Logo
Getu Temesgen
“ የሲዳማ ቡና ይግባኝ ተቀባይነት አላገኘም “ የኢ/እ ፌዴሬሽን
#ethiopia | ሲዳማ ቡና ለአለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አሰራር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የፋይናንስ መመሪያን ተላልፈው የተገኙ ክለቦች እና ተጨዋቾች ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ ማፅናቱ ይታወሳል።

ክለቦቹ በበኩላቸው ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድቤት በመውሰድ የተጫዋቾቹን እግድ አስነስተናል በሚል ተጨዋቾቹን መጠቀም ቀጥለው ነበር።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ የኢትዮጵያ ዋንጫን ጨምሮ ክለቦቹ ያልተገቡ ተጫዋቾችን ያሰለፉባቸው ጨዋታዎች በሙሉ በፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆኑ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጉዳዩን ወደ ዓለምአቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድቤት (CAS) በመውሰድ ይግባኝ ጠይቋል።

ሲዳማ ቡና የክስ ሂደቱ በሚታይበት ወቅት የፌዴሬሽኑ ውሳኔ በጊዜያዊነት እንዲታገድ ያቀረበውን ጥያቄ የካስ (CAS) የይግባኝ ግልግል ክፍል ተመልክቶ በምክትል ፕሬዘዳንቱ በኩል በወጣ ደብዳቤ ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረገ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል። #ts #sport #gtmc

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.