23 days ago
አዲስ ዘመን፣ አዲስ ተስፋ
*************
ከትምህርት ገበታ የሚቀዳ ዕውቀት የአንድን ሀገር የነገ ዕጣ ፈንታ እና የታሪክ አቅጣጫ የመወሰን ታላቅ ኃይል አለው።
ትምህርት የፊደል መቁጠሪያ መንገድ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገርን የወደፊት ዕድል የሚቀርፅ፣ የብልጽግናን ጎዳና የሚያበራ እና በዕውቀት ላይ ተመስርቶ የሀገር ሉዓላዊነትን የሚያስጠብቅ መሣሪያ ነው።
የሀገራችን ሥርዓተ ትምህርት ለብዙ ዓመታት በርካታ መዋቅራዊ ጉድለቶች የነበሩበት ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ኋላ ቀር አሠራሮችን በመሰናበት፣ ከሀገሪቱ የዕድገት ፍላጎት ጋር የተጣጣመ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት መቀረጹ የትውልዱን የነገ ዕድል የሚቀይር ታሪካዊ እርምጃ ሆኗል።
ትምህርት የዕውቀት መቅሰሚያ ብቻ ባለመሆኑ የሀገር ሉዓላዊነትን፣ የቴክኖሎጂ ዕውቀትን፣ እና የኢኮኖሚ ከፍታን የሚያረጋግጡ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ተረካቢ ዜጎች የሚኮተኮቱበት ነው።
የተሻሻለው የትምህርት ሥርዓታችን በተግባር፣ በዲጂታል እና በቴክኖሎጂ አቅም ላይ ያተኮረ በመሆኑ፤ ተማሪዎች የነገውን ዓለም የሚመጥን ብቃት ከወዲሁ እንዲያዳብሩ እያደረጋቸው ይገኛል።
በዚህ የዲጂታል ዘመን በቴክኖሎጂ ፈጠራ ንቅናቄ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በየክፍል ደረጃው የምታስተምራቸው ህፃናትና ወጣቶች የበለፀገች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ከፊት የሚመሩ ቁልፍ ዜጎች ናቸው።
አዲሱ የትምህርት ዘመን የነገዋን ኢትዮጵያ በዕውቀት፣ በሥነ-ምግባር፣ በሀገር ፍቅር እና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ለታነፁ ስልጡን ልጆቿ የማስረከብ የታሪክ ቅብብሎሽ ሂደት አካል ነው።
በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #newyear #newacademicyear #education #reform #digitalization #ebc #ebcdotstream

25 days ago
ከፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ወደ ብቃት ማዕከል የኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ
**************
የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ለረጅም ጊዜ ለከፍተኛ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ተጋልጦ በመቆየቱ፣ ትምህርት የፖለቲካ መሣሪያ ሆኖ ዘልቋል።
አሠራሩ በብቃትና በታማኝነት ላይ የተመሠረተ ባለመሆኑም፣ ተማሪዎች በራሳቸው ችሎታና እውቀት መለካት ተስኗቸው ነበር።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደጠቀሱት በፊት የትምህርት ቤቶች አስተዳደር በፖለቲካዊ ታማኝነት ላይ መመሥረቱ በትምህርት ጥራት ላይ ቀጥተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ ፈጥሯል ።
የመምህራን የማስተማር ፍላጎት መዳከም፣ የግብዓት እጥረት እና በክፍል ውስጥ ከፍተኛ የተማሪዎች ብዛት መኖር፣ የትምህርቱን ውጤታማነት በእጅጉ ጎድቶት እንደነበርም ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።
ሥርዓቱ ተማሪዎችን ለገበያ ፍላጎት ወይም ለሕይወት ክህሎት ማዘጋጀት ባለመቻሉ፣ ከዩኒቨርሲቲ የሚመረቁ ተማሪዎች በሥራ ዓለም አቅም ማሳየት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር።
ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የሰለጠነ የሰው ኃይል የማይተካ ሚና እንዳለው በመገንዘብ፣ መንግሥት የትምህርት ዘርፉን የጥራትና የተደራሽነት ችግር ለመቅረፍ ስር ነቀል የሪፎርም እርምጃዎችን ወስዷል።
በዚህም የትምህርት ሥርዓቱን ከገበያ እና ከኢትዮጵያ ነባራዊ ፍላጎት ጋር ለማጣጣም የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ተደርጓል።
የግብረገብነት ትምህርትን ወደ ትምህርት ቤቶች መመለስ እና ቴክኒክና ሞያ በመባል የሚታወቁት የተግባር ክህሎቶች በትምህርት ስርአቱ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡
በትምህርት ዘርፉ የነበረው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት በመወገዱ፣ መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደሮች የሚመዘኑት በብቃታቸው፣ በችሎታቸው እና ለተማሪዎች በሚሰጡት እውቀት ብቻ ሆኗል።
ከዚህም በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ የማውጣትና ወደ ራስ-ገዝ አስተዳደርነት የመቀየር ሂደት ተጀምሯል።
የዩኒቨርሲቲ አመራሮችን በውድድር እና በብቃት የመምረጥ አዲስ ሥርዓት በመዘርጋቱ፣ ከኢትዮጵያም ሆነ ከውጭ አገር ብቁ ባለሙያዎች በዩኒቨርሲቲ አመራርነት እንዲወዳደሩ ዕድል ተከፍቷል።
ለተግባር ተኮር ትምህርት ትኩረት በመስጠት፣ ለተግባር እውቀቶች (እንደ አናጢነት፣ ግንበኝነት፣ ወዘተ) የነበረውን ዝቅተኛ የህብረተሰብ አመለካከት በመለወጥ፣ ተማሪዎች ወደ ተግባር ተኮር ትምህርቶች በስፋት እንዲገቡ እየተደረገ ነው።
ሪፎርሙ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የመማር ማስተማር ሂደቱ መሻሻል እያሳየ ነው። ተማሪዎች በአካዳሚክ እና በተግባራዊ ክህሎት የተሻሉ መሆናቸውም በሥራ ገበያው ላይ በግልጽ እየታየ ነው፡፡
በላሉ ኢታላ
#ebc #ebcdotstream #ethiopian #education #reform

3 months ago
የአገሪቱን የመስኖ ሽፋን ወደ 2.6 ሚሊዮን ሄክታር ለማድረስ የተያዘው ግብ እመርታ እያሳየ መሆኑ ተገለጸ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር
መግለጫ እነሆ ፥
#ethiopia | አገራዊ የመስኖ ልማት ጉዞ ተስፋ ሰጪ እመርታ የኢትዮጵያ በመስኖ የመልማት አቅሟን፤ ለመጠቀምና ተፈጥሮ የለገሰቻትን ውሃ፣ መሬት፣ ምቹ የአየር ሁኔታ እንደዚሁም አምራች የሰውሃይል በአግባቡ መጠቀም ባለመቻሏ ለዘመናት የራሷን የምግብ አቅርቦት እንኳን መሸፈን ሳትችልና በችግር ወቅት ለዕርዳታ ወደ ውጪ ስታማትር መኖሯ የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ነው፡፡
ኢትዮጵያን በተለያየ ጊዜያት ያስተዳደሩ መንግስታት ምርታማነት ለማሳደግ ያስችለናል ያሏቸውን የተለያዩ ሙከራዎች በመከተል ጥረት ቢያደርጉም በሚጠበቀው ልክ ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ አገራችን የራሷን የምግብ አቅርቦት መሸፈን ሳትችል፣ በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ በማውጣት ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ የምግብ ምርቶችን ከውጭ ስታስገባ ኖራለች።
እንደ ሃገር ሰፋፊ የመስኖ ፕሮጀክቶች ከ1960ዎቹ ጀምሮ መተግበር ቢጀምሩም ቁጥራቸው እጅግ ጥቂትና ውጤታቸውም በዛው ልክ ውስን እንደነበር በመስኩ የተደረጉ የዳሰሳዎች ጥናቶች ያሳያሉ ፡፡ ለአብነትም ለስኳር ልማት የተገነቡ ፕሮጀክቶች እንደ ወንጂ፣ መተሃራ፣ ፊንጫ ፣ የአሚባራ፣ የአልዌሮ፣ የጎዴ፣ የተንዳሆ እና የከሰም መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠቃሾች ቢሆኑም በትግበራ ሂደት ግን ለአመታት ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ውጤታማ ሳይሆኑ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
ይህንን አዙሪት በመስበርና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ ከተፈጥሮ ዝናብ ባሻገር የከርሰ-ምድርና የገጸ-ምድር ውኃን በአግባቡ በመጠቀም መስኖን ማስፋፋት ወሳኝ ሆኖ ተገኝቷል። በተለይም ባለፉት የለውጥ አመታት የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ የተለመደና ፈተና የሆነ አዙሪት ለመላቀቅ የሚያስችሉ የተለያዩ እቅዶችን አዘጋጅቶ እና ዘርፉን ራሱን በቻለ ሚኒስቴር መስራቤት ደረጃ በማደራጀት አዲስ የፖሊሲ መር የልማት ጥረትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ስራ መስራት ጀምሯል፡፡
መንግስት የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ከወሰዳቸው ወሳኝ እርምጃዎች መካከል የመስኖ ልማት ዘርፍን ውጤታማ በሆነ መንገድ በማሻሻል ምርታማነትን ማሳደግ እንዲቻል ዘርፋ ለአጠቃላይ አገራዊ እድገት የሚኖረውን ሚናም በልዩ ትኩረት ለማሳደግ እንዲያስችለው መስኖ በጥናት በተለዩ ቦታዎች ላይ በልዩ ትኩረት እንዲያስፋፋ በማለም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴርን በ2014 ዓ/ም እንዲቋቋም አድርጓል፡፡ በዚህም የአገር አቅም በፈቀደ ልክም መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ በጀት እንዲመደብለት እና በዘርፉ ተግባራዊ ለውጥ እንዲመጣ የሚያስችሉ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴርም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማትን ወደ ተቀናጀ የልማት አቅጣጫ በመምራት፤ ሀገራችን ያላትን ከፍተኛ የውሃና ሰፊ የመሬት ሀብት ማዕከል በማድረግ፤ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት እና በቆላማ አካባቢ የሚገኘውን እምቅ የልማት ፀጋዎችን በማጥናትና ለአርብቶአደሩና ከፊልአርብቶአደሩ ጥቅም እንዲዉል በማድርግ የሀገራችንን የምግብ ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ ለማስቻል መተግበር የጀመራቸውም ስራዎች አመርቂ ውጤቶች ማሳየት ጀምረዋል፡፡
መስሪያ ቤቱ ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማስጠናትና በመገንባት፤በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በክልሎች የሚገቡ አነስተኛ መስኖዎችን በመከታተልና ድጋፍ በመስጠት በሃገሪቱ ምርትና ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ያስቻሉ ተግባራትን መጀመሩም ከወዲሁ መታዘብ ይቻላል፡፡
በተለይ ደግሞ ባለፋት ሁለት የበጀት አመታት ማለትም በ2017 እና 2018 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈጻጸም ዙርያ የተከናወኑ ስራዎች በአጠቃላይ በዘርፋ የሚታዩ ጅምር ሙከራዎችን ወደ አዲስ ታሪክ ያሸጋገረ ምዕራፍ ላይ መድረሱን መታዘብ ይቻላል።
ዘርፋ ከተሰጠው ልዩ ትኩረትና በአገር አቀፍ ደረጃ የመስኖ ልማት ጥያቄዎች መበራከት ከጅምሩ በቂ ጥናቶችና የዲዛይን ስራዎች ጥልቅ የበጀት ዝግጅትና በከፍተኛ የህዝብና የመንግስት አመራር ማእቀፎች በቂ ውይይት ተደርጎባቸው እንዲሁም የአፈጻጸም ስጋቶችና በተለይም ከአጠቃላይ የበጀት ዝግጅቶች አንጻር በነበሩ ውስንነቶች ጉልህ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በፍጥነት በመመካከር መሰረታዊ የማጣጣም ስራዎች መከወን በመቻሉ በርካታ ስራዎችን በተከታታይ ወራት በስኬት ሐዲድ ለማስጓዝ ተችሏል።
በዚህም በነዚህ ሁለት አመታት ለበርካታ አመታት ግንባታቸው የተጓተቱ ፣ የዲዛይን ስራ ጉድለቶች የነበሩባቸው ተጠናቀውም ለረጅም ጊዜ ጥገና ያልተደረገላቸው እና ከፍተኛ ብልሽት አጋጥሟቸው የነበሩ ፕሮጀክቶችን ቁርጠኛ በሆነ የፕሮጀክት አመራር ክትትል እና ጥብቅ የኮንትራት አስተዳደር ስርዓትን መሰረት በማድረግ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
ለዚህ ስኬት ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችንም መንግስት የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ ያለውን ፅኑ ፍላጎትና እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ድጋፍ ከግንዛቤ በማስገባት ይህንንም በሚመጥን መልኩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ በጥራት በፍጥነት እና የኮንትራት ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ የሰጠው በሳል አመራርም ተጠቃሽ ምክንያት ነው።
በዚህም ምክንያት ለአመታት የዘገዩና የማህበረሰባችን የአመታት የቅሬታ ምንጨ ሆነው የኖሩትን በአጠቃላይ 10 የሚሆኑ ግዙፍ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በአጭር ግዜ ከውስብስብ ችግሮች በማላቀቅ በልዩ ትኩረት ቅድሚያ በተሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት በተፋጠነ ጊዜ እንዲጠናቀቁ ጥረት ተደርጓል።
እነዚህም የመስኖ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የማልማት አቅማቸው እና ተጠቃሚ የሚያደርጉት እማና አባ ወራወዎች በቅደም ተከተላቸው መሰረት የሚከተሉት ናቸው ፡-
1.ጊዳቦ ሎት 2 - የማልማት አቅሙ- 13420 ሄ/ር 26840 እማ/አባወራዎች
2. ጎዴ -የማልማት አቅሙ -10,000 ሄ/ር 20000 እማ/አባወራዎች
3. ወልመል ሎት 1 እና 2 – 12040 ሄ/ር -24080 እማ/አባወራዎች
4. ጨልጨል ሎት 2- 4145 ሄ/ር 8290 እማ/አባወራዎች
5.የቄጦ መስኖ 5000 ሄ/ር 10,000 እማ/አባወራዎች
6. የታችኛው ርብ -3200 ሄ/ር 6400 እማ/አባወራዎች
7. የተንዳሆ - 60,000 ሄ/ርያለማል 120,000 እማ/አባወራዎች
8. የከሰም መስኖ -20 ሺኅ ሄ/ር 40,000 እማ/አባወራዎች
እንዲሁም አርጆ ዲዴሳ እና መገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች መሠረታዊ የግንባታ ሥራቸው አልቆ የማጠናቀቂያ ሥራቸው እየተፋጠነ ከመሆኑም በላይ በቅርቡ በክብር የሚመረቁ ይሆናል፡፡
መገጭ እና አርጆ የመስኖ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ በአጠቃላይ የ10ሩ ፕሮጀክቶች ብቻ ድምር የማልማት አቅማቸው 224,805 ሄክታር ሲሆን 450,000 እማና አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚደርጉ ናቸው፡፡
በሌላ በኩል እንደ ጨልጨል (ሎት1) አጂማጫጫ፣ ካሊድ ዲጆ፣ ሎጊያ፣ ላይኛው ጉደር፣ አንገር ፣ ፈንታሌ፣ ወይቦ፣ ላይኛው ርብ፣ ሽንሌ፣ እና አደኣ በቾ የመስኖ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በዕቅዳቸው መሠረት የግንባታ ስራዎቻቸው እየተከናወ ባጠናቀቅናቸው የመስኖ ፕሮጀክቶች በአሁኑ ወቅት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን በማልማት የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀናጁ ስራዎች በመተግበር ላይ እንገኛለን፡፡
መንግስት ለመስኖ ልማቱ ዘርፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በተሰሩ ስራዎች ከለውጡ በፊት 490 ሺህ ሄክታር የነበረው የመስኖ ሽፋን ወደ 2.6 ሚሊዮን ሄክታር ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡ አሁን የተጀመሩ ፕሮጀክቶችም ሲጠናቀቁ የአገራችን የመስኖ ሽፋን በከፍተኛ መጠን የሚጨምር ይሆናል፡፡ እነዚህ መሰረተ ልማቶችም የተጀመረውን የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነት በማረጋገጥ ረገድ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
በ2017 እና በ2018 በጀት አመት ፕሮጀክቶች አጠናቅቀን ለስኬት ስንበቃ ፤ ግንባታዎች ባቀድነው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ስያደርጉ የቆዩትን፣ እንደዚሁም በቀጣይነትም ስራን ሊያስጓጉሉ የሚችሉትን ቁልፍ ማነቆዎች በጥናት በመለየት ውስብስብ ለሆኑና ለቆዩ ችግሮች ተገቢ እና ህጋዊ መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የተሰሩ ስራዎች ሚናቸው ትልቅ ነው፡፡
በመሆኑም ይህ ፈጣን የፕሮጀክት አፈጻጸም እና ክትትል በቀላሉ የተገኘ እንዳልሆነ መገንዘብ ያሻል።
ለመሆኑ በእነዚህ የግንባታ 2 አመታት እንደማንኛውም የኮንስትራክሽን ዘርፍ የመስኖ ግንባታ ያጋጠሙት ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የተሰጣቸው መፍትሔዎችስ ?
በግንባታ ሂደቱ ያጋጠሙንን ተጠባቂና ተጠባቂ ያልሁኑ ተግዳሮቶች ተወጥተን የግንባታ ስራችንን ስናከናውን በግንባታ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ያሳደሩ ዋና ዋና ተግዳሮቶችን የሚከተሉት ናቸው፦
* የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ከውኃ ጋር የተቆራኙና በካበተ የዘርፍ ጥናት የተደገፋ መሆን የሚገባቸው በመሆናቸው በዘርፉ ልምድ ያላቸው በቂ አገር በቀል የአማካሪና ተቋራጮች አቅም በበቂ አለመኖሩ ከጅምሩ የታዩ ተግዳሮቶች ነበሩ:: በተጨማሪም አብዛኞቹ ፕሮጀክቶች የሚከናወኑት በመንግስት የልማት ድርጅቶች ሲሆን ተቋማቱ በዘርፋ ለሚደረግ የመሰረተ ልማት ግንባታ የነበራቸው ልምድና አቅምም ውስን ከመሆኑም በላይ ከግሉ ዘርፍ የሚሳተፉት በጣት የሚቆጠሩ ተቋማትም ገና አጥጋቢ ቁመና ያልነበራቸው መሆኑ።
* የበጀት እጥረትና የገንዘብ አቅርቦት መዘግየት፦ ፕሮጀክቶቹ ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቁ ቢሆንም በየዓመቱ የሚመደበው በጀት አነስተኛ መሆኑና የተፈቀደው በጀትም በወቅቱ ጥሬ ገንዘብ ሆኖ ባለመለቀቁ ከክፍያዎች መስተጓጎል የተነሱ መጓተቶችና የዋጋ ንረት ፕሮጀክቶች በሚፈለገው ደረጃ ማከናወን አለመቻሉ፣
* ከፍተኛ የገበያ የዋጋ ንረት (Market Inflation)፦ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍና አገር ውስጥ ሁኔታዎች ምክንያት እንደ ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ነዳጅ እና የጉልበት ዋጋ ላይ በየግዜው ከፍተኛ ጭማሪ ማጋጠሙ። በዚህም ምክንያት የፕሮጀክት በዘገዩ ቁጥር ወጪዎቻቸው በየግዜው እንዲጨምሩ ምክንያት ሆነዋል ::
* የስትራቴጂካዊ ግንባታ ዕቃዎች አቅርቦት እጥረት፦ ሲሚንቶ፣ ብረትና ነዳጅ በገበያ ላይ በበቂ ሁኔታ በወቅቱ አለመገኘታቸው የግንባታውን ፍጥነት በእጅጉ ገድበውት ቆይተዋል። በዚህም ምክንያት ፕሮጀክቶች በእቅዳቸው ልክ እንዳይከወኑ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል ::
* የግድብ እና መስኖ መሰረተ ልማቶች ዲዛይን ስራዎች ጉልህ ክፍተቶችና ያጋጠሙ የጂኦሎጂካል ውስብስብነት ችግሮች :: ምንም እንኳን ፕሮጀክቶች መነሻ የሚሆኑ ጥናትና ዲዛይን ተሠርቶባቸው ቢጀመሩም፣ በትግበራ ወቅት በሚያጋጥሙ የመሬት አቀማመጥና የጂኦሎጂካል ይዘቶች ምክንያት የዲዛይን ክለሳዎችን ማድረግ የግድ ማስፈለጉ የውል ማሻሻያዎችንና የጊዜ ማራዘሚያዎችን እንዲደረጉ የግድ የሚያስብሉ ሁኔታዎች አጋጥመዋል ::
በዚህም ምክንያት ለሚኖሩ ለውጦች ተጨማሪ የኮንትራት ወጪ እና ግዜ መጠየቃቸው የግድ ሆኗል።
የተወሰዱ ስልታዊና መዋቅራዊ የማስተካከያ እርምጃዎች የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ያጋጠሙትን የአሠራር ክፍተቶች፣ የኦዲት ግኝቶችና የባለድርሻ አካላትን አስተያየቶች እንደ ግብዓት በመውሰድ ሰፊ ተቋማዊ ለውጥ (Institutional Reform) አድርጓል።
በዚህም መሠረት የተወሰዱት ቁልፍ ተቋማዊ እርምጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦
* ልዩ የፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በአዲስ መልክ በ2017ዓ/ም ተቋቁሟል ፦ከዋናው መሥሪያ ቤት እስከ ፕሮጀክት ሳይት የነበረውን የቁጥጥር እና ክትትል ለማጥበቅና የውል አስተዳደር እንዲሁም የቁጥጥር ሥርዓቱን (Contract Administration & Construction supervision) በዲጂታል ፕላትፎርም ጭምር ለማዘመን ዘርፈ-ብዙ ብቁ ባለሙያዎችን ያቀፈ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ተቋቁሟል።
* ጥብቅ የክትትልና ግምገማ (M&E) ሥርዓት መዘርጋት፦የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ወርሃዊ፣ ሩብ ዓመት፣ ግማሽ ዓመት እና ዓመታዊ የክትትልና የመስ ክምልከታ ሥርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ ሆኗል።
* በኮንትራት ስምምነት መሰረት ለፕሮጀክቶች ክትትል የሚያስፈልገውን ሎጅስቲክስ እንዲሟላ ተደርጓል፥- በአዲስ መልክ ለተደራጀዉ ፕሮግራም ጽ/ቤት ከማዕከል እስከ ፕሮጀክት ሳይት ለተመደቡ የስራ መሪዎችና ሙያተኞች የሚያስፈልጉ የመስክን ነባራዊ ሁኔታ የሚቋቋሙ የመስክ ተሽከርካሪዎች እና የቢሮ ቁሳቁሶችን በኮንትራት ስምምነት ውስጥ በተቀመጠው መሰረት በማሟላት የክትትል አመራሮች እና ባለሙያዎች በተቀናጀ መልኩ ጉልበታችዉና እውቀታቸዉን ለፕሮጀክቶቹ ስኬት የሚያውሉበትን ሁኔታ በመፍጠር በጊዜና በጥራት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ውጤታማ ስራ እየተመዘገበ ይገኛል::
* የቁሳቁስ አቅርቦት ሰንሰለትን ማሳለጥ (Supply Chain Optimization)፦ የሲሚንቶ እና የነዳጅ እጥረትን ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ በቀጥታ ከአምራች ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች ጋር ስልታዊ ትስስር በመፍጠር የግንባታ ግብዓቶች ሳይቆራረጡ ፕሮጀክት ሳይት ላይ እንዲቀርቡ አድርጓል።
* ባለሦስት ወገን ስምምነት (Tri-party Agreement) መተግበር፦ በተቋራጭ፣ በአማካሪ መሐንዲስ፣ በባለቤት(ሚኒስቴሩ) እና በቁሳቁስ አቅራቢዎች መካከል የተቀናጀ የጋራ መግባቢያ ስምምነት በመፈረም ሥራዎች በተቀመጠላቸው ወሰን፣ በጀትና ጥራት ኮንትራት መሰረት አድርገው እንዲከናወኑ ተደርጓል።
* አዳዲስ መመሪያዎችና ስታንዳርዶች ማዘጋጀት፦ ወደፊት ለሚከናወኑ ማናቸውም ግንባታዎች መነሻ የሚሆኑ የፕሮጀክት አስተዳደርን የሚያዘምኑ አዳዲስ የአሠራር ደንቦችና መመሪያዎች ተዘጋጅተዋል።
* የዋጋ ማስተካከያ መፍቀድ፦ አገር በቀል ተቋራጮች ፕሮጀክቶች በወቅቱ መጠናቀቅ ባለመቻላቸው ያጋጠመውን የዋጋ ንረት በራሳቸ መቋቋም ባለመቻላቸው፣ በመንግስት የተቀመጡ አሠራሮችን በመከተል ቀደም ሲል የዋጋ ማስተካከያን ይከለክሉ የነበሩ ውሎችን ከ2013 ጀምሮ በተሰጠው የመንግስት ውሳኔ መሰረት ውሎችን በማሻሻል የዋጋ ማስተካከያ በሃገር ደረጃ እንዲደረግ ፈቅዷል።
* የበጀት እጥረትና የገንዘብ አቅርቦት መዘግየትን በተመለከተ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት በመወያየት እና በመስራት አስፈላጊው በጀት እና ጥሬ ገንዘብ በወቅቱ ለመስኖ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲለቀቁ ማድረግ ተችሏል፡፡
የመስኖ ፕሮጀክቶች እንደ ማንኛውም የግንባታ ፕሮጀክቶች መንግስት ባወጣው የግዥ መመሪያዎች፣ ደንቦች እና ውሎች የሚተዳደሩ ናቸው :: የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር መ/ቤት ከሌሎች ተቋማት የተረከባቸውንም ሆነ በራሱ የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች የሚያስተዳድረው የመንግስትን ህግና ስርአትን በማክበር በኮንትራት ውል ስምምነት መሰረት ብቻ ነው፡፡
በዚህም መሰረት በየግዜው ልዩ ፍቃድ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሲያጋጥሙም በህግ የመፍቀድ መብት ያለውን የመንግስት አካል ፍቃድ በማግኘት ብቻ የተፈፀሙ ስራዎችን መከወን ተችሏል ፡፡
ከመስኖ ፕሮጀክቶች ውስብስብ ባህሪ በመነሳት በተቻለ መጠን ባሉ ሀገራዊ አቅሞች እና ልምድና አቅም ባላቸው አማካሪ ድርጅቶች ዝርዝር ጥናትና ዲዛይን ሳይሰራ የመስኖ ፕሮጀክቶች አይጀመሩም፡፡ ሆኖም በትግበራ ወቅት የዲዛይን ክፍተቶች መኖራቸው ሲታወቅ በተቀመጠው የውል አስተዳደር ስምምነት መሰረት የፕሮጀክቶች የዲዛይን ችግር እንዲፈታ በማድረግ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በዲዛይን
ማሻሻያው መሰረት እንዲቀጥሉ እና እንዲጠናቀቁ ይደረጋሉ፡፡
ምንም እንኳን የዲዛይን ክፍተቶች ችግር ደረጃ ቢለያይም ፕሮጀክቶች በተግባር የዲዛይን ክፍተቶች እንደሚያጋጥማቸው ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቶች ውል አስተዳደር አንፃርም ተቋራጭ እና አማካሪ ድርጅቶች በገቡት ውል መሰረት ብቻ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ውሎችን ያስተዳድራል በዚህም የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ውጤትም ይህንኑ ሀቅ ያረጋግጣል። በመሆኑም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከውል ውጪ የሚፈፀሙ ምንንም አይነት ግዥዎችና ጭማሪዎችም የሉም።
አለማቀፍ ልምዶች እንደሚያሳዩት ማንኛውም ፕሮጀክት ተግባራዊ በሚደረግባት ወቅት በገቢያ ሁኔታ ለሚከሰቱ የዋጋ ጭማሪዎች ተገቢውን አሰራር እና ኮንትራት ስምምነትን በመከተል የሚፈቀዱ የዋጋ ማስተካከያዎችን በማድረግ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
በአገራችን ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ የግንባታ ግብአቶች በመጨመሩ፣የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ እና በአለማቀፍ ሁኔታዎች መለዋወጥ ምክንያት የግንባታ ሴክተሩ በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ ገብቶ ቆይተው የነበሩ ፕሮጀክቶች በመኖራቸውም እስካሁንም ከተመሳሳይ ችግሮች ሙሉ በሙሉ ለማገገም የሚያስችል ስራ መስራትም ቀጣይ የቤት ስራችን ይሆናል፡፡
በዚህም ምክንያት አገር በቀል ተቋራጭ ድርጅቶች የተከሰተውን የግንባታ ግብአቶች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በራሳቸው መቋቋም እንዳቃታቸው መንግስት በመገንዘቡ የተቀመጡ አሰራሮችን በመከተል የዋጋ ማስተካከያ እንዲደረግ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ቀደም ሲል የዋጋ ማስተካከያ ይከለክሉ የነበሩ ውሎችን በማሻሻል የዋጋ መስተካከያ መፍቀድ እና ተግባራዊ ማድረግ ከፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የሚያስገኘውን ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት በተሰጠው ፍቃድ መሰረት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
ኢትዮጵያ በዝናብ ጥገኝነት ላይ የተመሠረተውን የግብርና ክፍለ-ኢኮኖሚ ወደ መስኖ መርና አስተማማኝ ምርታማነት ለመቀየር የጀመረችውን ጉዞ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው አሁን የተጀመሩት ተቋማዊ ሪፎርሞች እና ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ወደ ውጤት የመቀየር ጅምሮች ቀጣይነት ሲኖራቸው ብቻ ነው። ይህንን ለማደናቀፍና ኮንትራትና ፕሮጀክት አስተዳደር ስርዓትን በአግባቡ መረዳት ባቃታቸው ወይም ሆን ተብሎ ሂደቶችን ለማጠልሸት የሚሰሩ ስራዎች በፍፁም ተቀባይነት ሊኖራቸው አይችሉም ::
እንደሚታወቀው ሃገራችን በተለያዩ ሴክተሮች አስደናቂ የሆኑ ስኬቶችን እያስመዘገበች ትገኛለች፡፡ ከዚህ አንጻር እንደ ሃገር የምናስመዘግባቸው ስኬቶች ለህዝባችንን እና ለአጋሮቻችን የሚሰጠው ትርጉም ትልቅ የመሆኑን ያህል ይህ ጅምር እመርታ የማያስደስታቸው በከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነት እና የአጋሮች ጥረት የተገኙ ውጤቶች የሚያቅራቸው ሀይላት መኖራቸው ግን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ከዚህ አንጻር በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመስኖ ዘረፍ እየተገኘ ያለውን ስኬት ለመገንዘብና እውቅና ለመስጠት ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡ ይሁን እንጂ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ይህንን ሁኔታ ወደ ጎን በመተው የተቋቋመለትን አላማ እና የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉአላዊነት እና የህዝብ ጥቅም ታሳቢ በማድረግ በዘርፉ የሚገኙ አሰራሮችንና ህጎችን መሰረት በማድረግ በሃገሪቱ የጀመራቸውን በውጤት የታጀበ የመስኖ ፕሮጀክቶች የማጠናቀቅ ድሎችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ለኢትዮጵያ የምግብ ሉኣላዊነት መረጋገጥ እንሰራለን!!
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚንስቴር
ሃምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም

ትውልድን ከመሠረት ማነጽ፦ በመዋቅራዊ ሽግግር ላይ የሚገኘው የሀገራችን የትምህርት ዘርፍ
***********************
በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማደጉ በራሱ ትልቅ ስኬት ቢሆንም፣ የትምህርት መሠረት በሆነው የመጀመሪያ ደረጃ ጥራት ላይ ትልቅ ክፍተት እንደነበር ይታወቃል።
የቀድሞው የትምህርት ሥርዓት ትኩረት በዋናነት በየክልሉ ዩኒቨርሲቲዎችን ማስፋፋት እና የተመራቂዎችን ቁጥር ማብዛት ነበር።
ከመሠረቱ በትኩረት ያልተሠራባቸውን ተማሪዎች አስመርቆ ማውጣቱ ለትምህርት ጥራቱ ማሽቆልቆል ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርላማ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ንግግሮች እና በተግባር ባካሄዷቸው ንቅናቄዎች፣ “ከላይ ወደ ታች” የነበረውን የተዛባ አካሄድ በመቀየር “ከታች ወደ ላይ” የሆነ ስትራቴጂ መከተላቸውን አመልክተዋል።
ከለውጡ ወዲህ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችም ይህንኑ የትምህርት ጥራት ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት ያለሙ ናቸው።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የትምህርት ጥራቱን ለማሻሻል ከተከናወኑ ሥራዎች መካከል በሀገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፀደ ሕፃናት ትኩረት የሰጡ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶች እና ማዕከላት በስፋት መገንባት ነው።
ቀደም ሲል የቅድመ-መደበኛ ትምህርት የግል ትምህርት ቤቶች ብቻ የሚያከናውኑት ተግባር አድርጎ ይመለከት የነበረውን የተዛባ አተያይ በመስበር ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረጉ መዋዕለ ሕፃናት በስፋት ተገንብተዋል።
በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የአፀደ ሕፃናት ክፍሎች በነፃ እንዲካተቱ መደረጉ፣ ማኅበረሰቡ ልጆቹን ያለምንም ክፍያ እንዲያስተምር ሰፊ ዕድል ፈጥሯል።
በዚሁ መሠረት ባለፉት 7 ዓመታት ብቻ ከ35 ሺህ በላይ መዋዕለ ሕፃናትን መገንባት ተችሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ማብራሪያ፣ “እነዚህ ሕፃናት ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ሕልውና መሆናቸውን ስለምናውቅ ነው ከመሠረቱ የምንሠራው” ማለታቸው የተደረገውን መሠረታዊ ለውጥ ያመላክታል።
የትምህርት ቤት ምገባ ለትምህርት ጥራት ያለውን ጉልህ ፋይዳ ታሳቢ በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናትን የመርሐ ግብሩ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
ይህ ስትራቴጂ ሕፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲቆዩ፣ መጠነ ማቋረጥ እንዲቀንስ እንዲሁም በአካልም በአእምሮም ጤናማ ሆነው እንዲያድጉ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
ከሥር በአግባቡ ተኮትኩተው የመጡ ተማሪዎች ትክክለኛ እና በቂ ዕውቀት የሚያገኙበትን ተቋም በማዘጋጀት በኩልም መንግሥት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል።
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ከመደመር መጽሐፍ ሽያጭ እና መሰል ገቢ ማሰባሰቢያ ኢኒሼቲቮች በተገኘ በጀት በሁሉም ክልሎች 35 የሁለተኛ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ገንብቷል።
ከዚህ በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በየአካባቢው እየተገነቡ ይገኛሉ። ደረጃቸውን የጠበቁ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን መገንባት ላይም በትኩረት እየተሠራ ነው።
መንግሥት ከመሠረቱ የጀመረውን ይህን የትምህርት ጥራትን የማሻሻል ሥራ ሀገር አቀፍ የጥራት መለኪያ ሥርዓት በማውጣት ጭምር እየተከታተለው ይገኛል።
ተግባራዊ የተደረገው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) እንዲሁም በ8ኛ ክፍል ክልላዊ እና በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናዎች አሰጣጥ የተዘረጋው ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓት የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ሥራው አካል ነው።
በአንድ ሀገር የትምህርት ጥራት የሚለካው በዩኒቨርሲቲዎች ብዛት ወይም ከተቋማቱ በሚወጡ ተመራቂዎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን፣ ተማሪዎቹ ከመነሻው በሚቀስሙት ዕውቀት እና ክህሎት እንዲሁም በተግባር በሚያሳዩት ብቃት ነው።
ሀገራችንም “ከታች ወደ ላይ” ስትራቴጂዋን በመከተል የትምህርት ተደራሽነትን ከጥራት ጋር ለማስማማት እያደረገችው ያለው ጥረት እጅግ ተስፋ ሰጪ ነው።
አፀደ ሕፃናትን ከማስፋፋት ጀምሮ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራምን ማጠናከር፣ ጥብቅ የምዘና ሥርዓት መዘርጋት እንዲሁም በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን መገንባት የነገውን ጠንካራ ትውልድ በቅድሚያ የማነጽ ሥራ ነው።
በጥቅሉ ኢትዮጵያ የመጻኢው የቴክኖሎጂ ዓለም ዋና ተዋናይ እንድትሆን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲን (AI University) ጨምሮ የነገውን ትውልድ የሚያንጹ ተግባራትን በስፋት እያከናወነች ትገኛለች።
ይህ ትውልድን የመገንባት ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ ጉዞ ሀገራችን ለወደፊት ሕልውናዋ እና ዘላቂ ዕድገቷ ያዋለችው ትልቁ እና አስተማማኙ ኢንቨስትመንት ተደርጎ የሚወሰድ ነው።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
#ethiopia #education #reform #quality #ebc

5 months ago
ባለፉት 9 ወራት የተመዘገበው አፈጻጸም ለበጀት ዓመቱ የተያዘውን የትሪሊዮን ገቢ ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው - የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ኃይል
********************
የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ኃይል ለ2018 በጀት ዓመት የተያዘውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በቀሪ ወራት በሚከናወኑ ሥራዎች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።
ግብረ ኃይሉ በሪፎርም ሥራዎች ዙሪያ ባለፉት 9 ወራት የተመዘገቡ ስኬቶችን እና የታዩ ውስንነቶችን በጥልቀት የገመገመ ሲሆን፣ የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።
ባለፉት 9 ወራት የተመዘገበው የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም በበጀት ዓመቱ የተያዘውን የትሪሊዮን ገቢ ዕቅድ ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው ብሏል።
የተያዘውን የገቢ ዕቅድ በተሟላ ሁኔታ ለማሳካትም በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል።
የብሔራዊ ታክስ ሪፎርም ታስክ ፎርስ ያስቀመጣቸው የቀጣይ ወራት የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።
ጎን ለጎንም አገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የሪፎርም ሥራዎችን በተሟላ ሁኔታ መተግበር እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል።
#ethiopia #tax #reform #revenue #ebc

8 months ago
⚖️ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዲስ ተቀጣሪ የሕግ ጉዳይ ጸሐፊዎች የመግቢያ ስልጠና ተሰጠ!
📜
#ethiopia | የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በቅርቡ ለቀጠሯቸው "የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ I" እና "የሕግ ጉዳይ ጸሐፊ II" ባለሙያዎች፣ ከየካቲት 06 እስከ 09/2018 ዓ.ም ድረስ የቆየ የመግቢያ ስልጠና ሰጥተዋል።
የስልጠናው ዋና ዋና ነጥቦች፦
📚 ይዘት፦
የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ታሪካዊ አመጣጥ፣ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተልዕኮ፣ መዋቅራዊ አደረጃጀት እና የውስጥ አስተዳደር ሕጎች ላይ ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
💡 የለውጥ ስራዎች፦
አዲስ ተቀጣሪዎች ፍርድ ቤቱ እያከናወናቸው ባሉት ዘመናዊ የሪፎርም ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ስልጠናው ትልቅ ሚና ይጫወታል።
👨⚖️ የስራ መመሪያ፦
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ለአዲስ ተቀጣሪዎቹ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው፦
አዲስ ተቀጣሪዎች ፍርድ ቤቶችን የተቀላቀሉት በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎቶች ወደ ተግባር እየገቡ ባሉበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆኑን ገልጸው፤ በቅንነት፣ በታማኝነትና በመልካም ሥነ-ምግባር ሕዝባቸውን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል።
ፍትሐዊ እና ዘመናዊ የዳኝነት ሥርዓት ለመገንባት የሚደረገው ጥረት በአዳዲስ ባለሙያዎች ብርታት ይበልጥ ይጠናከራል!
#federalcourt #legalprofessionals #judiciaryethiopia #reform #justicesystem #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
8 months ago
የበረሃው ምስጢር ፍፃሜ፦ የሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ሁለት ገፅታዎች
ጥር 26 በሊቢያ ናፉሳ ተራሮች ላይ የተሰማው የጥይት ድምፅ፣ የአንድን ሰው ህይወት ብቻ ሳይሆን የሊቢያን የ40 ዓመታት ታሪክ ዳግም የቀሰቀሰ ነበር።
የሙአመር ጋዳፊ ተመራጭ ልጅ ሰይፍ አል-ኢስላም በዚንታን ከተማ በሚገኝ መኖሪያው መገደሉ፣ ሀገሪቱን በሀዘን እና በደስታ ስሜት መካከል ከፍሏታል።
1. የሰይፍ አል-ኢስላም የግል ህይወት፦ በመጋረጃ የተሸፈነው ቤተሰብ
ሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ከወንድሞቹ በተለየ መልኩ የግል ህይወቱን ከሚዲያ እይታ ለማራቅ ይጥር ነበር።
ሚስት እና የፍቅር ህይወት፦ ሰይፍ አል-ኢስላም በለንደን በነበረው ቆይታ ከምዕራባውያን ጋር የነበረው ቅርርብ ለበርካታ ወሬዎች በር ከፍቶ ነበር። በተለይ ከእስራኤላዊቷ ተዋናይ ኦርሊ ዌይነርማን ጋር የነበረው ግንኙነት በወቅቱ መነጋገሪያ ነበር። ሆኖም በኋላ ላይ፣ ሰይፍ ከሩሲያዊት ሴት ጋር በድብቅ ትዳር መመስረቱን እና ይህች ሚስቱ በዚንታን በነበረበት አስቸጋሪ ዓመታት ከጎኑ እንደነበረች ይነገራል።
ልጆቹ፦ ሰይፍ ቢያንስ ሁለት ልጆች እንዳሉት የሚታመን ሲሆን፣ እነዚህ ልጆች በአባታቸው እና በአያታቸው ስም ምክንያት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እና የሚኖሩበት ስፍራ በሚስጥር ተይዟል። ከሊቢያ ውጭ (ምናልባትም በሩሲያ ወይም በአፍሪካ ሀገራት) በስደት እንደሚኖሩ ይገመታል። ሰይፍ በመጨረሻው የህይወት ዘመኑ የልጆቹን ድምፅ የሚሰማው በስልክ ብቻ እንደነበር የቅርብ ምንጮች ይገልጻሉ።
2. የተመዘገቡት ወንጀሎች፦ የጥቁር መዝገብ ዳሰሳ
ሰይፍ አል-ኢስላም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በሊቢያ ህዝብ ዘንድ ለፍርድ እንዲቀርብ የሚፈለግበት ዋነኛው ምክንያት በ2011 አመፅ ወቅት የፈፀማቸው ተግባራት ናቸው።
በሰው ልጆች ላይ የተፈፀመ ወንጀል፦ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ሰይፍን በግድያ እና በስቃይ (persecution) ወንጀል ይፈልገው ነበር። በሊቢያ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፈኞችን በከባድ መሳሪያ እንዲደበደቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል በሚል ይከሰሳል።
የደም ወንዝ ዛቻ፦ ሰይፍ በቴሌቪዥን ቀርቦ "ሊቢያን የደም ወንዝ እናደርጋታለን" በማለት የተናገረው ንግግር፣ በኋላ ላይ ለተከሰተው የንፁሃን እልቂት እንደ ማበረታቻ ተቆጥሮበታል።
የገንዘብ ምዝበራ፦ የጋዳፊ ቤተሰብ ከሊቢያ ህዝብ የነዳጅ ሀብት በመቶ ቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር አባክነዋል በሚል ከሚከሰሱት መካከል ሰይፍ ግንባር ቀደሙ ነበር።
3. "ተስፋ" ወይስ "አምባገነን"?
የሰይፍ አል-ኢስላም ታሪክ ያለ ሚዛናዊ እይታ ሊጠናቀቅ አይችልም። እርሱ በሊቢያውያን ዘንድ በሁለት መንገድ ይታያል፦
ሀ. እንደ ለውጥ ፈላጊ (The Reformist)
ከ2011 በፊት፣ ሰይፍ ሊቢያን ወደ ዘመናዊነት ለመቀየር የጣረ ሰው ተደርጎ ይታያል።
ሊቢያ የጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎቿን እንድታስወግድ በማድረግ ከዓለም ጋር እንድትታረቅ አድርጓል።
በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዲቋቋሙ ጥረት አድርጓል።
በለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ (LSE) የተማረው እውቀቱ፣ ሊቢያን ወደ ዴሞክራሲ ያሸጋግራታል የሚል ትልቅ ተስፋ በምዕራባውያን ዘንድ ጥሎ ነበር።
ለ. እንደ አምባገነን ቀጣይ (The Heir of Tyranny)
የስልጣን ወንበሩ ሲናወጥ ግን ያ የሰለጠነ ገፅታው ተቀይሯል።
ከህዝቡ ይልቅ ለቤተሰቡ ስልጣን ታማኝ በመሆን፣ በገዛ ወገኖቹ ላይ ጦርነት አውጇል።
"እኛ ካልገዛን ሊቢያ ትጠፋለች" የሚለው የአባቱ ፍልስፍና ተከታይ ሆኖ ተገኝቷል።
4. የዚንታን ፍፃሜ እና የሊቢያ የወደፊት እጣ
ሰይፍ አል-ኢስላም ከተገደለ በኋላ የሊቢያ ፖለቲካ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ገብቷል። የእሱ መገደል ለአንዳንዶች "የፍትህ መረጋገጥ" ሲሆን፣ ለሌሎች ደግሞ "ሊቢያን ሊያረጋጋ የሚችል ሰው ማጣት" ነው።
ለደጋፊዎቹ፦ ሰይፍ በትርምስ ውስጥ ለነበረችው ሊቢያ ብቸኛው መረጋጋት ሊያመጣ የሚችል "ልዑል" ነበር። ለእነሱ ሰይፍ የሞተው እንደ ሰማዕት ነው።
ለተቃዋሚዎቹ፦ የእሱ መገደል የጋዳፊን አገዛዝ ናፋቂዎች ተስፋ ያስቆረጠ እና ለወደፊት ዴሞክራሲያዊት ሊቢያ መንገድ የከፈተ ክስተት ነው።
ማጠቃለያ
የሰይፍ አል-ኢስላም ጋዳፊ ህይወት በለንደን የድሎት ህይወት ተጀምሮ በዚንታን በረሃማ ተራሮች ላይ በደም ተደምድሟል። የፈፀማቸው ወንጀሎች የታሪክ ጠባሳ ሆነው ቢቀሩም፣ በሊቢያ ፖለቲካ ውስጥ የነበረው ተፅዕኖ በቀላሉ የሚረሳ አይደለም። ዛሬ ላይ ሰይፍ የለም፤ ነገር ግን ሊቢያ አሁንም በእሱ "የደም ወንዝ" ዛቻ እና በነበረው "የለውጥ ተስፋ" መካከል የራሷን ማንነት ፍለጋ ላይ ትገኛለች።
የእሱ ሞት የአንድን ግዙፍ ቤተሰብ ታሪክ ቢዘጋም፣ የሊቢያ ህዝብ ግን አሁንም ወደፊት የሚመራውን እውነተኛ መሪ በመጠባበቅ ላይ ነው።

9 months ago
ቤትን ከመገንባት ወደ "ማምረት"! የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አስደናቂ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም 🏗️📈
"ከሪፎርሙ በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ39 እጥፍ የገቢ እድገት ተመዘገበ"
#ethiopia | የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ረሻድ ከማል በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ተገምግሟል። ኮርፖሬሽኑ በለውጥ ጎዳና ላይ መሆኑን የሚያረጋግጡ አዳዲስ ታሪካዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
የግማሽ ዓመቱ ዋና ዋና ድሎች፡-
💰 ታሪካዊ የገቢ እድገት:
በ6 ወራት ውስጥ 6.46 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል። ይህም፡-
የእቅዱን 99.4% ያሳካ ነው።
ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ147% እድገት አለው።
በ2010 ሪፎርሙ ሲጀመር ከነበረው ገቢ ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ39 እጥፍ ብልጫ አለው!
ብልሃት የተሞላበት ስራ (Zero Investment):
በኮሪደር ልማት ምክንያት የፈረሱ ሱቆችን ለመተካት፤ "በዜሮ ኢንቨስትመንት" ስልት 555 አዳዲስ የንግድ ሱቆች እየተገነቡ ነው። ይህም የገቢ መቀነስ ስጋትን ወደ እድል የቀየረ ብልህ እርምጃ ነው።
🏗️ ቴክኖሎጂ እና ዘመናዊነት:
የቤቶች እጥረት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ፤ ቤትን ከመገንባት ወደ "ማምረት" የሚያሸጋግረውን ዘመናዊ የ3D Printing ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር የማስገባት ወሳኝ ስራ ተከናውኗል።
📊 ጤናማ ፋይናንስ:
ተቋሙ ለተከታታይ 3 ዓመታት "ንጹህ የኦዲት አስተያየት" በማስመዝገብ የፋይናንስ ስርዓቱ ጤናማ መሆኑን አረጋግጧል።
በቀጣይም የገበያ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ እና የአቅርቦት ማዕከሉን በማጠናከር ለግንባታው ዘርፍ ግብዓት በብቃት ለማቅረብ አቅጣጫ ተቀምጧል።
#federalhousingcorporation #fhc #ethiopia #revenuegrowth #3dprintingconstruction #reform #drreshadkemal

አዲስ አበባ አህጉራዊ ኃላፊነቷን በብቃት በመወጣት፣ ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የጋራ መማማሪያ መድረክ መሆኗን ዳግም አረጋግጣለች።
ዛሬ በአህጉራችን መዲና አዲስ አበባ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ከመጡ ከንቲባዎች እና ከክልል አስተዳዳሪዎች ጋር ፍሬያማ የአቻ ለአቻ የመማማሪያ መድረክ እያካሄድን እንገኛለን።
በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) አማካኝነት በአፍሪካ ከተሞች የፋይናንስ አስተዳደር (Financial Management) አፈፃፀም ላይ በተካሄደው ጥልቅ የዳሰሳ ጥናት መሠረት፤ አዲስ አበባ ከተመዘነችባቸው 6 መስፈርቶች ውስጥ በ5ቱ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገቧ ልምድ እንድታካፍል ተመርጣለች።
ጥናቱ ከተካሄደባቸው ስድስት የአፍሪካ ከተሞች (ናይሮቢ፣ ዳሬሰላም፣ ሉሳካ፣ ኪጋሊ እና ያውንዴ) መካከል አዲስ አበባ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ቀዳሚ መሆን ችላለች። በተለይም የገቢ እና የፋይናንስ ሀብት አስተዳደርን በማዘመን ረገድ ከተማችን የጀመረችው ሪፎርም ውጤታማና ለአፍሪካ ከተሞች አርአያ መሆኑን የጥናቱ ግኝት አመላክቷል።
ይህ ስኬት፤ ከተማችን ከምትሰበስበው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ 71 በመቶውን ለልማት ሥራዎች በመመደብ፣ የዜጎችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስናደርግ የቆየነው የሪፎርም ጉዞ ውጤማነት ማሳያ ነው።
ዛሬ ከተለያዩ ከተሞች ለልምድ ልውውጥ የመጡት ተሳታፊ ከንቲባዎች እነዚህን የሪፎርም ሥራዎች በአካል በመጎብኘት፣ አዲስ አበባ በፋይናንስ እና በገቢዎች ስራ አቅሟን እንዴት ገንብታ ወደ ተግባራዊ ለውጥ እንደቀየረችው ሰፊ ተሞክሮ የምታካፍል ይሆናል።
ይህ መድረክ የአፍሪካ ከተሞችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጋራ የምንቀርጽበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
በመጨረሻም፣ ለዚህ ጥናት መሳካትና ለከተማችን እውቅና ለሰጡት ለተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA)፣ እንዲሁም የውጤቱ ባለቤት ለሆኑት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ለሥራ ባልደረቦቼ ሁሉ የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
አዲስ አበባ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ሆና ትቀጥላለች!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
Addis Ababa has once again reaffirmed its continental leadership by serving as a platform for mutual learning among our African brothers and sisters.
Today, in our continental capital, we are hosting a productive peer-to-peer learning forum with mayors and regional administrators from various African cities.
According to an in-depth survey conducted by the United Nations Economic Commission for Africa (UNECA) on the financial management performance of African cities, Addis Ababa was selected to share its experience after achieving outstanding results in five of the six key metrics evaluated.
Among the six African cities surveyed (Nairobi, Dar Es Salaam, Lusaka, Kigali, and Yaoundé), Addis Ababa emerged as the top performer. The findings specifically highlighted that the reforms our city initiated in modernizing revenue and financial resource management are both effective and serve as a blueprint for other African cities.
This success is a testament to the effectiveness of our reform journey, through which we have allocated 71% of the city’s total revenue to development projects to ensure the sustainable benefit of our citizens.
The visiting mayors and participants will personally tour these reform projects today. Addis Ababa will share its extensive experience in building financial and revenue capacity and translating that capacity into tangible, transformative change.
This forum represents a historic opportunity for us to collectively shape the future of African cities.
Finally, I would like to extend my deepest gratitude to the UNECA for conducting this study and recognizing our city, as well as to the residents of Addis Ababa and my colleagues, who are the true owners of this achievement.
Addis Ababa will continue to be a symbol of African prosperity!
May God bless Ethiopia and its people!

ከ1 ቢሊዮን ወደ 850 ሚሊዮን ዶላር፦ የኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ እዳ እንዲቀንስ ስምምነት ተደረሰ
ኢትዮጵያ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጋር ስታደርገው የነበረው የብድር ሽግሽግ ድርድር ስኬታማ ውጤት ማስመዝገቡ የተገለጸ ሲሆን፣ በመሰረታዊ ነጥቦች ላይ በተደረሰው ስምምነት መሰረት የሀገሪቱ አጠቃላይ የዩሮ ቦንድ እዳ መጠን በ15 በመቶ ወይም በ150 ሚሊዮን ዶላር እንዲቀንስ ተደርጓል።
ዓለም አቀፍ ጠበቆችን ቀጥራ ከአበዳሪዎች ጋር ስትደራደር የቆየችው ኢትዮጵያ፣ የ1 ቢሊዮን ዶላር እዳ እንዲሸጋሸግላት ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን የድርድሩ ሰነድ የሚያሳይ ሲሆን ይህም ለሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።
በስምምነቱ መሰረት ዋናው የብድር መጠን (Haircut) ተደርጎለት ወደ 850 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ እንዲል የተወሰነ ሲሆን፣ ይህ እዳ እስከ 2020 የኢትዮጵያ በጀት ዓመት ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ ታቅዷል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል በሦስት ዙር መከፈል የነበረበትና ሳይከፈል በመቆየቱ ኢትዮጵያን ለ "ቴክኒካዊ ውድቀት" (Technical Default) ዳርጓት የነበረው የ99 ሚሊዮን ዶላር የወለድ እዳ፣ አሁን ላይ ሀገሪቱ በአንድ ጊዜ ለመክፈል መስማማቷ በሰነዱ ላይ ሰፍሯል።
የረጅም ጊዜ ክፍያውን በተመለከተ፣ በቀጣዮቹ 8 ዓመታት ውስጥ የተሻለ የወጪ ንግድ ገቢ ከተገኘ ከገቢው 2.5 በመቶ በመቀነስ በዓመት 180 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወስኗል።
ይህ አሃዝ አበዳሪዎች ቀደም ሲል ከጠየቁት የ4.75 በመቶ የክፍያ ምጣኔ በእጅጉ የቀነሰ ሲሆን፣ ይህም በIMF የኢኮኖሚ ግምገማዎች ላይ ተመስርቶ የቀረበ የክፍያ አማራጭ መሆኑ ታውቋል። ስምምነቱ በይፋ ሥራ ላይ እንዲውልም የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት
(IMF) የመጨረሻ ይሁንታ እየተጠበቀ ይገኛል።
ይህ የብድር ሽግሽግ ስምምነት ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ገበያ በድጋሚ ለመመለስ ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።
የእዳ ጫናው መቀነሱ እንደ Fitch እና S&P ያሉ ተቋማት ለሀገሪቱ የሚሰጡትን የክሬዲት ደረጃ ሊያሻሽለው እንደሚችል የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ ላይ የነበረውን የብድር አለመክፈል ስጋት በመቀነስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) እንዲጨምር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራም የሚል ትንበያ ባለሙያዎች ይሰጣሉ።
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2014 የገባችበት የ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ እዳ በታህሳስ 2023 መከፈል የነበረበት ቢሆንም፣ በወቅቱ በነበረው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ሳይከፈል መቆየቱ ይታወሳል። ይህ አዲስ ስምምነት ሀገሪቱ ካለባት የብድር ጫና ወጥታ የጀመረችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ (Macroeconomic Reform) በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚረዳ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን የድርድሩ ውጤት ያመለክታል።

1 year ago
የሼህ አል-አሙዲ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ74 ሺህ ለሚልቁ ሰራተኞቹ በየወሩ ከ500 - 600 ሚሊዮን ብር ደሞዝ እንደሚከፍል ምን ያህሎቻችን እናውቃለን?
#ethiopia | ኢትዮጵያም የእናታቸው አደራ ሆናባቸው አል-አሙዲ ሀገርን በኢንቨስትመንት ረገድ ለመሳተፍ በኢትዮጵያ ከተሰማሩበት ጊዜ አንስቶ በሶስት ምዕራፍ የፖለቲካ ትርጓሜ እየተሰጠባቸው ብዙ ውጣ ውረድ ገጥሟዋል፤ ሸራተን ሆቴል እስኪዘጋ ድረስ፡፡
አል - አሙዲን ከሳኡዲ ስለመጡ “ወሀቢያን ወደ ኢትዮጵያ ሊያስፋፋ ነው፤ የእስልምና አክራሪነትን ሊያመጣ ነው” በሚለው ጥርጣሬ ሼራተን ለጊዜው እንዲዘጋ ተወስኖ እና ሆቴል ሳይሆን መስጊድ ነው የሚል ወሬም ተናፍሶ ሆቴሉ ተዘግቶ ከተፈተሸ በኋላ ተረጋግጦ እንደገና ተፈቅዶ መከፈቱንስ እናውቅ ነበር?
ያኔ የኢህአዲግ መንግስትን ይቃወሙና ተችተው ይጽፉ የነበሩ እንደ እነ ጋሽ ጻውሎስ ኞኞ ያሉትን ሼሁ ጀርመን ልከው ማሳከማቸው፤ ቀጥሎም አርቲስቶቹን እነ ታማኝ በየነና ፀሀዬ ዮሀንስ ላይ ከመንግስት ሹሞች ጫና ሲበዛባቸው አላሙዲን አሜሪካ ወስደው መደገፋቸውን ተከትሎ በመንግስት በኩል ጥርጣሬው መባሱን፤ በዚህ ሳያበቃም - አፍቃሬ ደርግ ተብለው እንደነበርም በሚድሮክ በጣም መረጃ ሰጪ ዶክመንተሪ ላይ ተጠቅሷል፡፡
“አፍሪካ ከልቤ ብትሆንም - ኢትዮጵያ ግን የእናቴ አደራ ናት አሉ” - ቢሊየነሩ ሼህ መሀመድ አላሙዲን፡፡
ለኢህአዲግ መንግስት ሼህ አላሙዲን በ1997 ምርጫ ድጋፍ ሁነት ላይ መገኘታቸውን ተከትሎ ብዙ ሰው ሚድሮክ የህወሀት ነው፣ የወያኔና የአዜብ መስፍን ነው እስከሚለው ድምዳሜ ድረስ የዘለቀው ነቆራ ሚድሮክን ከፖለቲካ ፓርቲ ጋር አላጥፎ በባለሀብቱና በድርጅቶቹ ላይ ከፍተኛ ፈተና ደቅኖም ማለፉን ዶክመንተሪው ከትቦታል፡፡
በሚድሮክ ዶክመንተሪ ላይ እንደ ወግ በጣም ቀልብን በሚገዛ ሁነት ማብራሪያውን የሚሰጡት አቶ ጀማል አህመድ እንዲህ ሲሉ በአጽንኦት ያነሳሉ - “አላሙዲ ለኢትዮጵያ ስላላቸው በጎ ሕልም በህዝቡ ዘንድ በቂ ግንዛቤ አልተያዘውም፤ እናም አሁንም ድረስ ፈተና ሆኖ የቀጠለው አብዛኛው የሼሁን የሀገር ወዳድነት ውስጠታቸውን አልተረዳውም”
መንግስት በደንብ ያመናቸው በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ነው ይሉና የሚድሮኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሲያብራሩ - “በዚህ ወቅት ሀገሪቱ ከባድ የፋይናንስ ማጥ ውስጥ ነበረችና አልአሙዲ የተጠየቁትን ድጋፍ ሁሉ በደስታ በማድረግ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን በቁርጠኝነት ቆመዋል”፡፡
የሚያደርጉት ድጋፍ ሼህ አላሙዲን የማህበራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት የሀገር ውለታ የዋሉ ሰዎችን መደገፍ መውደዳቸው ግን በአንዳንድ ፖለቲከኞች በበጎ ጎን አለመታየቱ ፈተና አመጣባቸው በማለት በቁጭት የሚያነሱት ስራ አስፈጻሚው አቶ ጀማል ለካ ደግነትም ፈተና መሆኑን ያወቅሁት በእሳቸው ነው በማለት በአግራሞት በምልሰት ሄደው ያወሱታል፡፡
ሌላው በሚድሮክ የውስጥ ድርጅት የአስተዳደራዊ ልቅ አሰራር ችግርና ሙስና ብሎም የገንዘብ ብክነትና ስርቆትን ተከትሎ ኩባንያዎቹ የመውደቂያ ቀናቸውን የሚቆጥሩ ነበሩና ከግራ አጋቢ ሁኔታ የገባው ሚድሮክ የራሱን customized መዋቅር አበጅቶ በስሩ ያሉ 45 ድርጅቶች በ6 ዘርፎች ተጣምረው በ2012 ዓ.ም መጨረሻ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ መፈጠሩ ይነገራል፡፡
ከወሎዋ ወልዲያ ትውልዳቸውን አድርገው ደሴ ወ/ሮ ስህን ት/ቤት ተከታትለው - የስራን ልምድ ከአንድ ስዊድን ካለ ትልቅ ኩባንያ ተቀጥረው ስለቢዝነስ ተሞክሮ ጨብጠዋል፡፡
አውሮፓ ላይ ነው ሀብት ቢያፈሩም ወደ ኢትዮጵያ ግን መጥተው አያውቁም ነበር፡፡ ይሁንና አንድ ቀን ግን እናታቸው የጤና አያያዛቸው አላምር አላቸው፤ እንግሊዝ ሀገር ለህክምና ከመሄዳቸው በፊት ግን ኢትዮጵያ ውሰዱኝ አሉ፡፡
ኢትዮጵያ መጥተው መርካቶን ጭምር ጎበኙ እና “ልጄ አደራህን!” አሉ ለሼህ አላሙዲን - “አደራ ሀገርህን ኢትዮጵያን አግዝ!” የሚል አደራ ተቀበሉ - ይህ የእናቲቱ አደራ አላሙዲንን ከበዳቸው፡፡
ለምን መንግስት ብቻ - የግል ባንክ ለምን አይኖርም ኢኮኖሚው እንዲያድግ መደገፍ አለበት መንግስት የሚለው ሌላ የተሳሳተ የፖለቲካ ስሌት አስነስቶባቸው - ስማቸውንም የጠለሸበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር - ከበጎ ምክር ይልቅ ጥርስ አስነከሰባቸው - በዚህ መዘዝ የስራቸው ቀዳሚ የነበረው የመጀመሪያውን ሼራተን ሆቴል ታሽጎባቸው ነበር፤ የተሳሳተ ስሌቱመ ስማቸውን አጠለሸባቸው፡፡
እኔ የተሸለምኩት መንግስት ኢትዮጵያ ሀገርህ ናት - ናና አልማ ስባል ነው - ለነገሩ የተወለድኩባትን እናት ሀገሬን እንዴት ነው የምረሳው ብለው ነበር በአንድ ሽልማት ስነ ስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር፡፡
ለበርካታ ወገኖች ስራ እድል በመፍጠር ኢትየጵያን ከድህነት መንጋጋ ፈልቅቆ ማውጣት ቅድሚያ ግዴታዬ ነው ይላሉ ዛሬም ድረስ ሼህ አል-አሙዲን፡፡
የሻይና ቡና ተክል ልማት ላይ በመሰማራት ኢትዮጵያን በዚህ ዘርፍ በአለም ቀዳሚ ረድፍ ላይ ማሰለፍ ህልማቸው ነበር፡፡
ሁሌም በተስፋ ይስተካከላል የጊዜ ጉዳይ ነው ይሉኝ ነበር በማለት አቶ ጀማል የሼሁን ጨለምተኛ አለመሆን ይገልፁና አሁን ያለው ፈተና ደግሞ ሳኡዲ ውስጥ ካለ ችግር ጋር የተያያዘ እና ከዛ ሀገር እንዳይወጡ በመደረጉ ድርጅቶቻቸውን ተከታትለው እንዳይመሩ እንደሆነ በቅሬታ ያነሳሉ፡፡ ይሁንና አሉ አቶ ጀማል - “አልአሙዲን ሁሌም ይፈተናሉ፤ አላህምዱሊላሂ ሁሌም ግን ፈተናውን ያልፉታል”፡፡
መንግስት ትኩረት የሰጣቸው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መዋቅር (home grown economic reform pillars) ከሚባሉት ከአይቲ በስተቀር በአራቱ ስለምንሳተፍ ትኩረቱ ለእኛ ጠቃሚ ነው ባይ ናቸው ከፍተኛው አመራር፡፡
ለ22 አመታት በኪሳራ የኖረው ኤልፎራ በዶሮ ዝርያ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚውን ስፍራ ስለመያዙ ተጠቅሷል፡፡ ጫጩትን ከውጭ ለምታስመጣው ኢትዮጵያ መድህን ሊሆን ጥረት ላይም ይገኛል፡፡ የሻይ ቅጠል ምርትን ከኬንያ እያስመጣች የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን በሚድሮክ ፍላጎቷን የሚሞላ አቅርቦትና የውጭ ምንዛሪ ገቢም እየተገኘበት ነው፡፡
የአፍሪካ ቢዝነስ ሊደርሺፕ ኦርጋናይዜሽን የአመቱ ምርጥ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሚል “CEO of the Year” በሚል ሚድሮክ የእውቅና ሽልማት እና በቅርቡም እንዲሁም የአፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ሌላ የእውቅና ሽልማት አንስቷል፡፡
ፋብሪካዎቹ ጋ ሲኬድ - እኛ የዚህ ድርጅት ባለቤቶች ነን - የዚህ ድርጅት እድገት በእኛ ይወሰናል - የሚል አባባል አለ - ሆራይዘን ጋ የነበሩ ሰራተኞች የፈጠሩት መሪ ቃል ነው - ሌሎቹም ተጋሩትና ቀጠሉ - ጀማል አዝዞት የሆነ አይደለም፡፡
ሚድሮክ ባለፉት አስር አመታት ሰርቶ አምርቶ ካመጣው የሽያጭ ገቢ በላይ የዘንድሮ አንድ አመቱ ውጤት እጅግ ያስከነዳልም ተብሏል፡፡
በውጭ አልሚነት የተመዘገቡት ሼህ አላሙዲን ብዙ ሚሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ይዘው መጥተው ድርጅቶች ከፍተው አምርተው በውጭ ምንዛሪም ሸጠው ከፍተኛ ገቢም አግኝተዋል፤ ግን አንድ ዶላር ከሀገር አውጥተው አያውቁም ተብሎላቸዋል፡፡
የዚህን እውነትነት ለማረጋገጥ አሉ አቶ ጀማል በዶክመንተሪው - “የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክም ጋ ሄዶ ማረጋገጥ ይቻላል፤ ከእኛ ብር ይወስዱ ስላልነበር፤ ማበረታቻ ቲፕ የሚሰጡት እንኳ በዩሮ ነበር፡፡
(Via:- ጋዜጠኛ እሸቱ ገለቱ)

ወንጌላዊ ኦኔስሞስ ነሲብና ዳግማዊ ምኒልክ፣
(ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ በእንግሊዝኛ እንደጻፉት፣ ሲሣይ ተፈራ መኮንን ወደ አማርኛ እንደተረጎመው)
#ethiopia | እንደ ልጅ ልጃቸው አቶ ኢዶሳ ገመቺስ ከሆነ ኦኔስሞስ ነሲብ የተወለዱት በኢሉባቦር ሁርሙ በሚባለው አካባቢ ሲሆን ዘመኑም 1842 ዓ.ም ነው፡፡ የኦኔስሞስ ነሲብ የልጅነት ስማቸው ሂቃ ሲሆን ሂቃ ማለትም በኦሮምኛ ፈቺው ወይም ተርጓሚው እንደማለት ነው፡፡ ወላጆቻቸው እንደትንቢት ሂቃ ብለው የሰየሟቸው ኦኔስመስ፣ ልክ እንደስማቸው የመጀመሪያውን የመጽሀፍ ቅዱስ የኦሮሚኛ ትርጉም በማዘጋጀታቸው ታረክ ሲያስታውሳቸው ይኖራል፡፡
የሂቃ የልጅነት ጊዜ አሳዛኝ ነበር፡፡ አባታቸው በ4 አመት እድሜያቸው እንደሞቱ ሂቃ በባሪያ ፈንጋዮች ታፍነው ተወሰዱ፡፡ ጠረፍ እስከሚደርሱ ድረስም በተለያዩ ጌቶች ስር በባርነት አድረዋል፡፡ አንዳንዶች ሂቃ ነጻ ከመውጣታቸው በፊት 4 ጊዜ በባርነት እንደተሸጡ ሲጽፉ ሌሎች ደግሞ የተሸጡበትን ጊዜ 8 ያደርሱታል፡፡ በመጨረሻም ምጽዋ ላይ በነበረው የፈረንሳይ ቆንሲል ዌርነር ሙዚንገር አማካኝነት ሂቃ ከባርነት ነጻ ወጥተዋል፡፡
ዌርነር ሙዚንገር በጥቅምት ወር 1863 ዓ.ም ከባርነት ነጻ የወጡትን ሂቃ ለስዊድናውያን ሚሲዮኖች ያስረከቡ ሲሆን የሂቃም ህይወት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በዘላቂነት መለወጥ ጀመረ፡፡ በመጋቢት ወር 1864 ዓ.ም የፋሲካ ቀን ዋና ጠባቂ ሆነው በተመደቡላቸው ሉንድሃል አማካኝነት ሂቃ ኦኔስሞስ በሚል አዲስ ስም እንዲጠመቁ ተደረገ፡፡
ኦኔስሞስ ነሲብ በ1868 ዓ.ም ወደ ስዊድን የተላኩ ሲሆን በዛም ለ5 አመት ያህል ሃይማኖታዊ ትምርት ተከታትለዋል፡፡ ከስዊድን እንደተመለሱም የአጼ ቴዎድሮስ የቀድሞ ጸሀፊና የስዊድን ሚሽን ት/ቤት መምህር የነበሩትን የጎጃሙን አለቃ ኃይሉ ልጅ ምህረት ሐይሉን አገቡ፡፡ ከዚህ በኋላም ከንቲባ ገብሩ አቅደው ከፍጻሜ ያላደረሱትን መጽሀፍ ቅዱስን ለኦሮሞ ህዝብ የማስተማር እቅድ በትውልድ አካባቢያቸው ለመፈጸም ሂቃ ወደዛው ለመጓዝ ወሰኑ፡፡
ነገር ግን አጼ ዮሀንስ የሚሲዮናውያንን እንቅስቃሴ አግደው ስለነበር፣ ኦኔስሞስ ወደ ወለጋ ለመጓዝ በቅድሚያ በቀይ ባህር ቀዝፈው ሱአኪን ወደምትባለው የሱዳን ወደብ መጓዝ ነበረባቸው፡፡ ከሱዳን ግዛት ወደ በርበር ካቋረጡ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ጠረፍ ወደ ሚያደርሰው አባይ በመጓዝ በታህሳስ ወር 1875 ዓ.ም ፋማካ ተብላ ወደምትጠራው የጠረፍ ከተማ ደረሱ፡፡ ነገር ግን ወደ ኢትዮጵያ ጠረፍ ማቋረጥ ከጀመሩ በኋላ ችግር እንዳለ በመስማታቸው ለመመለስ ተገደዱ፡፡
የመጀመሪያው ሙከራ ከከሸፈ ከ3 አመት በኋላ በ1878 ዓ.ም ኦኔስሞስ በታጁራና ሸዋ አድርገው ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ለመጓዝ ያደረጉት ጥረትም ንጉሥ ምኒልክ አስቀድመው የሰጡትን ተስፋ በሚጻረር መልኩ የሸዋ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ማቴዎስ ባሰሙት ተቃውሞ ምክንያት ውጤት አልባ ሆነ፡፡ በትውልድ አካባቢያቸው በአካል በመገኘት የወንጌልን ት/ት ለማስፋፋት በተደጋጋሚ ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ ያዘኑት ኦኔስሞስ ነሲብ መጽሀፍ ቅዱስን የትውልድ አካባቢያቸው ህዝብ በሚገባው የኦሮምኛ ቋንቋ ለመተርጎም ወሰኑ፡፡
የ4 አመት ህጻን ሆኖ የትውልድ አካባቢውን ለለቀቀ ሰው መጽሀፍ ቅዱስን ወደ ኦሮምኛ መተርጎም ቀላል ባይሆንም፣ ኦኔስሞስ አስቴር ጋኖ በተባሉ የሊሙ ኦሮሞ ወዳጃቸው እየታገዙ የትርጉም ስራቸውን ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻም ኦኔስሞስ አዲስ ኪዳንን እና ብሉይ ኪዳንን በቅደም ተከተል በ1885 ዓ.ም እና በ1891 ዓ.ም ወደ ኦሮምኛ በመተርጎም የትርጉም ስራቸውን አጠናቀቁ፡፡ የትርጉም ስራቸውን ለማከናወን በዋነኛነት የተጠቀሙት የአማርኛውን መጽሀፍ ቅዱስ ሲሆን በስዊድን ቋንቋ የተዘጋጀውን መጽሀፍ ቅዱስ ደግሞ ለማመሳከሪያነት ተጠቅመዋል፡፡
የመጀመሪያ ሚስታቸው ወ/ሮ ምህረት ከሞቱ ጥቂት አመታት በኋላ ኦኔስሞስ ሊዲያ ዲምቦ የተባሉትን የወለጋ ሲዮ አካባቢ ተወላጅ አገቡ፡፡ በአስመራ ከተማ ይገኙ ለነበሩ ወደ 500 የሚጠጉ የኦሮሞ ኮሚኒቲ አባላትም የወንጌል ትምህርትን ማስተማር ጀመሩ፡፡ ይህም የትውልድ አካባቢያቸውን ህዝብ በአካል በማስተማር ውጤታማ ስራ ከመስራታቸው በፊት በመፈጸሙ በጎ መንደርደሪያ ሆነላቸው፡፡
በ1885 ዓ.ም ኦኔስሞስ ሚስታቸውን፣ 3 ልጆቻቸውንና አዲስ ሰራተኞቻቸውን በመያዝ ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ተጓዙ፡፡ በአዲስ አበባም በከንቲባ ገብሩ አማካኝነት ኦኔስሞስ ከዳግማዊ ምኒልክና ከአቡነ ማታዎስ ጋር ተገናኙ፡፡ ኦኔስሞስም ለዳግማዊ ምኒልክ የተረጎሙትን የኦሮምኛ መጽሀፍ ቅዱስ ኮፒ በስጦታ አበረከቱ፡፡ በመጨረሻም ኦኔስሞስ በሚጓዙበት ሁሉ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የሚያዘውን የዳግማዊ ምኒልክ ደብዳቤ ታጥቀው ወደ ወለጋ ተጓዙ፡፡
በወለጋ እንደደረሱም በደጃዝማች ገብረ እግዚአብሔር ሞሮዳ/ኩምሳ ሞሮዳ ከፍተኛ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ ኦኔስሞስ ለመጓዝ ያሰቡት ወደ ትውልድ አካባቢቸው ኢሉባቦር የነበረ ቢሆንም በዳ/ምኒልክና በደጃ/ኩምሳ ሞረዳ በተደረላቸው የክብር አቀባበል ምክንያት ወንጌላዊ ስራቸውን በወለጋ ጀመሩ፡፡ ነጆ አካባቢ በምትገኘው ቦጂ ለኦኔስሞስ መሬት የተሰጣቸው ሲሆን በዛም የማስተማር ስራቸውን ጀመሩ፡፡
የኦኔስሞስን ሃይማኖታዊ ትምህርት በአደጋነት የተመለከቱ የኦርቶዶክስ አባቶች ባቀረቡት ክስ ምክንያት ኦኔስሞስ ወደ አዲስ አበባ ከተጠሩ በኋላ በአቡነ ማቴዎስ የእስራት ፍርድ ተፈረደባቸው፡፡ ነገር ግን ዳግማዊ ምኒልክ የአቡኑን ፍርድ ባለመቀበል ጉዳዩ በድጋሚ በአፈ ንጉሥ ኢስጢፋኖስ እንዲመረመር አዘዙ፡፡ በዚሁ መሰረት አፈ ንጉሡ ጉዳዩን በድጋሚ መርምረው ኦኔስሞስን ከቀረበባቸው ክስ በነጻ አሰናበቱ፡፡
ዳግማዊ ምኒልክ ከዚህም አልፈው ለኦኔስሞስ በንግድ ሚኒስቴር ስራ እንዲሰጣቸው አዘው የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የነበሩት ሹማምንት ኦኔስሞስ በንግድ ጉዳይ ለመስራት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት የላቸውም በሚል የምኒልክን ትዕዛዝ ሳይፈጽሙ ቀርተዋል፡፡ ኦኔስሞስ ነሲብ ወደ ወለጋ ተመልሰው በተለይም ከልጅ ኢያሱ ዘመን ጀምሮ በነጻነት ሲያስተምሩ ከቆዩ በኋላ በሰኔ ወር 1923 ዓ.ም በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ነፍስ ይማር!
ምንጭ፣ Pioneers of Change in Ethiopia: The Reformist Intellectuals of the Early 20th Century, Prof Bahru Zewde, PP.46-49
ምስል፦ ኦኔስሞስ ነሲብ ከባለቤታቸውና ከልጆቻቸው ጋራ ኤርትራ ውስጥ የተነሱት ፎቶግራፍ ነው፡፡ ፎቶው የመቼ እንደሆነ አልተገለጸም። #jemal_abdulaziz

Comments