2 months ago
"በተቀናጀ ዐቅም ተግተን ከሠራን፤ ብልጽግና ሕይወት፣ ድህነት ታሪክ ይሆናል" - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
********************
ለም አፈር፣ ንጹሕ ውኃና ሥራ ወዳድ ሕዝብ ባለበት ምድር፣ በተቀናጀ ዐቅም ተግተን ከሠራን - ብልጽግና ሕይወት፣ ድህነት ታሪክ ይሆናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ባጋሩት መልዕክት፥ የሐይቅ ዙሪያ አርሶ አደሮች መሬት እና እርሻቸውን ከጫት ወደ አትክልት እና ፍራፍሬ ክላስተር ማሸጋገራቸውን ጠቅሰዋል።
በዚህም አርሶ አደሮቹ የአካባቢን አንጻራዊ የልማት ጉልበት መለየት እና ወደ አትራፊ እና ዘላቂ የግብርና ጎዳና መሸጋገር ይገባል የሚለውን ሀገራዊ መርህ እና ስምሪት ተግብረው አሳይተዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሎጎ ሐይቅ ሪዞርት ምርቃት ላይ ባስተላለፉት ታሪካዊ መልዕክት፣ "ሐይቅ የታሪክ ብቻ ሳይሆን የፍራፍሬ ልማት፣ የተትረፈረፈ ምርት፣ የውበትና የጥጋብ ሥፍራ መሆን አለባት" ብለው እንደነበር አስታውሰዋል።
ዛሬ የርሳቸው ቃል ፍሬ አፍርቶ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን፣ ተሁለደሬ ወረዳ የጎበያ ቀበሌ በአትክልት እና ፍራፍሬ ክላስተር ተሸፍኗል፤ ይህ የልማት ትጋት ኢትዮጵያ ለጀመረችው የምግብ ሉዓላዊነት ተደማሪ ጥሪት እና ወረት ነው ብለዋል።
መንግሥት ለዚህ ልማት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል፤ ለም አፈር፣ ንጹሕ ውኃና ሥራ ወዳድ ሕዝብ ባለበት ምድር፣ በተቀናጀ ዐቅም ተግተን ከሠራን - ብልጽግና ሕይወት፣ ድህነት ታሪክ ይሆናል ነው ያሉት።
#ethiopia #horticulture #amhararegion #ebc

4 months ago
ሬድ ፎክስ ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የተፈጥሮ ፀረ ተባይ ነፍሳት ማራቢያ ማዕከል በይፋ አስመረቀ
#ethiopia | በአለም አቀፍ የአበባ ንግድ ዘርፍ ታዋቂ በሆነው ዱመን ኦሬንጅ ስር የሚንቀሳቀሰው ሬድ ፎክስ ኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ጠቃሚ ነፍሳትን የሚያረባ ዘመናዊ ማዕከል በቆቃ ነገዎ በሚገኘው የእርሻ ቦታው ስራ አስጀምሯል።
ይህ አዲስ መሠረተ ልማት በኢትዮጵያ የሆርቲካልቸር ኢንዱስትሪ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ያለ ኬሚካል ሰብሎችን በተፈጥሯዊ መንገድ በመንከባከብ ዘላቂ ግብርናን ማስፋፋት እንደሚቻል ያሳየ ትልቅ እመርታ ነው።
ማዕከሉ በዋናነት በማስዋቢያ ዕፅዋትና አበቦች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ተባዮችን ተለቅመው እንዲጠፉ የሚያደርጉ ስዊርስኪ እና ካሊፎሚከስ የተባሉ ጠቃሚ ትሎችን ያመርታል።
ይህም ሰው ሰራሽ ፀረ ተባይ ኬሚካሎችን በከፍተኛ ደረጃ በማስቀረት በተፈጥሯዊ መንገድ ተባይን የመቆጣጠር ዘዴን በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር ያስችላል።
የዚህ የቴክኖሎጂ ውጤት ጥቅሞች ዘርፈ ብዙ ሲሆኑ በኬሚካል ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ የሰራተኞችንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ጤና ይጠብቃል።
በተጨማሪም ወደ ውጭ በሚላኩ የአበባ ምርቶች ላይ የሚኖረውን የኬሚካል ቅሪት ስጋት በማስቀረት የሀገሪቱን ምርት በዓለም አቀፍ ገበያ ተመራጭ ያደርገዋል።
ጠቃሚ ነፍሳቱን ከውጭ ለማስገባት የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከመታደጉም በላይ በአየር ትራንስፖርት ጭነት ሳቢያ የሚፈጠረውን የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀትን በእጅጉ ይቀንሳል።
ይህ ማዕከል በዓመት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጠቃሚ ነፍሳትን የማምረት አቅም ያለው ሲሆን ይህም በ40 ሄክታር መሬት ላይ ለሚለማው እርሻ በቂ የተፈጥሮ መከላከያ ለማቅረብ ያስችላል።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ዮርዳኖስ ጀማል ሽኩሪ እንደገለጹት ይህ ማዕከል ተፈጥሮን በጥበብ በመጠቀም ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ትልቅ ማሳያ ሲሆን ሌሎች የዘርፉ ተዋናዮችም ይህንን ፈር ቀዳጅ አሰራር እንዲከተሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በኦሮሚያ ክልል እአአ በ2003 የተቋቋመው ሬድ ፎክስ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እስከ 100 ሄክታር መሬት ላይ በመንቀሳቀስ በዓመት ከ120 ሚሊዮን በላይ የተቆረጡ አበቦችና አፅቆችን ለውጭ ገበያ ያቀርባል።
ተቋሙ ለአካባቢው ነዋሪዎች እስከ 2500 የሚደርስ የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 72 በመቶ ያህሉ ሴቶች ናቸው። ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ በጤና አገልግሎት እና በኤሌክትሪክ አቅርቦት ዙሪያ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በላቀ ደረጃ እየተወጣ ይገኛል።
ይህ የቆቃ ነገዎ የነፍሳት ማራቢያ ማዕከል በምስራቅ አፍሪካ ከኬንያና ታንዛኒያ በመቀጠል ሶስተኛው ቢሆንም በይዘቱና በዘመናዊነቱ ግን ኢትዮጵያን በቀጠናው ቀዳሚ ያደርጋታል።
#horticulture #agriculture #environment #sustainability #ecofriendly #redfoxethiopia #dumenorange #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

7 months ago
ታሪካዊው ሆርቲፍሎራ ኤክስፖ 2026
ከ50 በላይ ሀገራት በአዲስ አበባ ይሳተፋሉ
የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር (EHPEA) ከኤች.ፒ.ፒ. (HPP) ኤግዚቢሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 10ኛው ዓለም አቀፍ የሆርቲካልቸር ንግድ ትርዒት ከመጋቢት 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
ከ50 በላይ ሀገራትን የሚወክሉ ከ150 በላይ አምራቾች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችና የፋይናንስ ተቋማት በአንድ ጣሪያ ስር ይገናኛሉ።
የሆርቲካልቸር ዘርፍ ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ 564.89 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኘ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ 2ኛ እንዲሁም በዓለም 5ኛ ግዙፍ የአበባ ላኪ ሀገር መሆን ችላለች።
ኤክስፖው መንግሥት አዲሱን የ10 ዓመት የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ እና የ15 ዓመቱን የአቮካዶ ልማት መርሐ ግብር ይፋ ካደረገ በኋላ የሚከናወን የመጀመሪያው ትልቅ ዓለም አቀፍ መድረክ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።
የበቆይታው ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)፣ ዘላቂ ፋይናንስ፣ የምግብ ደህንነት እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያተኮሩ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ውይይቶች ይካሄዱበታል።
ይህ የንግድ ትርዒት የአገሪቱን እምቅ አቅም ለዓለም ገበያ ይበልጥ በማስተዋወቅ፣ አምራቾችን ከዓለም አቀፍ ገዢዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ትልቅ ድልድይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
#getu #ethiopia #ehpea #horticulture #flowerindustry #export #economy #addisababa #hortiflora2026 #ኢትዮጵያ #ሆርቲካልቸር #ኤክስፖ #አበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

8 months ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፍቅረኛሞችን ቀን በማስመልከት ከ3,400 ቶን በላይ አበባ አጓጓዘ
#ethiopia | እንደ ኢትዮጵያ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማኅበር (EHPE) መረጃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘንድሮው የቫላንታይን ወቅት ከፍተኛ መጠን ያለው የአበባ ምርት ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች በማጓጓዝ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል። አየር መንገዱ የዓለምን የፍቅር በዓል ፍላጎት ለማርካት በሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ (ከጥር 14 እስከ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም) 3,425.188 ቶን አበባ ለዓለም ገበያ አጓጉዟል።
ቁልፍ መረጃዎች፡
* መዳረሻዎች፦ የአበባ ምርቶቹ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ እስያ እና አፍሪካ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ገበያዎችን አዳርሰዋል።
* የኢኮኖሚ ፋይዳ፦ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቅ አበባ ላኪ ሀገር ስትሆን፣ ዘርፉ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
* የገቢ ድርሻ፦ ባለፈው በጀት ዓመት ከሆርቲካልቸር ዘርፍ ከተገኘው 565 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ውስጥ 80% የሚሆነው ድርሻ የተያዘው በአበባ ምርት ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopianairlines #flowerexport #ethiopia #valentineseason #horticulture #flyethiopian #economy

Comments