🌼 እንኳን ለ"ቲካሻ-ቤንጊ" (የሸኮ ብሔረሰብ የምስጋና በዓል) በሰላም አደረሳችሁ! 🌼
"Dacha íti Tikasha Bengikn Zhazha Sakuke!"
#ethiopia | "ቲካሻ-ቤንጊ" በሸኮ ብሔረሰብ ዘንድ "የምስጋና ዓመት" ማለት ሲሆን፤ ፈጣሪ ለሰው ልጆች የሰጠውን ቸርነትና በረከት የሚመሰገንበት ታላቅ የቱባ ባህል መገለጫ ዕለት ነው።
በዓሉ ለምን ይከበራል?
🌾 የተዘራው እህል በተፈጥሮ አደጋ እና በተባይ ሳይበላሽ ለምርት በመብቃቱ፣
🕊️ በሀገር ላይ ሰላምና ጤና በመስፈኑ፣
🍯 ቀፎው ማር በማስገኘቱ ለፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብ ነው።
የበዓሉ ልዩ ክዋኔዎች፡
የምርት ጥምጣም:
ከአዲሱ እህል የተዘጋጁ ምግቦች በቅድሚያ በባላባቶች ከተቀመሱ በኋላ ለህዝቡ ይዳረሳሉ።
የዘር ምርቃት: የሀገር ሽማግሌዎች እና ባላባቶች ለቀጣይ ዓመት የሚሆን የእርሻ ዘር ተቀብለው ይመርቃሉ።
የጥጋብ በዓል: ቲካሻ ቤንጊ ከሃይማኖታዊው "ሚያንጉ" ስርዓት በተለየ መልኩ በአደባባይ በደስታ፣ በጭፈራ እና በፌሽታ የሚከበር የጥጋብ በዓል ነው።
ይህ በዓል የሸኮ ህዝብ ለተፈጥሮ ህግጋት ያለውን ጥልቅ ግንዛቤ እና ስነ-ምግባር የሚያሳይ ነው።
እንኳን ለ3ኛው "ቲካሻ-ቤንጊ" በዓል አደረሳችሁ!
ሙባረክ አበበ
#sheko #tikashabengi #culture #thanksgiving #ethiopia #harvestfestival #southwestethiopia

7 months ago