ኢራን የዓለምን ጉሮሮ ለፖኪስታን ከፈተች
#ethiopia | ለሳምንታት ተዘግቶ በቆየውና ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ በኩል፣ 20 ተጨማሪ የፓኪስታን ሰንደቅ ዓላማ ያረፉባቸው መርከቦች እንዲያልፉ ኢራን ፈቃድ መስጠቷ ተረጋገጠ። ይህ ውሳኔ በመካከለኛው ምሥራቅ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ለማርገብና የቀጠናውን መረጋጋት ለመመለስ ትልቅ ተስፋ የፈነጠቀ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር በሰጡት መግለጫ፣ የኢራንን ውሳኔ "ገንቢ እና የሚደነቅ" ሲሉ ገልጸውታል። ሚኒስትሩ አክለውም ውይይት እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ለቀጠናው ጦርነት ብቸኛ መፍትሔ መሆናቸውን በአጽንኦት ተናግረዋል።
ይህ እርምጃ የተሰማው፣ ፓኪስታን ዛሬ እሁድ በኢስላማባድ የምታስተናግደው የአራትዮሽ ስብሰባ ከመጀመሩ ጥቂት ቀደም ብሎ ነው። በስብሰባው ላይ የቱርክ፣ የግብፅ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ እና የፓኪስታን ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በመገኘት፣ ለአንድ ወር በዘለቀው የአሜሪካ-እስራኤል እና የኢራን ግጭት ዙሪያ መፍትሔ ለመፈለግ ይመክራሉ።
ከመጋቢት ወር መጀመሪያ አንሥቶ በተግባር ተዘግቶ የቆየው የሆርሙዝ ሰርጥ፣ ከጦርነቱ በፊት በቀን በአማካይ እስከ 138 መርከቦች የሚያልፉበት ወሳኝ የንግድ መስመር መሆኑ ይታወቃል። የዛሬው ውሳኔም ለዓለም አቀፍ ንግድ እና ለቀጠናው ሰላም አዲስ በር ሊከፍት እንደሚችል ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #iran #pakistan #hormuzstrait #geopolitics #middleeastnews #diplomacy #globaltrade #breakingnews

2 months ago