የድምፃዊት ፅላት ገዝሙ አዲስ የሙዚቃ አልበም ስኬት በሚል ርዕስ ለክብረ በዓል ሊበቃ ነው
#ethiopia | ታዋቂዋ እና ተወዳጅዋ ድምፃዊት ፅላት ገዝሙ አድማጮቿ ለበርካታ ዓመታት በጉጉት ሲጠብቁት የነበረውን አዲስ የሙዚቃ አልበም በቅርቡ ለህዝብ እንደምታቀርብ ይፋ አደረገች።
የ2018 ዓ.ም የኦዳ አዋርድ ተሸላሚ የሆነችው ድምፃዊት ፅላት ገዝሙ፣ ስኬት የሚል መጠሪያ የሰጠችውን ይህንን አዲስ አልበም ያዘጋጀችው በአስር የሙዚቃ ስራዎች አጅባ ነው።
ለአልበሙ መሳካትም በአጠቃላይ የ12 ዓመታት ረጅም የዝግጅት እና የጥበብ ስራ ጊዜ እንደፈጀበት ተገልጿል።
ድምፃዊቷ ዛሬ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጸችው፣ ህዝብ ለረጅም ጊዜ ሲጠብቀው የነበረው ይህ ስራ መጪው አርብ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ለአድማጮች ይሰራጫል።
አልበሙ በዕለቱ በድምፃዊቷ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል እንዲሁም ዞጃክ ዎርልድ ዋይድ በተሰኘው ዓለም አቀፍ የሙዚቃ አከፋፋይ ድርጅት አማካኝነት በመላው ዓለም በአንድ ጊዜ ለተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ታውቋል።
በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቋንቋዎች ባቀረበቻቸው ስራዎቿ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈችው ፅላት ገዝሙ፣ በአዲሱ አልበሟ ውስጥ የተካተቱት አስሩም ዜማዎች የኪነ ጥበብ ጉዞዋን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ እና ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶባቸው የተሰሩ መሆናቸውን አብራርታለች።
#tsilatgezmu #music #newalbum #ethiopianmusic #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago