Logo
Getu Temesgen
ታሪካዊው ሆርቲፍሎራ ኤክስፖ 2026
ከ50 በላይ ሀገራት በአዲስ አበባ ይሳተፋሉ

​የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር (EHPEA) ከኤች.ፒ.ፒ. (HPP) ኤግዚቢሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 10ኛው ዓለም አቀፍ የሆርቲካልቸር ንግድ ትርዒት ከመጋቢት 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።

​ ከ50 በላይ ሀገራትን የሚወክሉ ከ150 በላይ አምራቾች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችና የፋይናንስ ተቋማት በአንድ ጣሪያ ስር ይገናኛሉ።

​የሆርቲካልቸር ዘርፍ ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ 564.89 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኘ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ 2ኛ እንዲሁም በዓለም 5ኛ ግዙፍ የአበባ ላኪ ሀገር መሆን ችላለች።

​ኤክስፖው መንግሥት አዲሱን የ10 ዓመት የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ እና የ15 ዓመቱን የአቮካዶ ልማት መርሐ ግብር ይፋ ካደረገ በኋላ የሚከናወን የመጀመሪያው ትልቅ ዓለም አቀፍ መድረክ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።

​የበቆይታው ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)፣ ዘላቂ ፋይናንስ፣ የምግብ ደህንነት እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያተኮሩ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ውይይቶች ይካሄዱበታል።

​ይህ የንግድ ትርዒት የአገሪቱን እምቅ አቅም ለዓለም ገበያ ይበልጥ በማስተዋወቅ፣ አምራቾችን ከዓለም አቀፍ ገዢዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ትልቅ ድልድይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

​#getu #ethiopia #ehpea #horticulture #flowerindustry #export #economy #addisababa #hortiflora2026 #ኢትዮጵያ #ሆርቲካልቸር #ኤክስፖ #አበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.