Logo
Getu Temesgen
🏃‍♀️ የሴቶች ቀን በሩጫ ይከበራል!
የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ምዝገባ ነገ ይጀምራል 🏃‍♀️
#ethiopia | ​የኢትዮጵያ ሴቶችን ስኬትና ጥንካሬ የምናከብርበት፣ 23ኛው ዓመታዊ የ"ቅድሚያ ለሴቶች" 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ምዝገባ ነገ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በይፋ ይጀምራል።

​📅 የውድድሩ ቀን፦ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም.
📍 መነሻና መድረሻ፦ ቦሌ አትላስ ሆቴል አቅራቢያ
💰 የመመዝገቢያ ዋጋ፦ 590 ብር

​🎁 ልዩ የቅናሽ እድሎች፦
​📱 በኤም-ፔሳ (M-Pesa) ለሚመዘገቡ፦ 15% ቅናሽ
​💳 በዳሽን ባንክ ሱፐር አፕ ለሚመዘገቡ፦ 10% ቅናሽ

​🌟 የዘንድሮው ልዩ ገጽታዎች፦
​የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር በመክፈቻው ላይ ተገኝታለች።

​የዘንድሮው መልዕክት፦ "በመላ ኑሪ - በኮንፊደንስ ሩጪ" (በዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ የቀረበ)።

​ምዝገባው በኤም-ፔሳ፣ በዳሽን ሱፐር አፕ እና በአራት የሳፋሪኮም ሱቆች ይከናወናል።

​የታላቁ ሩጫ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ እንደገለጹት፣ ውድድሩ የሴቶችን ተሳትፎ ከማሳደግ ባለፈ የጤና ግንዛቤን ከማህበረሰብ ተሳትፎ ጋር ለማስተሳሰር ትልቅ ፋይዳ አለው።

​እናንት የሀገሬ ሴቶች፤ ጥንካሬያችሁን ለማሳየትና ለጤናችሁ ለመሮጥ ዝግጁ ናችሁ? ነገ ምዝገባ እንዳያመልጣችሁ!

​#womenrunethiopia #safaricomethiopia #mpesa #dashanbank #ቅድሚያለሴቶች #greatethiopianrun #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.