Logo
SeledaPost
#update

በሶማሊ ክልል በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ 12 ሰዎችን ለመቅበር የሄዱ ሶስት ሰዎች በአፈር መደርመስ ህይወታቸው አለፈ

በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ በተከሰተ ከባድ የመኪና አደጋ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል። አደጋው ሊከሰት የቻለው እሁድ ረፋድ ሶስት ሰዓት ላይ አንድ የአይሱዚ መኪና «ፎርስ» ተብሎ ከሚጠራ ሌላ ተሽከርካሪ ጋር በድንገት በመጋጨቱ ሲሆን በዚሁ አሳዛኝ አጋጣሚ የ12 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ አልፏል።

በተጨማሪም በአደጋው ሦስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።የደረሰውን የትራፊክ አደጋ ተከትሎ በቀብር ላይ በነበሩ ወገኖች ላይ የመቃብር ቦታ አፈር ተደርምሶ ተጨማሪ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ  ከ10 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ገልጿል ።

ቢሮዉ ባወጣዉ መግለጫ ህይወታቸውን ያጡትን ወገኖች ለመቅበር እየተደረገ በነበረ የቀብር ሥነ ሥርዓት ደግሞ ሌላ አሳዛኝ ክስተት ማጋጠሙን ገልጿል ። የቀብር ስነስርአት በመፈፀም በነበሩ ሀዘንተኞች ላይ የመቃብር ቦታ በመደርመሱ ህይወታቸውን ካጡት 3 ሰዎች በተጨማሪ ከ10 በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

Seledadotio
Seledadotio
21 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.