2 months ago
የኢትዮ- ጣሊያን የኮንስትራክሽንና የመሰረተ ልማት ፎረም ተጀመረ
#ethiopia | ዛሬ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም ተጀመረ።
ፎረሙ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ ሚኒስትሮች እና የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርና የዓለምቀፍ ትብብር ሀላፊ ማሪያ ትሪፖዲ በተገኙበት ተጀምሯል።
አሁን ላይ በመዲናችን የንግድ እንቅስቃሴ እያደገ፣ የኢንቨስትመንት ፍሰቱም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ እንደተናገሩት አዲስ አበባ በፍጥነት እየተለወጠች በመሆኗ፣ ይህ የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም መካሄዱ ወቅታዊ፣ ትክክለኛና እጅግ አስፈላጊ ነው።
የጣሊያን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያጠናክሩበት ፎረም ተካሄደ።
መጋቢት 16 ቀን 2018 አ.ም የኢትዮጵያን የመሠረተ ልማት አድማስ የሚያሰፋና የከተማ ውበት ሽግግርን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ተብሎ የታመነበት የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሠረተ ልማት እና የከተማ ተሃድሶ ፎረም ተከፍቷል።
ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው መድረክ፥በጣሊያን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር (MAECI) አዘጋጅነት የተሰናዳ ሲሆን፥ በጣሊያን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በመድረኩ ላይ ተገኝቷል።
ፎረሙ የጣሊያንን ዘመናዊ የምህንድስና ጥበብ እና የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ልምድ ከኢትዮጵያ የልማት ፍላጎት ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ነው።
በመድረኩ ላይ ከ25 በላይ ግዙፍ የጣሊያን ኩባንያዎች እና የኢንዱስትሪ ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል::
ቀልጣፋ የትራንስፖርት ትስስር መፍጠር ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ውብ የማድረግ ሥራ መስራት እንዲሁም ዘላቂ የኃይልና የውሃ አቅርቦት ግንባታን ማፋጠን የግንኙነቱ ዋና አላማ ነው።
ይህ መድረክ የሁለቱን አገራት የቆየ ግንኙነት ወደ ላቀ የንግድና የኢንቨስትመንት ምዕራፍ የሚያሸጋግር ጠንካራ ድልድይ ነው ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen)
#getutemesgen #ehpea #horticultureethiopia #economynews #ethiopianexports #hortiflora2026 #flowerindustry

ታሪካዊው ሆርቲፍሎራ ኤክስፖ 2026
ከ50 በላይ ሀገራት በአዲስ አበባ ይሳተፋሉ
የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር (EHPEA) ከኤች.ፒ.ፒ. (HPP) ኤግዚቢሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 10ኛው ዓለም አቀፍ የሆርቲካልቸር ንግድ ትርዒት ከመጋቢት 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
ከ50 በላይ ሀገራትን የሚወክሉ ከ150 በላይ አምራቾች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችና የፋይናንስ ተቋማት በአንድ ጣሪያ ስር ይገናኛሉ።
የሆርቲካልቸር ዘርፍ ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ 564.89 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኘ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ 2ኛ እንዲሁም በዓለም 5ኛ ግዙፍ የአበባ ላኪ ሀገር መሆን ችላለች።
ኤክስፖው መንግሥት አዲሱን የ10 ዓመት የሆርቲካልቸር ስትራቴጂ እና የ15 ዓመቱን የአቮካዶ ልማት መርሐ ግብር ይፋ ካደረገ በኋላ የሚከናወን የመጀመሪያው ትልቅ ዓለም አቀፍ መድረክ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል።
የበቆይታው ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI)፣ ዘላቂ ፋይናንስ፣ የምግብ ደህንነት እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያተኮሩ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ውይይቶች ይካሄዱበታል።
ይህ የንግድ ትርዒት የአገሪቱን እምቅ አቅም ለዓለም ገበያ ይበልጥ በማስተዋወቅ፣ አምራቾችን ከዓለም አቀፍ ገዢዎች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ ትልቅ ድልድይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
#getu #ethiopia #ehpea #horticulture #flowerindustry #export #economy #addisababa #hortiflora2026 #ኢትዮጵያ #ሆርቲካልቸር #ኤክስፖ #አበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen