ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ማግስት፦ የነገዋ ኢትዮጵያ አቅጣጫ እና ከመንግሥት የሚጠበቁ ኃላፊነቶች
***************************
የዘንድሮው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
ምርጫውን አሸንፎ መንግሥት የሚመሰርተው ፓርቲ የሕዝብን አደራ ተቀብሎ ሀገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ የማሻገር ከባድ ኃገራዊ ኃላፊነት ይወድቅበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ መድረኮች ባስተላለፏቸው መልዕክቶች፣ የፓርላማውን አብላጫ ድምጽ በማግኘት መንግሥት የሚመሰርተው ፓርቲ ድርብ ኃላፊነት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሻገር የተጀመሩ እና በዕቅድ የተያዙ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በተሻለ ሁኔታ መፈጸም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ከእነዚህ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
ሰብዓዊነትን ማዕከል ያደረገ አመራር እና የጸጥታ ተቋማት ግንባታ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ "ሰብዓዊነትን ማዕከል ያደረገ አመራር" አስፈላጊነትን ደጋግመው አንስተዋል።
አዲስ የሚመሰረተው መንግሥትም ይህን መርህ በተግባር በመተርጎም የዜጎችን ደኅንነት እና ሰላም ማስቀደም ይጠበቅበታል።
የጸጥታ እና የደኅንነት ተቋማትን ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆኑ፣ ዘመናዊ እና ሕዝብን የሚያገለግሉ አድርጎ የመገንባቱ የሪፎርም ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሠራ ቆይቷል። ይህ አሁንም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
የዜጎች ደኅንነት በእኩልነት ሲረጋገጥ እና የጸጥታ መዋቅሩ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ መብት ለማስጠበቅ ሲቆም ብቻ ሀገራዊ መረጋጋትን እና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን ማሳካት ይቻላል።
ጎረቤትን ያስቀደመ ዲፕሎማሲ እና ቀጣናዊ ትስስር
በውጭ ግንኙነት ረገድ አሸናፊው ፓርቲ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ሥራ መሥራት ይኖርበታል።
መንግሥት የሚከተለውን ጎረቤት ተኮር የዲፕሎማሲ ስትራቴጂ ይበልጥ በማጠናከር ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስር ውስጥ ያላትን የመሪነት ሚና ማስቀጠል ይጠበቅበታል።
ከዚህም ባሻገር ለመካከለኛው ምሥራቅ እና ለባሕረ ሰላጤው ጂኦፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች የቅርብ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል።
በቀጣናው ሊፈጠሩ የሚችሉ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን የሚቋቋም ሚዛናዊ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን መተግበር በቀጣይ ከመንግሥት የሚጠበቅ ወሳኝ ኃላፊነት ነው።
የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ
አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት ሌላው ትልቅ ኃላፊነት ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን ማረጋገጥ ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በማስፋት የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ከማሳደግ ባለፈ፣ ሀገራችን ከካርበን ንግድ ተጠቃሚ የምትሆንበትን "የአረንጓዴ ወርቅ" የኢኮኖሚ ሥርዓት መገንባት ይገባዋል።
ይህ አካሄድ የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባሻገር፣ አዲስ የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ አቅም በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል።
የሀገራዊ ምክክር ውጤትን ተግባራዊ ማድረግ
አዲሱ መንግሥት ትልቅ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ጉዳዮች መካከል የሀገራዊ ምክክሩን ውጤት ተቀብሎ ወደ ተግባር መቀየር ቀዳሚው ነው።
የምክክሩ ውጤት የነገዋን የበለጸገች እና የተረጋጋች ኢትዮጵያን ለመገንባት ጠንካራ መሰረት የሚጥል ነው።
የምክክሩ ውጤት የሕግ የበላይነት የነገሰባት፣ ሰብዓዊ መብቶች ይበልጥ የሚከበሩባት እና የተጠናከረ የፍትሕ ሥርዓት የተረጋገጠባት ሀገር ለመገንባት ወሳኝ ግብዓት ነው።
የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም
ኢትዮጵያ የተገበረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤታማነቱ እየታየ ይገኛል። በዚህም ኢትዮጵያ በዘንድሮው በጀት ዓመት ማጠቃለያ የ10.2 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደምታስመዘግብ ይጠበቃል።
የመንግሥት ቀጣዩ ዋና ሥራ ይህ ዕድገት ወደ እያንዳንዱ ዜጋ ሕይወት እንዲወርድ ማድረግ ነው።
ለዚህም የዋጋ ንረትን መቆጣጠር፣ የኑሮ ውድነትን ማቃለል እና የውጭ ብድር ጫናን ማስተካከል ከአዲሱ መንግሥት የሚጠበቁ እና ፈጣን ምላሽ የሚሹ አንገብጋቢ የቤት ሥራዎች ናቸው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopia #economicreform #macroeconomy #diplomacy #greenlegacy #ebc

1 month ago