የኒያ ፋውንዴሽን የአውቲዝም ማዕከል ግንባታን ለማጠናቀቅ አገር አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ አቀረበ
#ethiopia | የኒያ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነውንና ደረጃውን የጠበቀ አውቲዝም ማዕከል ግንባታን ፍጻሜ ለማድረስ መጠነ ሰፊ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር መጀመሩን በዛሬው እለት በማዕከሉ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ይህ ማዕከል በአውቲዝም እና በሌሎች የአእምሮ እድገት ውስንነቶች ላይ ለሚገኙ ዜጎች ዘመናዊ የሕክምና፣ የትምህርትና የማገገሚያ አገልግሎቶችን ለመስጠት ታቅዶ እየተገነባ ያለ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
ፋውንዴሽኑ በመንግሥት በኩል በተሰጠ 4,824 ካሬ ሜትር የቆዳ ስፋት ያለው ቦታ ላይ እያስገነባው የሚገኘውን ይህንን ማዕከል ለማጠናቀቅ የሕዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን በመግለጫው ላይ ተገልጿል።
እስካሁን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት የግንባታው ሂደት በተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ቀሪ ስራዎችን መቶ በመቶ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት የገንዘብ አቅም እንደሚያስፈልገው ተጠቁሟል።
በቀረበው ጥሪ መሠረት ማንኛውም ዜጋ በ300 ብር ብቻ አንድ የሕንጻ ግንባታ ግብዓት በመግዛት ለታሪካዊው ፕሮጀክት አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ ቀርቧል።
"አውቲዝም እና ሰብዓዊነት - እያንዳንዱ ሕይወት ዋጋ አለው" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ንቅናቄ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ይህ ማዕከል ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፣ ባለፉት ዓመታት በአውቲዝም ምክንያት ልጆቻቸውን የት እንደሚያደርሱ ግራ ተጋብተው ለነበሩና በኢኮኖሚም ሆነ በማኅበራዊ ሕይወት ለተጎዱ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ትልቅ ተስፋና እፎይታን እንደሚሰጥ ይታመናል።
ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልጉ ግለሰቦች፣ ተቋማትና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሚከተሉት አማራጮች ማበርከት ይችላሉ፡-
📌 በቴሌ ብር ወደ 9616 OK ብለው በመላክ 1 ብር ወይም ከዚያ በላይ መለገስ ይችላሉ።
📌 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጭር የሒሳብ ቁጥር 2135 ላይ መለገስ እንደሚቻል ተገልጿል።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

4 months ago