Logo
Getu Temesgen
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ9 ወራት ውስጥ ከ1.1 ሚሊየን በላይ ፓስፖርቶችን ማሰራጨቱን አስታወቀ
#ethiopia | የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለዜጎች የሰጠውን አገልግሎት በተመለከተ ዝርዝር መግለጫ ሰጥቷል። ተቋሙ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከ1.1 ሚሊየን በላይ ፓስፖርቶችን ለደንበኞች ማድረስ መቻሉን ገልጿል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ አምቦ መቃሳ እንደገለጹት፣ ተቋሙ ከመደበኛና አስቸኳይ ፓስፖርት በተጨማሪ በቪዛ እና በሌሎች ድንበር ተሻጋሪ አገልግሎቶች ላይ ውጤታማ ሥራዎችን አከናውኗል።

ፓስፖርት፦ከ1,100,000 በላይ ለዜጎች ተሰጥቷል።

ቪዛ፦824,951 ቪዛዎች ተሰጥተዋል።

የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ከ29,000 በላይ ተሰጥቷል።

*በአየርና በየብስ ድንበሮች ከ5.4 ሚሊየን በላይ ገቢና ወጪ መንገደኞች አገልግሎት አግኝተዋል።

ተቋሙ አገልግሎቱን ለማሳለጥ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ እንቅፋት የሆኑ አካላት ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል። በዚህም መሰረት፦

*በሕገ-ወጥ ደላላነት የተሰማሩ እና የአገልግሎት አሰጣጡን ስም ለማጠልሸት የሞከሩ 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እነዚህ ግለሰቦች በሕገ-ወጥ መንገድ አስቸኳይ ፓስፖርት በመሙላትና መሰል ተግባራት ላይ ተሰማርተው የተገኙ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #immigration #passport #visa #news #ኢትዮጵያ #ፓስፖርት #ኢሚግሬሽን #ዜና #አዲስአበባ

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.