Logo
FastMereja
ያለ ንብረት ማስያዣ ብድር የሚሰጠው «ኪሴ» ፕላትፎርም በይፋ ሥራ ጀመረ!
#fastmereja I አሪፍፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ አ.ማ፣ ኤምዚ ቴክ እና መፍትሔ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ በመተባበር «ኪሴ» የተሰኘ አዲስ በወኪሎች (Agents) የሚመራ የዲጂታል ጥቃቅን ብድር ፕላትፎርም በዛሬዉ እለት በይፋ አስተዋወቁ።

ይህ የሦስትዮሽ አጋርነት በሀገራችን በአነስተኛና ጥቃቅን ንግዶች ዘርፍ የሚታየውን የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ የታለመ ሲሆን፤ ያለ ምንም መደበኛ ንብረት ማስያዣ(Collateral-free) በህብረተሰቡ ዘንድ ባለው ማህበራዊ እምነት እና የዕለት ተዕለት ግንኙነት ላይ በመመስረት አገልግሎቱን ተዳራሽ እንደሚደረግ ነዉ የተገለፀዉ።

መፍትሔ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ፦ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተመዘገበ ሕጋዊ አበዳሪ ተቋም በመሆን የብድር ካፒታሉንና የፋይናንስ አቅርቦቱን ያመቻቻል።ኤምዚ ቴክ (MZ Tech)፦ የ«ኪሴ» ፕላትፎርም ልማትና የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቱን ያበለጸገ ሲሆን፣ ሀገር አቀፍ የወኪሎችን መረብ ይመራል።አሪፍፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ አ.ማ፦ በሀገር አቀፍ የክፍያ መደቡ (Payment Gateway) አማካኝነት የብድር መውጫ፣ የመልስ ክፍያ ዝውውር እና የዲጂታል ክፍያ ሂደቶችን ያመቻቻል።

ተበዳሪዎች በአካባቢያቸው በሚገኙ የሰለጠኑ ወኪሎች አማካኝነት ለአጭር ጊዜ የንግድ ብድር ማመልከት እንደሚችሉ የተጀለፀ ሲሆን ማመልከቻው በመፍትሔ ማይክሮፋይናንስ እንደተጸደቀም፣ በአሪፍፔይ የክፍያ መስመር በኩል በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በቀጥታ ወደ ደንበኛው የሞባይል ዋሌት ወይም የባንክ ሂሳብ ገቢ እንደሚደረግ ተገልጿል።

መድረኩ የብድር ብቃትን ለመመዘን አማራጭ መረጃዎችን (Alternative Data) በመጠቀሙ፣ መደበኛ የፋይናንስ ሰነድ ወይም መያዣ የሌላቸውን ስራ ፈጣሪዎችና አነስተኛ ነጋዴዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፤ የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

21 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.