Logo
Ethio telecom
በበጀት ዓመቱ ከ17.18 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የቴሌብር ደንበኞች እስከ 35.04 ቢሊዮን ብር የአነስተኛ ብድር አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷል

ኩባንያችን በ“ቀጣዩ አድማስ” ስትራቴጂ ሁለተኛ ዓመት በቴሌብር አማካኝነት የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የዲጂታል ኢኮኖሚ ሥነ-ምህዳሩን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን ያከናውናል።

በአዲሱ 2019 በጀት ዓመት የቴሌብር ደንበኞች ቁጥርን በ11.7 በመቶ በማሳደግ 67.69 ሚሊዮን ለማድረስ አቅዷል።

የቴሌብር አጠቃላይ የግብይት ብዛት (Transaction Volume) 4.99 ቢሊዮን ለማድረስ የታቀደ ሲሆን፣ ይህም 7.4 ትሪሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብ ፍሰት በዲጂታል ሥርዓቱ ውስጥ ለማንቀሳቀስ ያስችላል።

የአነስተኛ ብድር አገልግሎት ከ17.18 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ደንበኞች 35.04 ቢሊዮን ብር ለመስጠት ታቅዷል። ይህም ለግለሰቦችና ለአነስተኛ ንግዶች የዲጂታል ብድር አገልግሎቶች ተደራሽነት መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

የዲጂታል ቁጠባ መጠን ወደ 29.39 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ የታቀደ ሲሆን፤ ይህም ለ3.88 ሚሊዮን ደንበኞች የፋይናንስ ደኅንነትን የሚፈጥርና የቁጠባ ባህልን የሚያሳድግ ነው።

ቴሌብር የሀገራችንን ዲጂታል ፋይናንስ አካታችነት እና የዲጂታል ሥነ-ምህዳር አንቀሳቃሽ ሞተር በመሆን የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ማፋጠኑን አጠናክሮ ይቀጥላል።

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3UvAR5j
#ethiotelecom #telebirr #nexthorizon #digitalethiopia #digitalafrica #gsma #itu #worldbank #oecd #g6countries #hopr #hof

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.