Logo
Getu Temesgen
አሜሪካ 8 ስደተኞችን ከጅቡቲ ደቡብ ሱዳን ወደሚገኘው የጦር ሰፈሯ ማዛወሯን የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር አስታወቀ
#ethiopia | የቬትናም፣ ኩባ፣ ላኦስ፣ ሜክሲኮ እና ማይናማር ዜግነት ያላቸው ወንጀለኞች፤ በጅቡቲ የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ የሕግ ሂደት ከጨረሱ እና ከሳምንታት እስራት በኋላ እንዲወጡ መደረጋቸውን መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ግለሰቦቹ አሜሪካ ውስጥ የግድያ፣ ፆታዊ እና የአደንዛዥ ዕፅ ወንጀል እስረኞች የነበሩ ሲሆን የትውልድ ሀገሮቻቸው ሊቀበሏቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ወደ ደቡብ ሱዳን የተዛወሩት።

እርምጃው የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተወሰኑ ስደተኞች ወደ ሦስተኛ ሀገራት እንዲዛወሩ (ዲፖረት እንዲደረጉ) በውሳኔው መፍቀዱን ተከትሎ የመጣ ነው። የታችኛው ፍርድ ቤት የፍትሕ ሂደቱን አልተከተለም በማለት ስደተኞቹን ማስወጣት በማገድ ለታሳሪዎች ከአንድ ቀን ያነሰ የይግባኝ ጊዜ ሰጥቶ ነበር።

ትራምፕ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን በማስወጣት ስደት እንደሚያስቆሙ በበዓለ ሲመታቻው ወቅት ቃል ገብተዋል። አስተዳደራቸው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ ትውልድ ሀገራቸው ወይም ወደ ሦስተኛ ሀገራት ለመላክ እንዳቀደ ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡ #sputnik

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.