አዋሽ ባንክ በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን የኢፍጣር መርሃ-ግብር አካሄደ!
#fastmereja : አዋሽ ባንክ የ1447ኛውን የረመዳን ወር ፆም ምክንያት በማድረግ የረመዳን ወር የሚታወቅበትን የመረዳዳት እና የመተጋገዝ እሴት ለማጎልበት ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን የኢፍጣር መርሃ-ግብር አካሂዷል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው እንደገለፁት ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ላለፉት 31 ዓመታት ሰው-ተኮር በሆኑ ተግባራት ላይበመሳተፍ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል።
በተለይም በማዕያ: ማጋራት፤ በትምህርት፣ በጤና፣ በስራ ፈጠራ እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን የመኖሪያ ቤት ግንባታ ከፍተኛ በጀት በመመደብ በርካታ ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ነዉ የገለፁት።
እያይዘውም እዋሽ ባንክ ባሉት ከ1,005 በላይ ቅርንጫፎች አማካይነት ከ3.5 ሚሊዮን በላይከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞችን ማፍራቱን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በሁሉም ቅርንጫፎቹ የወለድ ነፃ ባንክ አገልግሎት (Awash Ikhlas) ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ የፋይናንስ መፍትሄዎችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ጨምረው ገልጸዋል።
ባንኩ እስካሁን በወለድ ነፃ ፋይናንስ ዘርፍ ብቻ ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ የሃላል ፋይናንስ አገልግሎት ለማቅረብ እንዲሁም በሐጅ አገልግሎት ዘርፍም መሪ ባንክ በመሆን የሐጅ ተጓዦች የገንዘብ አሰባሰብን በአስተማማኝ እና ተደራሽ በሆነ ሁኔታ አከናውኗል።
አዋሽ ባንክ የማህበረሰቡ አካል እንደመሆኑ መጠን በደስታም ሆነ በሃዘን ጊዜ ከማህበረሰቡ 97 በመቆም ለወገን ደራሽ የሆነ ባንከ በመሆኑ በቀጣይም ተመጣጣኝ፣ ፍትሃዊ እና ተደራሽ የፋይናንስ አገልግሎት ማቅረቡን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

6 months ago