አዋሽ ባንክ በየስር ሌና የበጎ አድራጎት ድርጅት የኢፍጣር መርሃ-ግብር አካሄደ!
📆 የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
📍አዲስ አበባ
አዋሽ ባንክ ከመደበኛው የባንክ አገልግሎት ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ቀጥሏል። ባንኩ 1447ኛውን የረመዳን ወር ፆምን ምክንያት በማድረግ፣ ዛሬ ሰኞ የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው የስር ሌና የበጎ አድራጎት ድርጅት የኢፍጣር መርሃ-ግብር አከናውኗል።
ባንኩ ይህንን የድጋፍ መርሃ-ግብር ያዘጋጀው የረመዳን ወር የሚታወቅበትን የመረዳዳት እና የመተጋገዝ እሴት ለማጎልበት መሆኑ ተገልጿል።
የስር ሌና የበጎ አድራጎት ድርጅት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ ደካማ ወገኖችን በመደገፍ ረገድ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ተቋም ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት 1,700 የሚሆኑ ዜጎችን በቀጥታ በመርዳት ላይ ይገኛል።
ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት፣ አቅመ ደካማ አረጋውያን እና ሴቶች የትኩረት ማዕከሉ ናቸው። ለተረጂዎቹ የምግብ፣ የትምህርት እና የልብስ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ የአቅመ ደካማ ድጋፍ ስራዎችን ያከናውናል። ዜጎች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የወጣቶች የሥራ ማስጀመር ድጋፎችን ይሰጣል።
አዋሽ ባንክ መሰል የበጎ አድራጎት ተግባራት ማህበራዊ ትስስርን እንደሚያጠናክሩ ገልጾ፣ በቀጣይም መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
#fastmereja I #ማህበራዊ

6 months ago