Logo
EBC
የመደመር አንቀጽ

በየዘመኑ የሚፈጠሩ ከሥተቶችና ለውጦች በዘመናት መካከል በሰዎች ምልከታዎችና እሳቤዎች ላይ ለውጥ ይፈጥራሉ። አንድ ዘመን የሚጋሩ በተመሳሳይ ክሥተቶች ውስጥ ያለፉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ትውልድ ይባላሉ፡፡

ትውልድ ማለት በትናንት፣ በዛሬ እና በነገ ጊዜ ቀመር ውስጥ ተፈጥረው ባለፉ፣ አሁን በሚኖሩና ገና በሚፈጠሩ ሰዎች መካከል ያለ ልዩነትን ለመግለጽ የምንጠቀምበት ብያኔ ነው፡፡

በአጠቃላይ እያንዳንዱ ትውልድ ራሱን የቻለ ማንነቱ የሚገለጽበት እሴቶችና ልማዶች እንዲሁም ሌሎች የጋራ ጠባዮች አሉት። እነዚህም የጋራ ጠባዮች ከዕድሜ ማዕቀፉና ካለፈበት ታሪካዊ ኹነቶች ጋር ተዳምረው፤ ከሌላው ትውልድ የተለየ እንዲሆን ያደርገዋል።

እያንዳንዱ የትውልድ አባል አንድ ዘመንን፣ ተመሳሳይ የሕይወት ልምድና ታሪካዊ ኹነቶችን ተጋርቶ የሚያልፍ ስለሆነ ተቀራራቢነት ያለው ጠባይ የሚያንጸባርቅ ነው።

በመሆኑም አንድን ትውልድ ለመረዳትና ከሌላው ትውልድ የሚለይበትን ቁም ነገሮች ለመገንዘብ፤ አራት ጉዳዮችን መመልከት ያስፈልጋል።

እነዚህም የዕድሜ ክልል ወይም የትውልድ ዘመን፣ የጋራ ኹነቶችና ለውጦች፣ በዘመኑ ተቀባይነት ያለው የጋራ ዕይታ (ፓራዳይም) እና ተመሳሳይ ጠባይ ናቸው፡፡

የመደመር ትውልድ
ገጽ - 8 #ebc #ethiopia #ebcdotstream #medemer Ethiopian Broadcasting Corporation #generations

3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.