ፓስፖርት ማውጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀላል እንዲሆን ይደረጋል - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
************************
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የዜጎችን እንግልት ለመቀነስና አሠራሩን ለማዘመን በጀመረው የሪፎርም ሥራ፤ ወደፊት ማንኛውም ሰው ከቤቱ ሳይወጣ የፓስፖርት አገልግሎት በዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚያገኝበትን አሰራር ለመፍጠር እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ከኢቢሲ "ስለ ሀገር" ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ተቋሙ ሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአካሄደው ሪፎርም ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋሙ የያዘውን የዲጂታል አገልግሎት ግብ ለማሳካት ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር ሲስተሙን በማቀናጀት ላይ ይገኛል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ይህም ተገልጋዮች ዐሻራ ለመስጠት በአካል መገኘት ሳያስፈልጋቸው፣ በፋይዳ ሲስተም ላይ ያለውን መረጃ በቀጥታ በመጠቀም አገልግሎቱን በኦንላይን ብቻ እንዲያጠናቅቁ ያስችላቸዋል ብለዋል።
በተቋሙ ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከልም ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱን ጠቁመው፤ ተገልጋዮች ቅሬታ ካላቸው በአካል በተዘጋጁ የአስተያየት መስጫ ዴስኮች ብቻ ሳይሆን፣ በኦንላይን አማራጭ ምስልና ቪዲዮ በማያያዝ ጭምር ማቅረብ የሚችሉበት አሠራር መመቻቸቱን አመልክተዋል።
እያንዳንዱ የተቋሙ ሠራተኛ የኮምፒውተር አጠቃቀም ከአሻራ ጋር የተገናኘ በመሆኑ፣ ማን ምን ዓይነት ሥራ እንደሠራና ምን ዓይነት ጥፋት እንደፈጸመ በኦዲት መለየት ተችሏል። በዚህም መሠረት በዲሲፕሊን ኮሚቴ አማካኝነት በማስረጃ የተደገፈ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልጸዋል።
በኦንላይን አፕሊኬሽን ስም ተገልጋዮችን የሚያታልሉ ደላሎችን ለመከላከልም፣ አንድ ሰው ከአንድ ቦታ ሆኖ ከአሥር በላይ ሰዎችን መመዝገብ የማይችልበት ሲስተም ተዘርግቷል። ይህም ደላሎች የቴክኖሎጂ ክፍተትን በመጠቀም ሕዝቡን እንዲበዘብዙ ያለውን ዕድል እንደቀነሰው ተናግረዋል።
አገልግሎቱ በየጊዜው ራሱን እያዘመነ የሚሄደውን የማጭበርበር ተግባር ለመመከት፣ ቴክኖሎጂውንና የሕግ ማስከበር ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። ይህ የሪፎርም ሥራ ተጠናክሮ ሲቀጥል፣ ተገልጋዩ ያለምንም እንግልትና ያለ ተጨማሪ ክፍያ ፓስፖርቱን እቤቱ ሆኖ የሚያገኝበትን አሠራር ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሠራ ተገልጿል።
በላሉ ኢታላ
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopian #passport

13 days ago