የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዩጋንዳን የኢቦላ ምላሽ አደነቁ
#ethiopia | ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ባለው የድንበር መዝጋት ውሳኔ ላይ ግን ታጢንበት ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ በሚገኝ ሆስፒታል በመገኘት የኢቦላ ሕሙማን ማቆያ ክፍልን መጎብኘታቸውን ሮይተርስ ፅፏል።
በዚሁ ወቅትም የዩጋንዳን የኢቦላ ምላሽ አድንቀው፣ ፈጣንና ብቃት ያለው ነው ያሉ ሲሆን የሀገሪቱ የክትትል፣ የምርመራና የታካሚ አያያዝ ሥርዓቶች በተረጋጋ ሁኔታ ሥራቸውን እየሠሩ ነው ሲሉም በይፋዊ የኤክስ ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።
ይሄው የቁጥጥርና ክትትል ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የመከሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ያላትን ድንበር ለመዝጋት ያሳለፈችውን ውሳኔ እንደገና ልታስብበት ይገባል ሲሉ ለዩጋንዳ ምክረ ሀሳብ አቅርበዋል።
አክለውም፤ “እኔ በዩጋንዳ ነኝ፤ መንግሥቱም ለኢቦላ ወረርሽኝ ፈጣንና ብቃት ያለው ምላሽ ሰጥቷል” ሲሉ ጽፈዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት፤ በዩጋንዳ 19 የተረጋገጡ የኢቦላ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል። ከእነዚህ ውስጥ 14 ያህሉ ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ወደ ዩጋንዳ የገቡ ሰዎች ሲሆኑ 5 ያህሉ ደግሞ የዩጋንዳ ዜጎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በበሽታው ምክንያት ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ገልጸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው ሐዘናቸውን ገልጸዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ከአፍሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር በመተባበር ወረርሽኙን ለመዋጋትና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል ያለው ቻነል ዋን ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago