Logo
EBC
የመደመር አንቀጽ

ትውልድ የተቀራራቢ ዕድሜ ስብስብ ነው። ዕድሜ አንድ ሰው የኖረበት ወይም አንድ ከሥተት የቆየበት የጊዜ ርዝማኔ ነው። በዚህ የቆይታ ርዝማኔ ውስጥ የሰው ልጅ በተለያዩ የዕድገት ደረጃዎች ወይም የለውጥ ሂደት ውስጥ ያልፋል።

በትውልድ ፍሰት ውስጥ እያንዳንዱ ሰው የመጪው፣ የዛሬው ወይንም ያለፈው ትውልድ አባል ተብሎ ሊቆጠር ይችላል። ትውልድ ሕዝብን በዕድሜና በዘመን ከፋፍሎ የመመልከቻ መነጽርነው።

ግለሰብን የትውልድ አባል ከሚያደርጉት የትውልድ መገለጫዎች መካከል ዕድሜ አንዱ ነው። የአንድ ትውልድ አባላት የተቀራራቢ ዕድሜ ባለቤቶች ናቸው። ከሞላ ጎደል ልጅነታቸው፣ ወጣትነታቸው፣ ጉልምስናና እርጅናቸው በተቀራራቢ ወቅት የተፈጸመ ነው።

አንድ ትውልድ የተቀራራቢ ዘመን ተጋሪ ነው። ትውልድን ያለ ዘመን መግለጽ አይቻልም። ዘመን አንድ ትውልድ ተወልዶ፤ ዕድሜውን ኖሮ፤ ለቀጣዩ ትውልድ ዐሻራ ጥሎ፤ የሚያልፍበት የጊዜ ቁራጭ ነው።

አንድ ትውልድ ለአንድ ወቅት እንጂ ለዘላለም አይኖርም። ወቅት ሲባል ካለፈው ትውልድ የተወረሰው መልካም ጉዳዮችና ችግሮች ያሉበት፤ ለቀጣዩ ትውልድ ዐሻራችንን የምናሳርፍበት፤ ተወልደን ኖረን የምንሞትበት የዘመን ሰሌዳ ነው።

እንደ ዕድሜያችን ተማሪ፣ መሪ፣ መካሪ፣ ወዘተ የምንሆንበት ወቅት የተለያየ ነው።

የመደመር ትውልድ
ገጽ - 9

Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #generations #መደመር #የመደመርትውልድ

11 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.