Logo
Getu Temesgen
አሜሪካ ደቡብ አፍሪካ ከቡድን 7 (G7) ጉባኤ እንድትገለል ፈረንሳይ ላይ ጫና እያሳደረች ነው
#ethiopia | በፈረንሳይ ኤቪያን ከተማ በግንቦት 2018 ዓ.ም (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) በሚካሄደው የቡድን 7 (G7) አባል ሀገራት ጉባኤ ላይ ደቡብ አፍሪካ እንዳትሳተፍ አሜሪካ በፈረንሳይ ላይ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እያሳደረች መሆኑን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ይህ የአሜሪካ እንቅስቃሴበሁለቱ ሀገራት መካከል ለወራት የዘለቀውና እየተሻከረ የመጣው ግንኙነት ውጤት እንደሆነ ተገልጿል።

ደቡብ አፍሪካ የአሜሪካ የቅርብ ወዳጅ በሆነችው እስራኤል ላይ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የመሰረተችው የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ዋነኛው የውጥረት ምንጭ ሆኗል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ነጭ አፍሪካውያን ከሀገሪቱ እየተሰደዱ ነው” በማለት የሰነዘሩት አወዛጋቢ መከራከሪያ ለዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫው ተጨማሪ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ ውሳኔ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የአፍሪካን ድምፅ የመወከል አቅም ባላት ደቡብ አፍሪካ እና በምዕራባውያን ኃያላን መካከል ያለውን ልዩነት ይበልጥ ያሰፋዋል ተብሎ ተሰግቷል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #southafrica #usa #g7summit #france #diplomacy #internationalrelations #g7 #breakingnews #africanews #etbusinessview

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.