5 months ago
የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊከተል ይችላል፦ IMF
*********************
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ፣ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ፣ የከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊከተል እንደሚችል አስጠነቀቁ።
ጦርነቱ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ ንረቱ ተባብሶ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ እስከ 125 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ እያገረሸ ያለው የዋጋ ግሽበትም በዚሁ ከቀጠለ በዓለም ዙሪያ የኑሮ ውድነቱን ይበልጥ ያባብሰዋል ነው ያሉት።
IMF ግጭቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይቆማል በሚል ቀደም ሲል አስቀምጦት የነበረው የ3.1% አማካይ ዕድገት እና የ4.4% አማካይ ግሽበት ትንበያም አሁን ባለው ሁኔታ ሊሳካ እንደማይችልና ሁኔታው ከዚህ የከፋ እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ጦርነቱ በቶሎ ካልቆመ የዓለም ኢኮኖሚ ዕድገት ይበልጥ እየቀነሰና የዋጋ ግሽበት ደግሞ ይበልጥ እየጨመረ መሄዱ የማይቀር ነው ብለዋል።
በሀና ምንዳሁን
#middleeastwar #oilprice #economy #imf #ebc

6 months ago
ቶታል ኢነርጂስ እና የቱርኩ ቲፓኦ (TPAO) በጥቁር ባሕር የጋራ የነዳጅ ፍለጋ ለማድረግ ተስማሙ
#ethiopia | የፈረንሳዩ የኢነርጂ ግዙፍ ቶታል ኢነርጂስ እና የቱርክ ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ (TPAO) በጥቁር ባሕር ውስጥ የሃይድሮካርቦን ፍለጋ ለማካሄድ የሚያስችል የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ተፈራረሙ። ሰኞ ዕለት ይፋ የሆነው ይህ ስምምነት የሁለቱን ኩባንያዎች የቴክኒክ ትብብር የሚያጠናክርና በጥቁር ባሕርም ሆነ በሌሎች ዓለም አቀፍ መድረኮች በጋራ ለመሰማራት የሚያስችል ማዕቀፍ የፈጠረ ነው።
ይህ ስምምነት ባለፈው ወር በቱርክ የኢነርጂ ሚኒስትር ቀርቦ የነበረውን የትብብር ሐሳብ ወደ ተግባር የለወጠ መሆኑ ተገልጿል።
የሁለቱ ኩባንያዎች ስምምነት ይፋ በሆነበት ወቅት፣ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ መናር ታይቷል። አሜሪካ በኢራን ላይ የባሕር ላይ እገዳ ልታደርግ ትችላለች በሚል በተፈጠረ ስጋት፣ የነዳጅ ዋጋ በ 8% ጭማሪ አሳይቶ አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ከ 102 ዶላር በላይ ተመዝግቧል።
ይህን ተከትሎ የዓለም አገራት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፦
በነዳጅ ዋጋ መናር ሳቢያ ለዜጎቿ የሚሆን የ 1.9 ቢሊዮን ዶላር የዋጋ ማቅለያ ዕርዳታ ለማድረግ አቅዳለች።
ከሰባት ዓመታት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢራን ነዳጅ መረከብ መጀመሯ ታውቋል ሲል የዘገበው ካፒታል ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #totalenergies #tpao #blacksea #oilprice #energycrisis #turkey #iran #globalnews #ኢነርጂ #ነዳጅ #ጥቁርባሕር

የዓለም የነዳጅ ዋጋ እየወረደ ነው
#ethiopia | በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን ተከትሎ፣ በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ እያሳየ ይገኛል።
በዘገባዎች መሠረት፣ የአሜሪካው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት (WTI) የነዳጅ ዋጋ የ18% ቅናሽ በማሳየት ወደ 92.60 ዶላር ወርዷል።
በተመሳሳይ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋም በ6% ቀንሶ በአሁኑ ወቅት አንድ በርሜል 103.40 ዶላር እየተሸጠ ይገኛል።
ለነዳጅ ዋጋው መውረድ በዋነኝነት የሚጠቀሰው የሁለቱ ሀገራት ስምምነት ሲሆን፣ በቀጣይም ለዓለም የነዳጅ ዝውውር ቁልፍ የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ ለሁሉም መርከቦች ክፍት ሆኖ ነጻ እንቅስቃሴ ሲጀመር የዋጋ ቅናሹ ይበልጥ ሊጨምር እንደሚችል የዘርፉ ተንታኞች ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #oilprice #worldnews #economy #fuel #globalmarket #breakingnews #energy #internationalrelations

7 months ago
🚨 1,900 መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ ቆመዋል
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ውጥረት በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየፈጠረ ይገኛል። ከየካቲት 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተከፈተውን መጠነ-ሰፊ ጥቃት ተከትሎ የባህር ላይ ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ቆሟል።
ወደ 1,900 የሚጠጉ የንግድ መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ እና በፋርስ ባህረ ሰላጤ አካባቢ መንቀሳቀስ አቅቷቸው ቆመዋል።
ኢራን "ከጥቃት አድራሾቹ አገራት ጋር ንክኪ ያላቸው መርከቦች በወሳኙ የሆርሙዝ ሰርጥ እንዳያልፉ" መከልከሏ ለቀውሱ ዋነኛ መንስኤ ሆኗል።
እንቅስቃሴያቸው ከተገታው መርከቦች መካከል ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ፣ የኬሚካል እና የተለያዩ የንግድ ዕቃዎችን የያዙ መርከቦች ይገኙበታል።
ይህ እገዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲንር ከማድረጉም በላይ፣ ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት (Supply Chain) ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል እየፈጠረ ይገኛል። ሁኔታው ካልረገበ የዓለም ኢኮኖሚ የከፋ ጉዳት ሊገጥመው እንደሚችል ስጋቶች እየጨመሩ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #middleeastcrisis #globaltrade #oilprice #hormuzstrait #breakingnews #shippingindustry #internationalrelations #energysecurity

ስሪላንካ የነዳጅ እጥረትን ለመቋቋም የሥራ ቀናትን ቀነሰች
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን ቀጥሏል። የነዳጅ ዋጋ በአንድ በርሜል 100 ዶላር መሻገሩንና በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚደረገው የነዳጅ ትራንስፖርት መገታቱን ተከትሎ፣ የእስያ አገራት ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ተጋርጦባቸዋል።
ይህን ተከስቶ ያለውንና ሊመጣ የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመቋቋም ስሪላንካ ጥብቅ የቁጠባ እርምጃዎችን መውሰድ ጀምራለች።
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች በየሳምንቱ ረቡዕ ዝግ እንዲሆኑ መወሰኑን የሀገሪቱ መንግሥት አስታውቋል። በዚህም መሠረት በሀገሪቱ የሥራ ቀናት ወደ አራት ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል።
ይሁን እንጂ እንደ ጤና እና ኢሚግሬሽን ያሉ ወሳኝ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዚህ ውሳኔ ሳይካተቱ መደበኛ ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
ከሥራ ቀን ቅነሳው በተጨማሪ፣ ስሪላንካ ዜጎች በኮታ ነዳጅ የሚገዙበትን "ብሔራዊ የነዳጅ ፓስ" ምዝገባ በይፋ ጀምራለች። በዚህም መሠረት፦
* ለግል መኪና 15 ሊትር
* ለሞተር ሳይክል 5 ሊትር ብቻ በሳምንት እንዲፈቀድ ተወስኗል።
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አኑራ ኩማራ ዲሳናያኬ "ለከፋው ሁኔታ መዘጋጀት አለብን" ሲሉ ለዜጎቻቸው ጥሪ አቅርበዋል። ስሪላንካን ጨምሮ ሌሎች የእስያ አገራትም ተመሳሳይ ጥብቅ የቁጠባ እርምጃዎችን ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #srilanka #fuelcrisis #globaleconomy #energysaving #asianews #oilprice

Sponsored by
Surafel
7 months ago
የነዳጅ ዋጋ ያናረው የሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ ውጥረት
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ወታደራዊ ግጭት በዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት እና ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል። በተለይም በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ እና በነዳጅ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች መቀጠላቸውን ተከትሎ፣ የነዳጅ ዋጋ ዛሬ ማለዳ ባልተጠበቀ ሁኔታ የ9 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በአንድ በርሜል ከ100 ዶላር በላይ ሆኗል።
የወቅታዊው ቀውስ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ መዘጋት፦ የዓለምን 20 በመቶ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት የሚያስተላልፈው ስልታዊው የሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ በኢራን ከፍተኛ ቁጥጥር ስር መውደቁ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲቆም አድርጓል።
* የመሠረተ ልማት ጥቃቶች፦ ኢራን በዱባይ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ በጭነት መርከብ ላይ ጥቃት ከመሰንዘሯም ባለፈ፣ በባሕሬን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና በሳዑዲ ዓረቢያ ግዙፍ የነዳጅ ቦታዎች ላይ የድሮን ጥቃቶችን ሰንዝራለች።
* የኢራቅ የነዳጅ ምርት መቋረጥ፦ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ በሚገኘው የባስራ ወደብ ላይ በደረሰ ጥቃት ምክንያት፣ ኢራቅ በሁሉም የነዳጅ ማስተላለፊያ ተርሚናሎች ላይ ሥራዋን ለማቆም ተገድዳለች።
* የዋጋ ንረት፦ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ዛሬ ባሳየው ጭማሪ፣ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከነበረበት ዋጋ አንጻር የ38 በመቶ ብልጫ አሳይቷል።
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የጀመሩት ጥቃት እየበረታ መሄድ እና ቴህራን በበኩሏ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ለማድረስ የጀመረችው ዘመቻ፣ የዓለም የኃይል አቅርቦት ዋስትናን አደጋ ላይ ጥሎታል። ጦርነቱ የሚቆምበት ምልክት አለመታየቱ ደግሞ በቀጣይ ቀናት የነዳጅ ዋጋ ይበልጥ ሊንር እንደሚችል ስጋት ፈጥሯል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #oilprice #globaleconomy #hormuzstrait #middleeastconflict #energycrisis #brentcrude #fuelnews #breakingnews #ኢኮኖሚ #ነዳጅ #ዜና

9 months ago
⛽ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ቀነሰ
#ethiopia | የቬንዙዌላ ነዳጅ ወደ አሜሪካ መግባቱ ቻይናን አስቆጥቷል የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቬንዙዌላ ከ30 እስከ 50 ሚሊዮን በርሜል የሚደርስ ድፍድፍ ነዳጅ ለአሜሪካ ለማቅረብ መስማማቷን ይፋ ካደረጉ በኋላ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ፈጣን ቅናሽ ማሳየቱን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።
📉 የገበያው ምላሽ፦ የዋጋ መውረድ
በትራምፕ መግለጫ ማግስት የነዳጅ ገበያው ከአንድ በመቶ በላይ ቅናሽ አሳይቷል፦
* የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ፦ ከአንድ በርሜል 60 ዶላር በታች ወርዷል።
* የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ፦ በ1.4 በመቶ ቀንሶ 56.44 ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል።
የቻይና ስጋት እና የቤጂንግ ቁጣ
ይህ ስምምነት ቬንዙዌላ 80 በመቶ የሚሆነውን የነዳጅ ምርቷን ወደምትልክላት ቻይና የምታደርገውን ኤክስፖርት ሊያስተጓጉል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፦
"የአሜሪካ ጥያቄ ዓለም አቀፍ ሕግን
የሚጥስ እና የቬንዙዌላን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ነው፤ ቬንዙዌላ በሀብቷ ላይ ሙሉ ስልጣን አላት" ሲል ድርጊቱን ኮንኗል።''
📱 ትራምፕ ምን አሉ?
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገጽ "ትሩዝ ሶሻል" (Truth Social) ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ የነዳጁ ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ጥቅም እንዲውል እንደሚቆጣጠሩት ገልጸዋል። "ይህ ነዳጅ በመርከብ ተጭኖ በቀጥታ በአሜሪካ ወደሚገኙ ወደቦች ይመጣል" ሲሉ የአሜሪካን ቀጥተኛ ተሳትፎ አረጋግጠዋል።
ይህ እርምጃ በዋሽንግተን እና በቤጂንግ መካከል ያለውን የንግድ እና የፖለቲካ ውጥረት ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊያሸጋግረው እንደሚችል ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ትራምፕ #ነዳጅ #ቬንዙዌላ #ቻይና #ኢኮኖሚ #ዓለምአቀፍዜና #አሜሪካ #የነዳጅዋጋ #trump #oilprice #venezuela

Comments