Logo
Getu Temesgen
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መስማት የተሳናቸውን የሚያመለክት የትራፊክ ምልክት ተመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መስማት የተሳናቸውን ሰዎች የሚያመለክት አዲስ የትራፊክ ምልክት በይፋ ተመርቋል። ይህ እርምጃ መስማት የተሳናቸው ዜጎች በትራፊክ አደጋ እንዳይጋለጡ እና የመንገድ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ያለመ ነው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የተደረገውን የመክፈቻ ንግግር ያቀረቡት የDCDO ስራ አስኪያጅ አቶ ናትናኤል ሽፈራው፣ ይህ ቀን መስማት የተሳናቸው ዜጎች በሀገሪቱ የትራፊክ ደህንነት ሥርዓት ውስጥ በይፋ የተካተቱበት ታሪካዊ ዕለት መሆኑን ገልጸው፣ ለሁሉም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

አዲሱ የትራፊክ ምልክት በተለይ በመስማት የተሳናቸው ሰዎች የሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች አሽከርካሪዎች ተጨማሪ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ ፍጥነታቸውን እንዲቀንሱ እና የሚደርሱ አደጋዎችን በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ ይጠቅማል ተብሏል። በመሆኑም ምልክቱን ለሕዝብና ለአሽከርካሪዎች በስፋት ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።

የምረቃ ፕሮግራሙም በፓናል ውይይት፣ በግጥም፣ በሰርከስ ትርኢት፣ በደም ልገሳ፣ በባዛር እና በሌሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅቶች ታጅቦ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #roadsafety #trafficsafety #inclusivetransport #deafcommunity #trafficsigns #roadsafetyawareness

21 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.