1 month ago
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ10 ወራት ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
*****************
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት ውስጥ ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) የ10 ወራት የእቅድ አፈጻጸምን አስመልክተው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ተቋሙ የሪፎርም እና በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በመከተሉ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ በሪፎርም ስራዎች እና በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረጉ፣ በማጭበርበር ምክንያት ሊጠፋ የነበረና ሀገር ልታጣው የነበረ 256.7 ቢሊዮን ብር በጥቅሉ ወደ ገቢ መቀየር መቻሉን ገልጿል።
በበጀት ዓመቱ 725 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ፣ በ10 ወራት ውስጥ ብቻ ከ600 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል። ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ258 ቢሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ተመላክቷል።
ለዚህ ስኬታማ አፈጻጸም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እና የተቋሙ አዲስ አደረጃጀት ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተጠቅሷል።
በሌላ በኩል፣ ከገቢ እና ወጪ ኮንትሮባንድ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ 23.1 ቢሊዮን ብር ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች (አልባሳት፣ ማዕድናት፣ መድኃኒቶች፣ ኮስሞቲክስና ኤሌክትሮኒክስ) ተይዘው ገቢ ተደርገዋል። በድንገተኛ ፍተሻና ቁጥጥር ብቻ 2.8 ቢሊዮን ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።
የሕግ ማስከበር ስራውን በተመለከተም፣ በሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማሩ 1,295 ኮንትሮባንዲስቶችን በቁጥጥር ስር በማዋል ለሕግ ማቅረብ መቻሉ ተረጋግጧል።
ኮሚሽኑ የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን ለማበረታታትና ኢንቨስትመንትን ለመደገፍ በሚያደርገው ጥረት፣ ለዘርፉ የሚውል 328.5 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉንም ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
በቀሪዎቹ የበጀት ዓመቱ ወራትም ሕገ-ወጥ ዝውውርን በመከላከል እና የመንግስትን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ ረገድ የተጀመረው ውጤታማ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በሂሩት እምቢአለ
#ebcdotream #customscommission #revenue

ባለፉት 9 ወራት የተመዘገበው አፈጻጸም ለበጀት ዓመቱ የተያዘውን የትሪሊዮን ገቢ ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው - የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ኃይል
********************
የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ኃይል ለ2018 በጀት ዓመት የተያዘውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በቀሪ ወራት በሚከናወኑ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።
ግብረ ኃይሉ በሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ ባለፉት 9 ወራት የተመዘገቡ ስኬቶችን እና የታዩ ውስንነቶችን በጥልቀት የገመገመ ሲሆን፣ የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።
ባለፉት 9 ወራት የተመዘገበው የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን የትሪሊዮን ገቢ ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው ብሏል።
የተያዘውን የገቢ ዕቅድ በተሟላ ሁኔታ ለማሳካትም በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል።
የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ታስክ ፎርስ ያስቀመጣቸው የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።
ጎን ለጎንም አገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የሪፎርም ሥራዎችን በተሟላ ሁኔታ መተግበር እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።
#ethiopia #tax #reform #revenue #ebc

3 months ago
Addis Ababa Revenues Bureau/u12e8u12a0u12f2u1235 u12a0u1260u1263 u1308u1262u12ceu127d u1262u122e
https://www.tiktok.com/u00... Ababa Revenues Bureau/u12e8u12a0u12f2u1235 u12a0u1260u1263 u1308u1262u12ceu127d u1262u122e","work_info":null,"__module_operation_CometTextWithEntitiesRelay_textWithEntities":{"__dr":"ProfileGeminiWeakReferenceLink_user$normalization.graphql
Addis Ababa Revenues Bureau/የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
https://www.tiktok.com/@ad...
5 months ago
አዲስ አበባ አህጉራዊ ኃላፊነቷን በብቃት በመወጣት፣ ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የጋራ መማማሪያ መድረክ መሆኗን ዳግም አረጋግጣለች።
ዛሬ በአህጉራችን መዲና አዲስ አበባ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ከመጡ ከንቲባዎች እና ከክልል አስተዳዳሪዎች ጋር ፍሬያማ የአቻ ለአቻ የመማማሪያ መድረክ እያካሄድን እንገኛለን።
በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) አማካኝነት በአፍሪካ ከተሞች የፋይናንስ አስተዳደር (Financial Management) አፈፃፀም ላይ በተካሄደው ጥልቅ የዳሰሳ ጥናት መሠረት፤ አዲስ አበባ ከተመዘነችባቸው 6 መስፈርቶች ውስጥ በ5ቱ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገቧ ልምድ እንድታካፍል ተመርጣለች።
ጥናቱ ከተካሄደባቸው ስድስት የአፍሪካ ከተሞች (ናይሮቢ፣ ዳሬሰላም፣ ሉሳካ፣ ኪጋሊ እና ያውንዴ) መካከል አዲስ አበባ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ቀዳሚ መሆን ችላለች። በተለይም የገቢ እና የፋይናንስ ሀብት አስተዳደርን በማዘመን ረገድ ከተማችን የጀመረችው ሪፎርም ውጤታማና ለአፍሪካ ከተሞች አርአያ መሆኑን የጥናቱ ግኝት አመላክቷል።
ይህ ስኬት፤ ከተማችን ከምትሰበስበው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ 71 በመቶውን ለልማት ሥራዎች በመመደብ፣ የዜጎችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስናደርግ የቆየነው የሪፎርም ጉዞ ውጤማነት ማሳያ ነው።
ዛሬ ከተለያዩ ከተሞች ለልምድ ልውውጥ የመጡት ተሳታፊ ከንቲባዎች እነዚህን የሪፎርም ሥራዎች በአካል በመጎብኘት፣ አዲስ አበባ በፋይናንስ እና በገቢዎች ስራ አቅሟን እንዴት ገንብታ ወደ ተግባራዊ ለውጥ እንደቀየረችው ሰፊ ተሞክሮ የምታካፍል ይሆናል።
ይህ መድረክ የአፍሪካ ከተሞችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጋራ የምንቀርጽበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
በመጨረሻም፣ ለዚህ ጥናት መሳካትና ለከተማችን እውቅና ለሰጡት ለተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA)፣ እንዲሁም የውጤቱ ባለቤት ለሆኑት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ለሥራ ባልደረቦቼ ሁሉ የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
አዲስ አበባ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ትቀጥላለች!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
Addis Ababa has once again reaffirmed its continental leadership by serving as a platform for mutual learning among our African brothers and sisters.
Today, in our continental capital, we are hosting a productive peer-to-peer learning forum with mayors and regional administrators from various African cities.
According to an in-depth survey conducted by the United Nations Economic Commission for Africa (UNECA) on the financial management performance of African cities, Addis Ababa was selected to share its experience after achieving outstanding results in five of the six key metrics evaluated.
Among the six African cities surveyed (Nairobi, Dar Es Salaam, Lusaka, Kigali, and Yaoundé), Addis Ababa emerged as the top performer. The findings specifically highlighted that the reforms our city initiated in modernizing revenue and financial resource management are both effective and serve as a blueprint for other African cities.
This success is a testament to the effectiveness of our reform journey, through which we have allocated 71% of the city’s total revenue to development projects to ensure the sustainable benefit of our citizens.
The visiting mayors and participants will personally tour these reform projects today. Addis Ababa will share its extensive experience in building financial and revenue capacity and translating that capacity into tangible, transformative change.
This forum represents a historic opportunity for us to collectively shape the future of African cities.
Finally, I would like to extend my deepest gratitude to the UNECA for conducting this study and recognizing our city, as well as to the residents of Addis Ababa and my colleagues, who are the true owners of this achievement.
Addis Ababa will continue to be a symbol of African prosperity!
May God bless Ethiopia and its people!

🏨 ሒልተን አዲስ አበባ በትርፍ አደገ📈
* የ308.6 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ተመዘገበ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ስር የሚተዳደረው አንጋፋው ሒልተን አዲስ አበባ፤ በተጠናቀቀው የ2017 የሒሳብ ዓመት አስደናቂ የፋይናንስ አፈጻጸም ማስመዝገቡን አስታወቀ።
የሪፖርቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
💰 የተጣራ ትርፍ፡ 308.6 ሚሊዮን ብር (ባለፈው ዓመት 140.4 ሚሊዮን ብር ነበር)።
💵 ጠቅላላ ገቢ፡ 506.4 ሚሊዮን ብር።
📊 የዕድገት መጠን፡ ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ 97% ዕድገት አሳይቷል።
🏦 ጠቅላላ ሀብት፡ የሆቴሉ ሀብት 1.98 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
የስኬቱ ሚስጥር ምንድን ነው?
የሆቴሉ ማኔጅመንት እንደገለጸው፤ ለዚህ ከፍተኛ ትርፍ ዋና ምክንያቶች፡-
የአዲስ አበባ የቱሪዝም ዘርፍ ማገገም፣
በከተማዋ የሚካሄዱ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች መጨመር እና
የሆቴሉ የአሠራር ቅልጥፍና መሻሻል ናቸው።
ለመንግስት የሚከፈለው ድርሻ
ኩባንያው ካገኘው ላይ 317 ሚሊዮን ብር የሚሆነውን ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በትርፍ ድርሻ (Dividend) መልክ ገቢ ያደርጋል።
የቱሪዝም ዘርፉ ማገገም ለኢኮኖሚው ትልቅ ተስፋ ነው! 🇪🇹
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#hiltonaddis #businessnews #ethiopia #tourism #revenue #economy #eih

Sponsored by
Surafel
6 months ago
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የግብር ከፋዮችን የባንክ አካውንት የመዘጋት ሥልጣን ገደበ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፣ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ያለምንም የላቀ አመራር ፈቃድ የግብር ከፋዮችን የባንክ ሂሳብ (አካውንት) እንዳይዘጉ የሚከለክል አዲስ መመሪያ ማውጣቱን አስታወቀ። ይህ እርምጃ በዘፈቀደ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለመቀነስና የንግዱን ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ለመጠበቅ የታለመ ነው።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ከከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ባደረጉት የምክክር መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም በኦዲተሮች የግል ውሳኔ ወይም በጥቃቅን የሂሳብ ስህተቶች ምክንያት አካውንቶች መታገዳቸው በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል።
ዝርዝሩን ያንብቡ
https://capitalethiopia.co...

Comments