Logo
FastMereja
አዲስ መመሪያ፡ ያለ ስልጠና ሰርተፊኬት ጋብቻ አይፈቀድም!
#fastmereja ​የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የፍቺ ቁጥር ለመቀነስ አዲስ የአሰራር ስርዓት ሊዘረጋ መሆኑን አስታወቀ። በዚህም መሰረት ማንኛውም ተጋቢ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና ሰርተፊኬት ሳይዝ ወደ ጋብቻ መግባት የማይችልበት አሰራር ተግባራዊ ይሆናል።

​ተፈጻሚነት፦ አሰራሩ በሚቀጥለው ዓመት ስራ ላይ እንዲውል ዝግጅት መጠናቀቁን የሚኒስቴሩ የአረጋውያንና ቤተሰብ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተስፋዬ ሮበሌ ገልጸዋል።

​ስራው ከሃይማኖት ተቋማትና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመመካከር የሚከናወን ይሆናል። ለትዳሮች መፍረስ ዋነኛው ምክንያት የግንዛቤ እጥረት በመሆኑ፣ ይህንን ለመፍታት የስልጠና ማኑዋሎች ተዘጋጅተዋል። በቤተሰብ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ተቋማት ስራቸውን በቅንጅት ለመስራት የጋራ ፎረም መስርተዋል።

​የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት፣ የፍቺ መጠን ካለፉት ዓመታት አንጻር የ 54 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ይህ አሃዝ ሚኒስቴሩ መሰል ጥብቅ እርምጃዎችን እንዲወስድ ምክንያት ሆኗል ሲል ሸገር ሬዲዮ ነው የዘገበው።

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.