት በመጋበዝ ለታዳጊው "High Civilian Honor" የተባለውን ከፍተኛ የሲቪል ክብር ሽልማት እንደሚሰጡት አስታውቀዋል።
ራይደር ዊሊያምስ በበኩሉ፣ ይህ በቪዲዮ የተቀረጸው ማዳን ብቻ ሳይሆን በዚያው ቀን ከስራ በኋላ ሌሎች ሁለት ሰዎችንም ከአደገኛ ማዕበል ማዳኑን ገልጿል።
ሔኖክ ወ/ ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #america #lifeguard #ryderwilliams

አንድ ቤተሰብ… አንድ ሕይወት… የእኛን እርዳታ ይጠብቃል!
አቤል መለሰ በትምህርቱ የላቀ ውጤት ያስመዘገበ፣ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ በትጋት ሲዘጋጅ የነበረ ብሩህ ተማሪ ነበር።
ይሁን እንጂ ታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ሲመለስ፣ በፒያሳ ሀገር አቀፍ ቲያትር አካባቢ ከተገነባ ሕንፃ 13ኛ ፎቅ ላይ የወደቀ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ከባድ ቁስ በራሱ ላይ በመውደቁ ከባድ የራስ ቅል ጉዳት ደረሰበት።
በላንሴት ጠቅላይ ሆስፒታል የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ቢደረግለትም፣ ከአደጋው በኋላ ለ7 ወራት ያህል እስካሁን ድረስ በአልጋ ላይ ራሱን ስቶ ይገኛል።
መጀመሪያ የሕክምና ወጪውን የሸፈነው ተቋራጭ በኋላ ድጋፉን በማቋረጡ፣ ቤተሰቡ አሁን ከፍተኛ የሕክምና ወጪ ጫና ውስጥ ገብቷል።
ዛሬ አቤል ሕይወቱን ለማዳን የእኛን እገዛ ይሻል። 🙏
እባክዎ በሚችሉት መጠን ያግዙ። የእርስዎ ትንሽ ድጋፍ ለአቤል ትልቅ ተስፋ ሊሆን ይችላል።
የባንክ ሒሳብ (CBE)
እታለማሁ አሰፋው ወ/መድኅን (ወላጅ እናት)
1000348860538
+251-911-398024 / +251-931-534451
እባክዎ ይህን መረጃ SHARE በማድረግ ለብዙ ሰዎች ያድርሱ። ምናልባት የእርስዎ አንድ ሼር ወይም አንድ አስተዋጽኦ የአቤልን ሕይወት ለማዳን ወሳኝ ሊሆን ይችላል።
ፈጣሪ የሚረዱትን ይባርክ።
Via: ቤተሰቡ

10 days ago
ከውኃ ኃይል ባሻገር፤ የኢትዮጵያ አዲሱ የኒዩክሌር ኃይል ጉዞ እና የብልጽግና ተስፋ
****************
ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥት የኃይል አቅርቦትና ፍላጎቷን ለማመጣጠን ከውኃ እስከ ንፋስ፣ ከጂኦተርማል እስከ ፀሐይ ኃይል ማመንጫዎችን በመገንባት በአፍሪካ አህጉር ተምሳሌታዊ ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች።
ከጊቤ I እስከ ኮይሻ ያሉ ግዙፍ የውኃ ኃይል ማመንጫዎች እንዲሁም ከአባ ሳሙኤል እስከ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የተዘረጉት መሠረተ ልማቶች ማኅበረሰቡንና የአምራች ኢንዱስትሪዎችን በማንቀሳቀስ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም ሆነዋል።
ሆኖም ዘላቂ የኃይል ፍላጎትን በተወሰኑ አማራጮች ብቻ ማሟላት አዋጭ አለመሆኑን የተረዳው መንግሥት፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የኒዩክሌር ኃይል አስፈላጊነትን በመገንዘብ ስትራቴጂካዊ የኃይል አቅርቦት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ገብቷል።
የኒዩክሌር ቴክኖሎጂ እንደ ፀሐይና ንፋስ ከአየር ንብረት ጋር የማይቀያየርና በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን ያለማቋረጥ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው በመሆኑ ለትላልቅ ኢንዱስትሪዎች፣ ለአምራች ሴክተሮችና ለቴክኖሎጂ ማዕከላት የማይንቀሳቀስ መሠረት ይጥላል።
ይህ ቴክኖሎጂ ኤሌክትሪክ በሚያመነጭበት ወቅት ምንም ዓይነት የካርቦን ልቀት የሌለው በመሆኑ ለአየር ንብረት ለውጥ ትግልና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።
በተጨማሪም ከቅሪተ አካል ነዳጆች የዋጋ መዋዥቅና ጥገኝነት ነፃ የሚያደርግ ሲሆን፣ ከኃይል ማመንጨት ባለፈ በሕክምና፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና ውኃ ማጣራት እንዲሁም ለብዙ ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ አለው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈረንሳይ 70 በመቶ የኤሌክትሪክ ፍላጎቷን በኒዩክሌር በመሸፈን አነስተኛ የካርቦን ልቀት ማረጋገጥ ስትችል፤ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችም በዘርፉ ትልቅ ስኬት አስመዝግበዋል።
ኢትዮጵያም ይህንን ዓለም አቀፍ ተሞክሮ በመቅሰም ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል የኒዩክሌር ኃይል ፍኖተ ካርታ ቀርጻለች።
ሀገራችን በዘርፉ የተሻለ ልምድና ተሞክሮ ካለው የሩሲያው ሮሳቶም (Rosatom) ስቴት ኮርፖሬሽን ጋር ስትራቴጂካዊ ስምምነት ያደረገች ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ጠንካራ የደህንነት መሠረተ ልማትና የፋይናንስ ዝግጅት በማጠናከር ቴክኖሎጂውን ለኢንዱስትሪ፣ ለሕክምናና ለሳይንስ ዕድገት ለማዋል የጀመረችውን ጉዞ አጠናክራ ቀጥላለች።
በመሐመድ ፊጣሞ
#ethiopia #nuclearenergy #greeneconomy #sustainabledevelopment #energytransition

ኬንያ እና ኢትዮጵያ እየተማማሩ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ደረጀ ድጉማ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከኬንያ የሕዝብ ጤና እና ሙያዊ ደረጃዎች መምሪያ ዋና ጸሐፊ ሜሪ ሙቶኒ ጋር የምክክር ስብሰባ አካሄዱ።
የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ ኬንያ የእናቶችና ሕፃናትን ጤና ለማሻሻል በሰው ሰራሽ አስተዋጽኦ (AI) የታገዘ አልትራሳውንድ ቴክኖሎጂን (AI-POCUS) በመተግበር ረገድ ያካበተችውን ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ማጋራት ነው።
በስብሰባው ወቅት ኬንያ በዲጂታል ጤና ፈጠራ፣ በመልካም አስተዳደር እና የኤአይ አልትራሳውንድ አገልግሎትን በማስፋፋት ረገድ ያስመዘገበችው እድገት የቀረበ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ በመዘርጋት የእናቶችና ሕፃናትን ሕክምና ለማጠናከር ለምናደርገው ዝግጅት ትልቅ ጥቆማ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
ይህ ውይይት ኢትዮጵያና ኬንያ በዲጂታል ጤና መፍትሔዎች፣ በእውቀት ሽግግር እና በቀጣናው ጠንካራ የጤና ስርዓት በመገንባት የእናቶችና ሕፃናትን የጤና ሁኔታ ለማሻሻል ያላቸውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም ያረጋገጡበት ሆኖ አልፏል።

12 days ago
የመከላከያ የላቀ የላብራቶሪ ማዕከል እና 7ቱ ልዩ የምርምር ላቦራቶሪዎች
********************************
የሀገራችንን የመከላከያ አቅም በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በምርምር ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የተቋቋመው የመከላከያ የላቀ የላብራቶሪ ማዕከል በ7 ዋና ዋና ዘመናዊ የምርምር ዘርፎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ይገኛል።
ማዕከሉ ሀገራዊ የዲጂታል እና የመረጃ ደኅንነትን የሚጠበቅበት የሳይበር ደኅንነት፣ ዘመናዊ የኤአይ ቴክኖሎጂን የሚያበለጽገው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ የኃይል አቅርቦትን የሚያሳድገው የኤሌክትሪክ ኃይል፣ እንዲሁም የራስ-ሰር ሥርዓቶችን የሚያመርተው የአውቶሜሽን ላቦራቶሪዎችን አካቶ ይዟል።
በተጨማሪም የመገናኛና የራዳር ሥርዓቶችን የሚያለማው የኮሙኒኬሽንና ኤሌክትሮኒክስ፣ የቴክኖሎጂ አካላት ፈጣን ቅርፅ ማውጫ የሆነው የ3D ዲዛይንና ፕሮቶታይፕ፣ እና የሕክምና ተግባራዊ ልምምድ ማዕከል የሆነው የነርሲንግ ሲሙሌሽን ላቦራቶሪዎች በማዕከሉ ውስጥ ተካተው በከፍተኛ ቁርጠኝነት አገልግሎትና ምርምር በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ይህ የላቀ የቴክኖሎጂ ማዕከል ለሀገራችን የመከላከያ ሰራዊት ዘመናዊነት እና ለሀገራዊ ቴክኖሎጂ ዕድገት ታላቅ ምዕራፍ ነው።
#ethiopiandefense #defensetechnology #researchanddevelopment #ethiopia

ሞተር ከአይሱዚ ጭነት መኪና ጋር ተጋጭቶ ሁለት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው
#ቦንጋ | በካፋ ዞን ቢጣ ወረዳ ሸዳ ቀበሌ ውስጥ ባለሁለት እግር ሞተር ከአይሱዚ ጭነት መኪና ጋር በተፈጠረ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው።
በአደጋው የሞተር ሳይክሉ አሽከርካሪ እና ከኋላው ተሳፋሪ ሆኖ የነበረው ግለሰብ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ለተጨማሪ ሕክምና ወደ ቦንጋ ገብረፃዲቅ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የቢጣ ወረዳ ፖሊስ የትራፊክ አስተባባሪን ጠቅሶ የወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።
የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ በትራፊክ ፖሊስ እየተጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን በበኩሉ፣ ባለሁለት እግር ሞተር አሽከርካሪዎች የአደጋ መከላከያ ሄልሜት መጠቀም በአደጋ ጊዜ የጭንቅላት ጉዳትን ለመቀነስ እጅግ ወሳኝ መሆኑን በድጋሚ አሳስቧል።

14 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የማንቸስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ፣ የዓለም ዋንጫው ኮከብ እና የወርቅ ኳስ አሸናፊው ሮድሪ በቀጣዩ ሳምንት የወገብ ቀዶ ሕክምና እንደሚያደርግ ያረጋገጡ ሲሆን፣ ተጫዋቹ በኢቲሃድ ስታዲየም እንደሚቆይ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ሮድሪ ስፔይን በሰሜን አሜሪካ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ አርጀንቲናን 1-0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ሻምፒዮን ስትሆን የቡድኑ አጋፋሪ እና የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ መመረጡ ይታወሳል። በውድድሩ ወቅት 756 ስኬታማ ኳሶችን በማመቻቸት እና በርካታ ኳሶችን በመቀማት የቡድኑን የተከላካይ ክፍል በግንባር ቀደምትነት መርቷል።
የዓለም ዋንጫን፣ የአውሮፓ ሻምፒዮንነትን፣ አራት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን፣ የቻምፒዮንስ ሊግን፣ የባሎንዶርን እና ሌሎች በርካታ ዋንጫዎችን በስሙ ያጻፈው አማካይ፣ ኮንትራቱ ለመጠናቀቅ የመጨረሻ ዓመቱ ላይ በመድረሱ ወደ ማድሪድ በመመለስ ሪል ማድሪድን ሊቀላቀል ይችላል የሚሉ ዘገባዎች ሲወጡ ቆይተዋል።
ሆኖም አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ሮድሪ ማንኛውም አሰልጣኝ ሊያሰለጥነው የሚመኘው ድንቅ ተጫዋች መሆኑን ገልጸው፣ የዝውውር ጭ ወሬዎች በታላላቅ ተጫዋቾች ዙሪያ የተለመዱ በመሆናቸው ስጋት እንደሌላቸው ተናግረዋል።
አሰልጣኙ አክለውም ሮድሪ ሰኞ ዕለት ቀላል የወገብ ቀዶ ሕክምና እንደሚያደርግና ከቀዶ ሕክምናው በኋላ አስፈላጊውን ዕረፍት አድርጎ ወደ ቡድኑ እንደሚመለስ አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት ኦገስት 16 ከአርሰናል ጋር በሚደረገው የኮሚዩኒቲ ሺልድ ጨዋታ እና በፕሪሚየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ከቦርንመስ ጋር በሚደረገው ፍልሚያ ላይ የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።

15 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የማንችስተር ሲቲ እና የስፔን ብሔራዊ ቡድን አምበል ሮድሪ የጀርባ ጉዳቱን ለማከም ቀዶ ሕክምና ሊያደርግ መሆኑ ታወቀ። ስፔንን ለ2026 የዓለም ዋንጫ ድል የመራው እና የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች (ወርቅ ኳስ) ተሸላሚው የ30 ዓመቱ አማካይ፣ አዲሱ የ2026-27 የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በሚያደርገው በዚህ ቀዶ ሕክምና ምክንያት ለምን ያህል ጊዜ ከመጫወቻ ሜዳ ውጭ እንደሚሆን እስካሁን የተወሰነ ጊዜ የለም።
ሮድሪ በሴፕቴምበር 2024 የጅማት (ACL) ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ከራቀ ወዲህ በተደጋጋሚ በጉዳቶች ሲሰቃይ የቆየ ሲሆን፣ አዲሱ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት ይህ የጀርባ ቀዶ ሕክምና ማጋጠሙ ለማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ማሬስካ ትልቅ ስጋት ደቅኗል። በተጨማሪም ከተጫዋቹ ጋር የነበረው ኮንትራት አንድ ዓመት ብቻ የቀረው በመሆኑ የወደፊት አየር ላይ መንጠልጠል በማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል።

16 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የ25 ዓመቱ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን እና የአርሰናል ማዕከላዊ ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ በዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ የገጠመውን ጉዳት ለማከም ቀዶ ሕክምና (ቀዶ ጥገና) እንደማያስፈልገው ተረጋገጠ።
ሳሊባ ፈረንሳይ በስፔን 2 ለ 0 በተረታችበት የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ በጨዋታው የመጀመሪያ 30 ደቂቃዎች ውስጥ በጉዳት ምክንያት ለመቀየር መገደዱ ይታወሳል። ተጫዋቹ በውድድሩ ላይ ከአንድ ጨዋታ ውጭ በሁሉም ጨዋታዎች በቋሚነት ተሰልፎ ተጫውቷል።
ክለቡ አርሰናል ባወጣው መግለጫ ተከላካዩ ቀዶ ሕክምና የማያደርግ ቢሆንም ለተወሰነ ጊዜ ግን ከመጫወቻ ሜዳ ውጭ ሆኖ የሕክምናና የእረፍት ጊዜ እንደሚያሳልፍ አረጋግጧል።

17 days ago
ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ታጥረው የተተዉ መሬቶች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቁ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ታጥረው ያለምንም አገልግሎት የተቀመጡ መሬቶችን በማጣራት በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
ከንቲባዋ ይህን ያስታወቁት፣ በከተማ አስተዳደሩ የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድና የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው።
እንደ ከንቲባዋ ገለጻ፣ አዲስ አበባ መሬት ታጥሮ የሚቀመጥባት ከተማ መሆን እንደሌለባት ቀደም ሲል የተደረሰውን ስምምነት የሚጥሱ አካላት ተጨማሪ ዕድል እንደማይሰጣቸው አስጠንቅቀዋል።
በሌላ በኩል፣ በከተማዋ የሰላምና ደህንነት ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን በመግለጽ፣ በርካታ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶች ያለ የደህንነት ችግር በሰላም መጠናቀቃቸውን አስታውሰዋል።
በተጨማሪም፣ የከተማዋ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት መዘመኑ ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰው፣ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጥናት መሠረት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በአፍሪካ ከተመረጡ ስድስት ምርጥ ከተሞች መካከል በአሠራር ደረጃ አንደኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አክለውም፣ በጤናው ዘርፍ የሕክምና ባለሙያዎች የሙያ ሥነ-ምግባርና የአገልግሎት ጥራት መሻሻሉን፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የጤና አገልግሎትና የመሠረተ ልማት ሥራዎችም ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነጻጸሩ በእጥፍ መጨመራቸውን ገልጸዋል።

20 days ago
ኩዌት የኢራንን ጥቃት ተከትሎ በርካታ የእሳት አደጋ ሠራተኞች መጎዳታቸውን አስታወቀች
የኩዌት እሳት አደጋ መከላከያ ቅዳሜ ዕለት የተፈጸመውን የኢራን ጥቃት ተከትሎ የተቀሰቀሰ እሳትን ለማጥፋት የተሰማሩ በርካታ ሠራተኞች ጉዳት እንደ ደረሰባቸው አስታወቀ።
"የመጀመሪያው ክስተት እሳቱን ለማጥፋት ሲጥሩ የነበሩ የእሳት አደጋ ተከላካዮች እና አንድ ሲቪል ሠራተኛ ላይ በርካታ ጉዳቶችን አድርሷል" ሲል ድርጅቱ በመንግሥት ለሚተዳደረው የዜና ወኪል ኩና ተናግሯል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት አካባቢ የነበሩ ሰዎች አካባቢውን እንዲለቅቁ የተደረጉ ሲሆን፣ የቆሰሉት ሰዎች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሕክምና ተቋም ተወስደዋል ሲል ጨምሮ ገልጿል።
የኩዌት ኤሌክትሪክ፣ ውሃ እና ታዳሽ ኃይል ሚኒስቴር፣ በኃይል ማመንጫው እና በውሃ ማጣሪያው ላይ ኢራን የፈጸመችወን ጥቃት ተከትሎ እሳት መቀስቀሱን አስታውቆ ነበር።
አሜሪካ ለሰባት ተከታታይ ሌሊት ጥቃት የፈጸመች ሲሆን ኢራንም በምላሹ የዩኤስ ጦር ኃይል መቀመጫ የሆኑ የቀጣናው አገራት ላይ ጥቃት ሰንዝራለች።
በዋሺንግተን እና ቴህራን መካከል ዳግም ጦርነት ያገረሸው በፓኪስታን አደራዳሪነት የተፈረመው የሰላም ስምምነት ውድቅ ከሆነ በኋላ ነው።
BBC

21 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ማንቸስተር ዩናይትድ ለአዲሱ የውድድር ዘመን ዝግጅት የሚያደርገውን የመጀመሪያ የቅድመ-ውድድር የወዳጅነት ጨዋታውን በፊንላንድ መዲና ሄልሲንኪ ከሬክስሃም ጋር ሊያደርግ መሆኑን በይፋዊ መጽሔቱ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል። ይህ ጨዋታ ነገ ቅዳሜ ከቀኑ 10፡00 ላይ የሚጀመር ሲሆን፣ ክለቡ በዚህ በጋ የሚያደርጋቸውን ሁሉንም ጨዋታዎች በክለቡ የቪዲዮ ቻናል አማካኝነት በቀጥታ እንደሚያስተላልፍ ገልጿል።
የማንቸስተር ዩናይትድ የሚዲያ ቡድን ከስፍራው ባጠናቀረው ዘገባ መሠረት፣ በነገው ጨዋታ ዙሪያ ትኩረት የሳቡ ዋና ዋና ነ 3 ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
1ኛ. የአዲሱ ፈራሚ አንድሬ ሳንቶስ የመጀመሪያ ጨዋታ ጉጉት
በዚህ በጋ ከሌላው የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ቼልሲ የተዛወረው ብራዚላዊው አማካኝ አንድሬ ሳንቶስ፣ ከክለቡ ጋር ለአንድ ሳምንት ልምምድ ካደረገ በኋላ ከቡድኑ ጋር ወደ ሄልሲንኪ መጓዙ ተረጋግጧል። በመሆኑም ነገ በቀይ ማልያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል ወይ የሚለው የብዙዎች ጉጉት ሆኗል። በሌላ በኩል፣ ሌላኛው አዲስ ፈራሚ ዩሪ ቲሌማንስ ከቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ጋር በፊፋ የዓለም ዋንጫ ላይ ከነበረው ተሳትፎ በኋላ እረፍት ላይ በመሆኑ እንዲሁም ግብ ጠባቂው ካርል ዳርሎው ካደረገው የሕክምና ክትትል እያገገመ በመሆኑ ከቡድኑ ጋር አልተጓዙም።
2ኛ. የአካዳሚ ወጣቶች እና አንጋፋ ተጫዋቾች ጥምረት
በአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ በሚመራው በዚህ ስብስብ ውስጥ እንደ ብራያን ምቤውሞ፣ ሉክ ሾው እና ፓትሪክ ዶርጉ ያሉ የዋናው ቡድን ቁልፍ ተጫዋቾች የተካተቱ ቢሆንም፣ በርካታ የታዳጊ ቡድን (አካዳሚ) ተሰጥኦዎችም ዕድል ለማግኘት አብረው ተጉዘዋል። ባለፈው የውድድር ዘመን በስኮትላንዱ ሴንት ሚሬን በውሰት ያሳለፈው የ19 ዓመቱ አማካኝ ጄኮብ ዴቫኒ፣ እንዲሁም ጄዳን ካማሰን፣ ጂም ትዋይትስ፣ ዳን አርመር እና ኤታን ዊሊያምስ ለአዲሱ የውድድር ዘመን በአሰልጣኙ አእምሮ ውስጥ ቦታ ለማግኘት ነገ ዕድል ሊሰጣቸው እንደሚችል ይጠበቃል። በተጨማሪም ቺዶ ኦቢ፣ ሺ ላሴ እና ሃሪ አማስ በቡድኑ ውስጥ ተጨማሪ የመጫወቻ ጊዜ ለማግኘት የሚፎካከሩ ይሆናል።
3ኛ. የግብ ጠባቂዎች መስመር ፈተና እና አዲስ ዕድል
የክለቡ ግብ ጠባቂዎች የነበሩት ሴኔ ላመንስ እና አልታይ ባይንድር ከዓለም ዋንጫ ተሳትፏቸው በኋላ እረፍት ላይ በመሆናቸው እና አንድሬ ኦናና በውሰት ወደ ትራብዞንስፖር በማንቀሳቀሱ፣ አንጋፋው ቶም ሄተን ቡድኑን በዋና ግብ ጠባቂነት እየመራ ይገኛል። ሄተን ውሉን እስከ 2026/27 የውድድር ዘመን ማጠናቀቂያ ማራዘሙ ይታወቃል። ሆኖም አሰልጣኝ ካሪክ ለወጣቶቹ ደርሞት ሚ እና ራዴክ ቪቴክ ዕድል ሊሰጣቸው ይችላል። በተለይም ቪቴክ ባለፈው የውድድር ዘመን በብሪስቶል ሲቲ በውሰት ቆይታው የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን ጠራርጎ በመውሰድ ያሳየው ድንቅ ብቃት፣ ነገ በማንቸስተር ዩናይትድ ማልያ በሚያሳየው አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል።

Comments