ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት የሃዘን መግለጫ ሰጡ
#fastmereja I የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም ቱፋ፣ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ በሰማዕትነት ማረፋቸውን ተከትሎ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሃዘናቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ በኤምባሲው በተዘጋጀው የሃዘን መግለጫ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት በመዝገቡ ላይ መልዕክታቸውን አስፍረዋል።
ሼክ ኢብራሂም ቱፋ ለኢራን ህዝብ እና መንግስት ያላቸውን ጥልቅ አጋርነት የገለጹ ሲሆን፣ ድርጊቱን "በእስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ የተፈጸመ አሰቃቂ ጥቃት" ሲሉ ጠርተውታል።
ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የአሊ ኻሜኒ ማረፍ "ኪሳራው ለኢራናውያን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ላሉ ሙስሊሞች ሁሉ ነው" በማለት የችግሩን ዓለም አቀፋዊነት ገልጸዋል።

3 months ago