Logo
EBC
ባለፉት 9 ወራት የተመዘገበው አፈጻጸም ለበጀት ዓመቱ የተያዘውን የትሪሊዮን ገቢ ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው - የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ኃይል
********************

የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ኃይል ለ2018 በጀት ዓመት የተያዘውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በቀሪ ወራት በሚከናወኑ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

ግብረ ኃይሉ በሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ ባለፉት 9 ወራት የተመዘገቡ ስኬቶችን እና የታዩ ውስንነቶችን በጥልቀት የገመገመ ሲሆን፣ የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።

ባለፉት 9 ወራት የተመዘገበው የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን የትሪሊዮን ገቢ ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው ብሏል።

የተያዘውን የገቢ ዕቅድ በተሟላ ሁኔታ ለማሳካትም በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል።

የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ታስክ ፎርስ ያስቀመጣቸው የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።

ጎን ለጎንም አገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የሪፎርም ሥራዎችን በተሟላ ሁኔታ መተግበር እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።
#ethiopia #tax #reform #revenue #ebc

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.