4 months ago
አሜሪካ ለቴህራን ተጨማሪ የማሰቢያ ጊዜ ሰጥቻለሁ አለች
#ethiopia | በዚህም ዛሬ ይጠናቀቅ የነበረውን የተኩስ አቁም ማራዘሟን አስታውቃለች።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምን እርምጃ ይወስዱ ይሆን በሚል በትኩረት ሲጠበቅ የነበረውን የተኩስ አቁም አስመልክቶ በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ውሳኔያቸውን አስፍረዋል።
ሆርሙዝን እንደዘጋን እንቀጥላለን ዛሬ የተጠናቀቀውን የተኩስ አቁም የመጨመረሻ ቀነ ገደብ ግን አራዝመናል ነው ያሉት ትራምፕ።
በዚሁ ፅሁፋቸው ኢራን ላይ ምንም አይነት ጥቃት እንደማይሰነዘር ገልፀው፤ ነገር ግን የሆርሙዝ ጉዳይ አሁንም በእኛ እጅ ነው የሚወሰዱ እርምጃዎችም ይቀጥላሉ ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ትራምፕ ወደዚህ ውሳኔ የመጡት ኢራን እቅዷን እስክታቀርብ የማሰቢያ ጊዜ ለመስጠት ነው የሚል ምክንያትን ያስቀመጡ ሲሆን ኢራናውያን ፖለቲከኞች ወጥ አቋም እንደሌላቸውና ባህሪያቸውም ተለዋዋጭ ነው በሚል ተችተዋል።
ምንም እንኳን እርሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ ፓኪስታንም ለዚህ ውሳኔ ምክንያት መሆኗን ቢቢሲ ከሪፐብሊካን ሰዎች ያገኘውን መረጃ ዋቢ አድርጎ ፅፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #channel1ethiopia

በሕንድ ለኢትዮጵያዊ የኤች.አይ.ቪ. ታማሚ የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተከናወነ
#ethiopia | በሕንድ ዴልሂ የሚገኘው 'ማክስ ሱፐር ስፔሻሊቲ' ሆስፒታል፣ በደሙ ውስጥ የኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ ለሚገኝ የ43 ዓመት ኢትዮጵያዊ ስኬታማ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረጉን አስታውቋል።
ይህ የሕክምና ስኬት ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ባለባቸው ታካሚዎች ላይ ንቅለ ተከላ ማድረግ እንደሚቻል በተግባር ያሳየ በመሆኑ በዘርፉ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።
ለንቅለ ተከላው ስኬታማነት ዋና ዋና አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነጥቦች፦
ሂደቱ በጥንቃቄ በተመራ የበርካታ የሕክምና ባለሙያዎች የጋራ ጥረት የተከናወነ ነው።
የዘመናዊ የፀረ-ሬትሮ ቫይረስ ሕክምናዎች መገኘት ለቀዶ ጥገናው ስኬት ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።
ይህ ውጤት በኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ የተያዙና የኩላሊት ሕመም ያለባቸው ታካሚዎች የተሻለ ሕክምና እንዲያገኙ አዲስ ተስፋ የፈነጠቀ መሆኑ ተገልጿል።
እንደ ስፑትኒክ ዘገባ ከሆነ፣ ይህ በሕክምናው ዘርፍ የተመዘገበው ስኬት ለወደፊቱ ተመሳሳይ የጤና ችግር ላለባቸው ወገኖች ሰፊ የሕክምና አማራጭ የሚከፍት ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #channel1ethiopia #healthnews #kidneytransplant #ethiopia #indiamedical #hivcare #medicalbreakthrough #maxhospital #globalhealth

Comments