Logo
EBC
ቻይና እና አሜሪካ የሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ ክፍት ሆኖ እንዲቆይ ተስማሙ
**********************

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በቤጂንግ ባደረጉት የፊት ለፊት ውይይት በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ ዙሪያ መክረዋል።

በውይይታቸውም በኢራን ጦርነት ሳቢያ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ያለው ውጥረት በበረታበት በዚህ ወቅት፣ ስትራቴጂያዊው የሆርሙዝ ባሕር ሰርጥ “ነፃ የኃይል አቅርቦት ፍሰትን ለመደገፍ ሲባል የግድ ክፍት ሆኖ መቆየት አለበት” በሚለው ነጥብ ላይ ፕሬዚዳንት ሺ መስማማታቸውን ኋይት ሐውስ አስታውቋል።

በሌላ በኩል፣ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ በኒው ዴልሂ፣ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የብሪክስ (BRICS) አባል ሀገራት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጦርነት እንዲያወግዙት አሳስበዋል።

ሚኒስትሩ “ቴህራን ለማንኛውም ዓይነት ውጫዊ ጫና በፍጹም እጅ እንደማትሰጥ” በአፅንኦት መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በደቡብ ሊባኖስ ከተሞች እና መንደሮች ላይ የእስራኤል ጥቃቶች አሁንም የቀጠሉ ቢሆንም፣ ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም ያለመ የሊባኖስ እና የእስራኤል ተደራዳሪዎች ሦስተኛ ዙር የቀጥታ ውይይት በዋሽንግተን ዲሲ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
#globalnews #usa #china #iran #hormuzstrait #brics #diplomacy

21 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.