Logo
Getu Temesgen
በፌደራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ሊጀምር ነው
#ethiopia | ​የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን ሥራ በጀመሩት አምስት የፌደራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ2019 የትምህርት ዘመን ተጨማሪ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

​የተማሪዎች ምዝገባ በቅርቡ እንደሚጀምር የጠቆመው ሚኒስቴሩ፣ የምዝገባ መስፈርቶችን፣ የተወሰነውን ጊዜ እና ሌሎችንም ዝርዝር መረጃዎች በቀጣይ በይፋ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጻል።

በመሆኑም ፍላጎቱ ያላቸው ተማሪዎች፣ ወላጆች እና አሳዳጊዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠባበቁና የትምህርት ሚኒስቴርን ኦፊሴላዊ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እንዲከታተሉ ጥሪ አስተላልፏል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.