Logo
Getu Temesgen
🏃‍♂️ አዳማ በምሽት ሩጫ ልትደምቅ ነው! 🌃✨

​"የ24 ሰዓት ንቁ ከተማ ለመሆን ታሪክ እየተሰራ ነው!"
#ethiopia | ​የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከላንድ አፍሪክ ኢቨንትስ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ታሪካዊውና የመጀመሪያው "የአዳማ የምሽት ሩጫ" (Adama Night Run) በመጪው ቅዳሜ በድምቀት ይካሄዳል።

​የሩጫው ልዩ ድባብ:

✅ አዲስ ልምድ:
በአዳማ አዳዲስ የኮሪደር ልማቶች እና የብርሃን ስራዎች ታጅቦ የሚደረግ የ5 ኪ.ሜ የሌሊት ውድድር።

✅ ቱሪዝም:
አዳማን የቀን ብቻ ሳይሆን የሌሊትም የቱሪስት መዳረሻ (Night Tourism) ለማድረግ ያለመ።

✅ ድምቀት:
ከ15,000 በላይ ተሳታፊዎች፣ አትሌቶች፣ የሙዚቃ ዝግጅቶች እና ደማቅ ኩነቶች ይጠበቃሉ።

​የዝግጅቱ ስራ አስኪያጅ አርቲስት እሳይያስ መለሰ፤ "አላማችን አዳማን በቱሪዝም ካርታ ላይ ጎልታ እንድትታይ ማድረግ ነው" ሲል ገልጿል። እስከ አሁን ከ10,000 በላይ ቲሸርቶች ተሸጠዋል።

​በዚህ ታሪካዊ ምሽት የአዳማን ውበት በሩጫ ለማድመቅ ተዘጋጅተዋል?

​#adamanightrun #nighttourism #adama #oromiatourism #landafrick #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.