የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊከተል ይችላል፦ IMF
*********************
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ፣ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ፣ የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊከተል እንደሚችል አስጠነቀቁ።
ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ ንረቱ ተባብሶ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ እስከ 125 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እያገረሸ ያለው የዋጋ ግሽበትም በዚሁ ከቀጠለ በዓለም ዙሪያ የኑሮ ውድነቱን ይበልጥ ያባብሰዋል ነው ያሉት።
IMF ግጭቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይቆማል በሚል ቀደም ሲል አስቀምጦት የነበረው የ3.1% አማካይ ዕድገት እና የ4.4% አማካይ ግሽበት ትንበያም አሁን ባለው ሁኔታ ሊሳካ እንደማይችልና ሁኔታው ከዚህ የከፋ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ጦርነቱ በቶሎ ካልቆመ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት ይበልጥ እየቀነሰና የዋጋ ግሽበት ደግሞ ይበልጥ እየጨመረ መሄዱ የማይቀር ነው ብለዋል።
በሀና ምንዳሁን
#middleeastwar #oilprice #economy #imf #ebc

3 months ago