Logo
Getu Temesgen
አሜሪካ ለቴህራን ተጨማሪ የማሰቢያ ጊዜ ሰጥቻለሁ አለች
#ethiopia | በዚህም ዛሬ ይጠናቀቅ የነበረውን የተኩስ አቁም ማራዘሟን አስታውቃለች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምን እርምጃ ይወስዱ ይሆን በሚል በትኩረት ሲጠበቅ የነበረውን የተኩስ አቁም አስመልክቶ በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ውሳኔያቸውን አስፍረዋል።

ሆርሙዝን እንደዘጋን እንቀጥላለን ዛሬ የተጠናቀቀውን የተኩስ አቁም የመጨመረሻ ቀነ ገደብ ግን አራዝመናል ነው ያሉት ትራምፕ።

በዚሁ ፅሁፋቸው ኢራን ላይ ምንም አይነት ጥቃት እንደማይሰነዘር ገልፀው፤ ነገር ግን የሆርሙዝ ጉዳይ አሁንም በእኛ እጅ ነው የሚወሰዱ እርምጃዎችም ይቀጥላሉ ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ትራምፕ ወደዚህ ውሳኔ የመጡት ኢራን እቅዷን እስክታቀርብ የማሰቢያ ጊዜ ለመስጠት ነው የሚል ምክንያትን ያስቀመጡ ሲሆን ኢራናውያን ፖለቲከኞች ወጥ አቋም እንደሌላቸውና ባህሪያቸውም ተለዋዋጭ ነው በሚል ተችተዋል።

ምንም እንኳን እርሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ ፓኪስታንም ለዚህ ውሳኔ ምክንያት መሆኗን ቢቢሲ ከሪፐብሊካን ሰዎች ያገኘውን መረጃ ዋቢ አድርጎ ፅፏል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #channel1ethiopia

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.