ለ10 ዓመታት ስቃይ የነበረው 10 ኪሎ ግራም የስብ እጢ በስኬት ተወገደ!
#ethiopia | በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ሙዱላ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስገራሚ የሚባል የሕክምና ስኬት ተመዝግቧል። አንዲት የ35 ዓመት ታካሚ ለ10 ዓመታት ያህል በጀርባዋ ላይ ተሸክማው የቆየችውና 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ግዙፍ የስብ እጢ (Giant Lipoma) በቀዶ ሕክምና በሰላም ተወግዶላታል።
የቦሄ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እኚህ ታካሚ፣ እጢው በፈጠረባቸው ከፍተኛ የክብደት ጫና ምክንያት ለዓመታት ለከፋ ስቃይና ለእንቅስቃሴ መገደብ ተዳርገው ቆይተዋል። ሆኖም በጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቱ ዶክተር ዮሴፍ ታፈሰ የሚመራው የሕክምና ቡድን ለሦስት ሰዓታት ባደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት ቀዶ ሕክምና፣ እጢውን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ችሏል።
በአሁኑ ወቅት ታካሚዋ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙና በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል።
ይህ ውጤት የሙዱላ ሆስፒታል ውስብስብ የሕክምና አገልግሎቶችን የመስጠት አቅሙ እያደገ መምጣቱን ያሳየ ታላቅ ስኬት ነው።
ለዚህ ስኬት የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሕክምና ቡድን አባላት፦
* ዶ/ር ዮሴፍ ታፈሰ (የቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት)
* ዶ/ር ሲሳይ አሸናፊ (ረዳት ሐኪም)
* አስራት ከበደና ናትናኤል ቦቶላ (የአንስቴዥያ ባለሙያዎች)
* ሲሳይ ንጋቱና ሙሉጌታ (ስክረብ ነርሶች)
* ዘውዴ ማንደሮና ጩፋሞ ማሴቦ (ራነር ነርሶች)
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #southtv #mudulahospital #healthnews #ethiopia #medicalsuccess #tembaro #surgerysuccess #healthupdate

3 months ago